🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.17K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-11 16:41:30
3.8K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 16:40:31 በቅንጅት በመስራት እና ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ እጣ ወጥቶላቸው  ወደ ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎችን በቀጣይ ሶስት ሳምንታት  ማስገባት ይገባል ተባለ

በቤቶች የተመረጡ ስራዎችን ማጠናቀቅ እና የአሳታፊ ፕሮጀክት መዝጋት ስራዎች የ15 ቀናት እቅድ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን እጣ ወጥቶባቸው ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎች ለማስገባት ከተጀመረው ፍጥነት በላይ በመሄድ በቀንም በምሽትም በቅንጅት በመስራት በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ ይገባል ያሉት አቶ ሽመልስ ታምራት በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ናቸው ፡፡

ኃላፊው አክለውም ባለው አጭር ጊዜ ቀሪ ስራዎች ነዋሪውን በማሳተፍ እንዲሰሩ እና  የገባ አና ያልገባ ነዋሪም ተለየቶ እንዲቀርብ ብለዋል፡፡

በግምገማው በዋናነት ለነዋሪ በተላለፉ በ7ቱ ቅርንጫፎች ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪው እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ምቹ ለማድረግ ቀሪ የተመረጡ ስራዎች የተመሩበት ሁኔታ ፤ ለመሰረተ ልማት ተቋማት ከቤቶች በኩል ያሉ ስራዎች በማጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎች እና የመሰረተ ልማት ተቋማት በሚፈለገው ልክ እየሰሩ መሆናቸው በዝርዝር ታይቷል፡፡

በግምገማው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ፣ ም/ስራ አስኪያጆች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
4.1K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 22:16:49
እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞችን ወደቤታቸው ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ የደረሰበት ደረጃ ተጎበኘ

በነባር ግንባታ ኘሮግራም በ40/60  በሰሚት እና በ20/80  በፉሪ ሀና እንዲሁም አዲስ የተጀመሩ የመጀመሪያ ዙር የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶች እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም አጠናቆ ነዋሪውን ወደ ቤቱ ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ በቢሮው እና በኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ።

ጉብኝቱ በዋናነት ነዋሪው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፤ የተጓደሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ያለበት ደረጃ ላይ ያተኮረ ሲሆን በጉብኝቱ ማየት እንደተቻለው ቀሪ ጥቃቅን ስራዎችን ቤቶች እያጠናቀቀ መሆኑ ፤ ውሀ እና ፍሳሽ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ እና መብራትም ነዋሪውን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን መመልከት ተችሏል።

ነገር ግን በፉሪ ሀና ሳይት ተደራሽ መንገድ ለነዋሪው ከመፍጠር አኳያ ያለው እንቅስቃሴ ደካማ በመሆኑ መንገዶች ባለስልጣን መፍጠን እንዳለበት በጉብኝቱ ላይ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች አሳስበዋል።

የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን በታሰበለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ወቅቱ የክረምት መሆኑ እና የወሰን ማስከበር ችግር የነበረበት ቢሆንም በተቻለ መጠን የመጀመሪያውን ዙር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በተደረገው ጉብኝት ለመረዳት ተችሏል።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
6.2K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:44:59
5.0K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:43:32 የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ 81 በመቶ ደርሷል

የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ ከሚያከናውንባቸው አካባቢዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተገነቡባቸው መንደሮች ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣኑ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ መፋጠን ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው የመግቢያና መውጫ የአክሰስ መንገዶችን ከመገንባት ባለፈ፣ ለቤት ልማት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውሉ የውስጥ ለውስጥ እና  ወደ ዋና ዋና መንገዶች የሚያደርሱ መጋቢ መንገዶችን በመገንባት ለአገልግሎት ሲያበቃ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ በከተማዋ ምስራቃዊ ክፍል የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር አንዱ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበረበት የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም እየተገነባ የሚገኘው የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ ለጋራ መኖርያ ቤቶች ነዋሪዎች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ይታመናል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ8 እስከ 15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡ አሁን ላይ 800 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የለበሰ ሲሆን፣ በቀሪው 200 ሜትር ላይ ደግሞ አስፋልት ለማልበስ የሚያስችሉ የግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የዚህ ፕሮጄክት የግንባታ ፊዚካል አፈፃፀም 81 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
5.0K viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:29:00
9.5K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:28:15 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች የቁልፍ መረከቢያ ቅፅ በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ

በ2015 በጀት ዓመት በወጣው 14ኛው ዙር የ20/80 እና 3ኛው ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኛ ነዋሪዎች የቁልፍ መረከቢያ ቅፅ በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡ እሰከ መጪው ሰኔ 20 ቀን 2015 ድረስ መውሰድ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ዘውዴ እንደገለፁት በ14ኛው ዙር የ20/80 እና 3ኛው ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኛ ነዋሪዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየቀረቡ የቁልፍ መረከቢያ ቅፅ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ዕድለኞች ቅፁን ለመረከብ ሲመጡ ከሚኖሩባቸው ወረዳዎች የተሰጠ የነዋሪነት መታወቂያ እንዲሁም ከባንክ ጋር የተዋዋሉበትን ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ በወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት እየቀረቡ መስተናገድ እንደሚችሉም አመልክተዋል፡፡

እስከ መጪው ሰኔ 20 ቀን 2015 ድረስ እየቀረቡ የቁልፍ መረከቢያ ቅፁን መውሰድ እንደሚችሉ የጠቆሙት አቶ ካሳሁን በዚህ ጊዜ ውስጥ ቅፁን መውሰድ ሳይችሉ የቀሩ ዕድለኛ ነዋሪዎች ቤቶቹ በሚገኙባቸው ክፍለ ከተሞች እየቀረቡ መውሰድ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑ ምንም ችግር አያጋጥማቸውም ብለዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በግንባር ቀርበው መዋዋል የማይችሉ ከሆነ ከሚመለከተው ህጋዊ ተቋም የተሰጠ የውክልና ደብዳቤ ይዘው በመቅረብ በተወካዮቻቸው በኩል መዋዋል እንደሚችሉ ገልፀው የብድር ውል ላልተዋዋሉ እና ካርታ ላልታተመላቸው ዕድለኛ ነዋሪዎች አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ እየተዘጋጀ በመሆኑ ተረጋግተው እንዲጠብቁም አሳስበዋል፡፡

በዘንድሮው በጀት ዓመት በ14ኛው ዙር የ20/80 እና 3ኛው ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ እንደወጣላቸው የሚታወስ ነው፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
9.8K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 19:51:10 ማስታወቂያ

ቀደም ሲል በተጠባባቂነት ተይዛችሁ የነበራችሁ በአካውንት ስህተት ምክንያት ያልተካተታችሁ እና መረጃችን ከክ/ከተማ ዘግይቶ የተላከ በሚል ቅሬታ አቅርባችሁ የነበራችሁ የማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ከዚህ በታች ተያይዞ በቀረበው ዝርዝር መሠረት የመተካካት ሥራ የተሰራ በመሆኑ በየተመደባችሁበት ማህበር ሪፖርት እንድታደርጉና የግንባታውን 70% እስከ ሰኔ 5/2015 ዓ.ም እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡

የአዲስ ከበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
9.9K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 19:35:11
ማስታወቂያ

ቀደም ሲል በ54 ማህበራት ተደራጅታችሁ እስከ ግንቦት 24/2015 ዓ.ም የግንባታውን 70% በነባር ቁጠባ ሂሳብ ደብተራችሁ እንድታስገቡ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡ 

ሆኖም በተደጋጋሚ ባቀረባችሁት የቀን ይራዘምልን ጥያቄ መሠረት ከ25/09/2015 እስከ 5/10/2015 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን የማህበራት ሰብሳቢዎች ከባንክ መረጃውን በመውሰድ የግንባታውን 70%  ያስገቡና ያላስገቡትን በመለየት እስከ 9/10/2015 ዓ.ም  ለህብረት ሥራ ማህበራት ኤጀንሲ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
10.9K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 20:29:30
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ

የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት በ54  ማህበራት ለተደረጃችሁ በሙሉ ፦

ቀደም ሲል በ07/09/2015 ዓ.ም
በወጣ ማስታወቂያ መሠረት ሰባ ከመቶውን (70%) ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት እንድታስገቡ ማሳወቃችን ይታወቃል።

ይሁንና የ54ቱ ማህበራት ተወካዮችና አባላት ባቀረቡት የማስገቢያ ጊዜው  ይራዘምልን ጥያቄ  መሰረት የማስገቢያው ግዜ ለተጨማሪ 10 የስራ ቀናት የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
7.5K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ