Get Mystery Box with random crypto!

እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞችን ወደቤታቸው ለማስገባት እየተደረገ ያ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞችን ወደቤታቸው ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ የደረሰበት ደረጃ ተጎበኘ

በነባር ግንባታ ኘሮግራም በ40/60  በሰሚት እና በ20/80  በፉሪ ሀና እንዲሁም አዲስ የተጀመሩ የመጀመሪያ ዙር የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶች እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም አጠናቆ ነዋሪውን ወደ ቤቱ ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ በቢሮው እና በኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ።

ጉብኝቱ በዋናነት ነዋሪው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፤ የተጓደሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ያለበት ደረጃ ላይ ያተኮረ ሲሆን በጉብኝቱ ማየት እንደተቻለው ቀሪ ጥቃቅን ስራዎችን ቤቶች እያጠናቀቀ መሆኑ ፤ ውሀ እና ፍሳሽ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ እና መብራትም ነዋሪውን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን መመልከት ተችሏል።

ነገር ግን በፉሪ ሀና ሳይት ተደራሽ መንገድ ለነዋሪው ከመፍጠር አኳያ ያለው እንቅስቃሴ ደካማ በመሆኑ መንገዶች ባለስልጣን መፍጠን እንዳለበት በጉብኝቱ ላይ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች አሳስበዋል።

የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን በታሰበለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ወቅቱ የክረምት መሆኑ እና የወሰን ማስከበር ችግር የነበረበት ቢሆንም በተቻለ መጠን የመጀመሪያውን ዙር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በተደረገው ጉብኝት ለመረዳት ተችሏል።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic