Get Mystery Box with random crypto!

በቅንጅት በመስራት እና ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ እጣ ወጥቶላቸው  ወደ ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎችን | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

በቅንጅት በመስራት እና ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ እጣ ወጥቶላቸው  ወደ ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎችን በቀጣይ ሶስት ሳምንታት  ማስገባት ይገባል ተባለ

በቤቶች የተመረጡ ስራዎችን ማጠናቀቅ እና የአሳታፊ ፕሮጀክት መዝጋት ስራዎች የ15 ቀናት እቅድ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን እጣ ወጥቶባቸው ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎች ለማስገባት ከተጀመረው ፍጥነት በላይ በመሄድ በቀንም በምሽትም በቅንጅት በመስራት በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ ይገባል ያሉት አቶ ሽመልስ ታምራት በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ናቸው ፡፡

ኃላፊው አክለውም ባለው አጭር ጊዜ ቀሪ ስራዎች ነዋሪውን በማሳተፍ እንዲሰሩ እና  የገባ አና ያልገባ ነዋሪም ተለየቶ እንዲቀርብ ብለዋል፡፡

በግምገማው በዋናነት ለነዋሪ በተላለፉ በ7ቱ ቅርንጫፎች ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪው እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ምቹ ለማድረግ ቀሪ የተመረጡ ስራዎች የተመሩበት ሁኔታ ፤ ለመሰረተ ልማት ተቋማት ከቤቶች በኩል ያሉ ስራዎች በማጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎች እና የመሰረተ ልማት ተቋማት በሚፈለገው ልክ እየሰሩ መሆናቸው በዝርዝር ታይቷል፡፡

በግምገማው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ፣ ም/ስራ አስኪያጆች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic