🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-12 21:37:34
ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ 400 ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም እና ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አከናወኑ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቅ/8 እና 9 ኘሮጀክት ፅ/ቤት ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የኢፍጣርና ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ከ400 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሪት ያስሚን ወሃብረቢ  በመርሀ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የፆም የፀሎት ወቅት ላይ በመሆናችን በአንድነት አብረን እናሳልፍ በሚል የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀው ወቅቱን በእዝነትና በመተሳሰብ ማሳለፍ ይኖርብናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዛሬው ፕሮግራም ሃይማኖት ሳይለይ የተካሄደ ለሙስሊም ወገኖች የኢፍጣር ለክርስቲያኖች ደግሞ ማዕድ የተጋራበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ያሉት  ደግሞ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ ሲሆኑ ፕሮግራሙን ላዘጁት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ቶማስ ደበሌ በበኩላቸው በበጎነት የምናደርገውን ስራ አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

ከአፍጥር ፕሮግራሙ በተጨማሪ በእለቱ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች ለእያንዳንዳቸው  5ሊትር ዘይት፣ 10 ኪሎ ዱቄት እና 5 ኪሎ ሩዝ  የበአል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
3.8K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:14:46
ለ400 አቅመ ደካሞች የአፍጥር ኘሮግራም ሊካሄድ ነው

ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ከቅ/8 እና 9 ኘሮጀክት ፅ/ቤት ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለ400 አቅመ ደካሞች የአፍጥር እና የአይነት ማእድ ማጋራት ለማከናወን ዝግጅቱን አጠናቋል ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም መርሀ ግብሩ ይጀመራል ።

በጎነት መልሶ ይከፍላል እና በጉልበትም በገንዘብም የተባበራችሁ የተቋሙ ሰራተኞች እና ባለድርሻዎች ምስጋና ይገባችኋል።


http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.1K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:51:30
ከጥር 1/2015 እስከ መጋቢት 26/2015 ዓ.ም ድረስ የቆየው የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት ከመጋቢት 27/2015 ጀምሮ ለ30 የስራ ቀናት ተራዘመ።
3.9K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 12:39:52
ዛሬ ከፍል ውሃ አካባቢ፣ ከጉለሌ እና ከአራዳ ክፍለከተሞች በልማት እና ከወንዝ ዳርቻ ለተነሱ የከተማችን ነዋሪዎች 200 ምትክ መኖሪያ ቤት፣ 525 ኮንዶሚኒየም ቤት፣ ለግል ይዞታ ባለቤቶች 1.1 ቢልዮን ብር ካሳና. 5.6  ሄክታር ምትክ መሬት አስረክበናል።

የወንዞቻችን ዳርቻ  አካባቢዎች በደረቅና ፍሳሽ እንዲሁም ከፋብሪካ በሚለቀቁ ቆሻሻዎች በመበከላቸው በሰው ልጅ ላይ የጤና ችግር የሚያስከትሉ፣ በዝናብ ወቅት በሰውና በንብረት ላይ አደጋ የሚያደርሱ ሲሆን ይህን በመቅረፍ የነዋሪዎቻችንን ህይወት ከአደጋ ለመታደግ በገባነው ቃል መሰረት እና ከተማዋን ንጹህ ፣ ውብና አረንጏዴ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ እና የቱሪስትት መስህብ ለማድረግ ከእንጦጦ እስከ ወዳጅነት ፓርክ 5.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ ጀምረናል።
በዚህ ልማት ሳቢያ ለተነሱ ነዋሪዎች የግል ይዞታ ለነበራቸው 1.1 ቢልዮን ብር የንብረት ካሳ ከፍለን 5.6 ሄክታር ምትክ መሬት በመረጡት አካባቢ ሰጥተናል።
200 ለሚሆኑ ነዋሪዎች ለመኖር ምቹ የሆነ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች አስረክበናል።

ኮንዶሚኒየም ቤት ለመረጡ 525 ነዋሪዎች ጥያቄያቸውን አሟልተን የቤታቸው ግንባታ እስኪጠናቀቅ ለ5 ወራት የሚሆን የቤት ኪራይ 36.6 ሚሊዮን ብር ከፍለናል።
በተግባር የነዋሪዎቻችንን ችግር ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ሁሉም በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆንባት ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
4.7K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 10:05:59
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍል ውሃ አካባቢ ለልማት እና ከወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ቤቶችን ያስተላልፋሉ::

በዚህም መሰረት:-

1. 200 ቤቶች ለልማት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ከጉለሌ ፣ አራዳ እና ልደታ ለተነሱ ነዋሪዎች ይተላለፋሉ
2. 5.6 ሄክታር መሬት ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎች የተዘጋጀ ሲሆን 1.1 ቢሊዮን ብር ካሳ ለነዚሁ ተነሺዎች ተከፍሏል
3. ኮንዶሚኒየም ቤት ተመድቦላቸው የቤቱ ግንባታ ተጠናቅቆ ቤታቸው እስኪገቡ የአምስት ወር የቤት ኪራይ በአጠቃላይ 36.6 ሚሊዮን ብር  የቤት ኪራይ ክፍያ ተፈፅሟል::

ከተማችን የምታፈናቅል ሳትሆን ሁሉንም ነዋሪዎች እኩል ተጠቃሚ የምታደርግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ የተሻለ ጤናማ የመኖሪያ አካባቢን በመፍጠር ላይ የምትገኝ ከተማ ናት::

ለነዋሪዎቻችን በቂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ያለው ምቹ የመኖሪያ አካባቢን እየገነባን የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት የቱሪስት መተላለፊያ ሳትሆን የቱሪስት መዳረሻ የሆነች ከተማ ለመገንባት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል::
4.8K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:09:40 የጋራ መኖሪያ ቤት እደለኞችን ውል የማዋዋል ሂደት አስመልክቶ በአንድ ማእከል እየተካሄደ ባለው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከከተማው የኮሙኒኬሽን ቢሮ እና ከEBC ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ዘጋቢ ፊልም 



4.4K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 18:17:54 የኘሮግራም ጥቆማ

የጋራ መኖሪያ ቤት እደለኞችን ውል የማዋዋል ሂደት አስመልክቶ በአንድ ማእከል እየተካሄደ ባለው አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተዘጋጀውን ዘጋቢ ፊልም  ዛሬ ምሽት 3:30 በEBC ይከታተሉ።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
5.1K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 15:29:42
ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅታችሁ ቤት ለመገንባት በመመዝገብ በ57 ቡድን ከተደለደላችሁት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ፡፡

ቀደም ሲል በተቋሙ ማህበራዊ ገፅ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ ቢተላለፍም እሰከአሁን ቀርባችሁ ሪፖርት ያላደረጋችሁ በመኖራችሁ ለመጨረሻ ጊዜ በ25/7/2015 - 27/7/2015 ድረስ ለ 3 ተከታታይ የሥራ ቀን ባምቢስ ከግሪክ ት/ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቢ.ቁ.601 ቀርባችሁ ሪፖርት ካላደረጋችሁ በገዛ ፍቃዳችሁ ከቡድን ድልድሉ የተሰረዛችሁ መሆኑን እና በምትካችሁ ተጠባባቂዎችን የምንተካ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
7.1K viewsedited  12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:38:54
4.6K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:38:47
4.5K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ