Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-01 13:37:48 ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በዘጠና ቀናት ዕቅድ የተገነቡ  ቤቶች ለአቅመ ደካሞች እና ለልማት ተነሺዎች አስረከቡ።

ከንቲባ አዳነች  በክፍለ ከተማው የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስተባበር በስድስት ብሎኮች የተገነቡ  ቤቶች ለአቅመ ደካሞች፥ ለውስብስብ የጤና እክል የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች፥ እና በከተማው እየተከናወነ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት ለተነሱ ነዋሪዎች ተላልፈዋል።

ዛሬ የቤት ባለቤት ከሆኑት ውስጥ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል  በነበረው ጦርነት ወላጆቻቸውን ያጡ  ህጻናት  ይገኙበታል።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማው ተለይተው በዛሬው ዕለት  የቤት ቁልፍ ለተቀበሉ ነዋሪዎች  ከንቲባ አዳነች የማዕድ ማጋራትንም አድርገዋል ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በተጠየቁ ጊዜ   በበጎነት  አቅማቸውንና ገንዘባቸውን ላበረከቱ የክፍለ ከተማው ባለሃብቶች  ምስጋና አቅርበዋል።

የከተማ አስተዳደራችን ቀዳሚ ትኩረት ያለንን ሀብት በፍትዊነት ለነዋሪዎች  ተደራሽ  ማድረግ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

የከተማችንን   የቱሪዝም ልማትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በጽኑ የምንፈልግ ሁላችን የልማት ተባባሪ መሆን ይጠበቅብናል  ሲሉም  ተናግረዋል።

ኃይላችንን አሰባስበን ከተባበርን ከተማችንን በሚፈለገው ደረጃ መለወጥ እንችላለን ያሉት ከንቲባዋ በሂደት በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የከተማችንን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቀን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብተናል ሲሉ ገልጸዋል ።
4.5K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 21:06:24
5.6K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 20:06:28
ማስታወቂያ

ለጋራ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት በሙሉ፡፡

በጋራ ህንፃ ህብረት ስራ ማህበር በመደራጀት የመኖሪያ ቤት ለመገንባት  በ57  ቡድን የተመደባችሁ የቡድን  ተወካዮች ሁሉ የቡድናችሁ አባላት ሆነው እስከዛሬ በተሰጡ ኦረንቴሽኖች ያልተገኙ እና የተገኙ ፤ እስከአሁን ምንም ሪፖርት ያላደረጉ ፤ ሰባ ከመቶውን (70%) መቆጠብ የማይችሉ እንዲሁም አድራሻ የሌላቸው (የስልክ ቁጥር) መረጃ  ይዛችሁ  ከ30/06/2015 - 01/07/2015 (ሀሙስ እና አርብ) ባምቢስ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 በስራ ሰአት በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ

እስከ አሁን ምንም ሪፖርት ባላቀረቡ እና ባልተገኙ  የቡድን አባላት ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በሚሰጣቸው ቀነ ገደብ መሰረት ካልቀረቡ  በምትካቸው  ተጠባባቂዎችን እንደምንተካ እናሳውቃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
9.2K viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 19:01:01
5.5K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 21:39:57 ማስታወቂያ
 
በማህበር በመደራጀት የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተመዝጋባችሁ እና ከ G+9 ከቡድን 1- 4 እና  የ G+13 በቡድን 1  ያላችሁ በ29/06/2015 ዓ.ም 5 ኪሎ በሚገኘው የህብረት ስራ ኤጀንሲ ቢሮ አምስተኛ ፎቅ የማህበሩ ጠቅላላ አባላት  ከታች በተጠቀሰው ሰአት መሰረት እንድትገኙ ተጠርችኋል።

G+9
ቡድን- 1 ጠዋት 2፡30
ቡድን- 2 ጠዋት 4: 00
ቡድን- 3 ጠዋት 5: 30
ቡድን- 4 ከሰአት 7:30

G+13

ቡድን - 1 ከሰአት 9: 00 

ማሳሰቢያ:- የተወከሉ ቡድኖች በእጃቸው ያለውንም የአባላት መረጃ ይዛችሁ  እንድትገኙ።

የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ
9.3K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 21:46:32
ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ እስከ ሰኔ ወር እንዲጠናቀቅ ከንቲባ አዳነች አሳሰቡ

የጋራ መኖርያ ቤቶችን ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ያለማጠናቀቅ ክፍተት መኖሩን የገመገሙት ከንቲባ አዳነች ለዚህ ክፍተት የሲሚንቶ እጥረት፣ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ልዩነት እንዲሁም የወሰን ማስከበር ችግር መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል

ሆኖም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ፣ የጋራ መኖርያ ቤቶችን መሰረታዊ ግንባታ መንግስት በአፋጣኝ በማጠናቀቅ፣ ቀሪውን ተጠቃሚው እንዲያሟላ የሚደረግ ሲሆን የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ቀሪ ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ይህንንም የሚከታተሉ ተቋማትና ኮሚቴዎች በየሳምንቱ የግንባታውን ሂደት ይከታተላሉ ብለዋል።

የተነሱት የግብዓት እጥረትና የዋጋ ልዩነቶችም አፋጣኝ እልባት አግኝተው እስከ ሰኔ ወር ባለው ግዜ ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለተጠቃሚው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
2.8K views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 11:59:44
ለጨረታ ከቀረቡ 5397 የንግድ ቤቶች ውስጥ ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

በ11 ሳይቶች በሚገኙ 5397 የንግድ ሱቆች ሽያጭ 52,614 የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል ተብሏል፡፡

ከሱቆቹ ሽያጭም ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ይገኛል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ገንዘቡም ከተማ አስተዳደሩ ለግንባታ ወጪ ያለበትን የቦንድ ብድር የሚቀንስበት ይሆናልም ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለ9 የስራ ቀናት ተጫራችች በተገኙበት ሲከፍት የቆየውን የንግድ ሱቆች ጨረታ ትላንት ማለትም በ24/06/2015 ዓ.ም ያጠናቀቀ ሲሆን ውጤቱንም በቅርቡ በጋዜጣ እና በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
3.8K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:38:56
3.1K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:38:55
3.1K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:37:54 የአድዋን ድል በልማቱ መስክም በመድገም ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለአድዋ ጦርነት ያስመዘገቡትን አኩሪ ድል የሀገሪቱን ልማት እና እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ አንድነቷ የተጠበቀ እና የበለጸገች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ይበልጥ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ ፡፡

በ127ኛው ዓመት የአድዋ ድል ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በበአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የፓል ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነት ያስመዘገቡትን ድል በልማቱ እና በስልጣኔውም ዘርፍ በመድገም ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ሀገር ለማስረከብ ይበልጥ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የአድዋ ድል የወራሪዎችን ቅስም የሰበረ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ አርበኞች በከፈሉት የደም መስዋዕትነት ያቆዩዋትን ሀገር የአሁኑ ትውልድም የሀገሪቱን አንድነት እና ኢኮኖሚ ወደ ላቀ  ደረጃ ለማድረስ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እና የትውልድ አደራውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶ በውይይት መድረኩ ላይ ባቀረቡት ሰነድ የአድዋ ድል ለኢትጵያውያን የድል ቀን ሲሆን ለሌሎች አፍሪካውያን እና ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ቀንዲል ማብራት የቸሩ መሆኑን አመልክተው ቅኝ ገዢዎችንም ማሸነፍ የሚቻል መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ አኩሪ ገድል እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

አፄ ምኒሊክ እና የጦር መሪዎቻቸው የተከተሉት በሳል የጦርነት ስልት ሀገሪቱን ለታላቅ ድል እንዳበቃት ያስታወሱት አቶ አብዲሳ ለመላው የሀገሪቱ ህዝብ ብሄር ኃይማኖትና ጾታ ሳይገድባቸው እንደ አንድ ሰው በመቆም ያስመዘገቡትን ገድል በአሁኑ ወቅት በየደረጃው እየተካሄዱ ያሉትን ታላለቅ ፕሮጀክቶች ዳር በማድረስ አድዋን ድል በልማቱም መሰክ መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች እና ሰራኘተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
3.1K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ