Get Mystery Box with random crypto!

የአድዋን ድል በልማቱ መስክም በመድገም ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ ጀግኖች | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የአድዋን ድል በልማቱ መስክም በመድገም ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለአድዋ ጦርነት ያስመዘገቡትን አኩሪ ድል የሀገሪቱን ልማት እና እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ አንድነቷ የተጠበቀ እና የበለጸገች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ይበልጥ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ ፡፡

በ127ኛው ዓመት የአድዋ ድል ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

በበአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የፓል ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነት ያስመዘገቡትን ድል በልማቱ እና በስልጣኔውም ዘርፍ በመድገም ለመጪው ትውልድ የበለጸገች ሀገር ለማስረከብ ይበልጥ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የአድዋ ድል የወራሪዎችን ቅስም የሰበረ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ አርበኞች በከፈሉት የደም መስዋዕትነት ያቆዩዋትን ሀገር የአሁኑ ትውልድም የሀገሪቱን አንድነት እና ኢኮኖሚ ወደ ላቀ  ደረጃ ለማድረስ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እና የትውልድ አደራውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶ በውይይት መድረኩ ላይ ባቀረቡት ሰነድ የአድዋ ድል ለኢትጵያውያን የድል ቀን ሲሆን ለሌሎች አፍሪካውያን እና ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ቀንዲል ማብራት የቸሩ መሆኑን አመልክተው ቅኝ ገዢዎችንም ማሸነፍ የሚቻል መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ አኩሪ ገድል እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

አፄ ምኒሊክ እና የጦር መሪዎቻቸው የተከተሉት በሳል የጦርነት ስልት ሀገሪቱን ለታላቅ ድል እንዳበቃት ያስታወሱት አቶ አብዲሳ ለመላው የሀገሪቱ ህዝብ ብሄር ኃይማኖትና ጾታ ሳይገድባቸው እንደ አንድ ሰው በመቆም ያስመዘገቡትን ገድል በአሁኑ ወቅት በየደረጃው እየተካሄዱ ያሉትን ታላለቅ ፕሮጀክቶች ዳር በማድረስ አድዋን ድል በልማቱም መሰክ መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች እና ሰራኘተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial