2023-01-07 16:39:42
ለ3ኛው ዙር የ40/60 የቤት እድለኞች በሙሉ ውል ለመዋዋል ስትመጡ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ይጠበቅባችኋል:-
እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል
ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤
በውክልና ከሆነ በውጪ ጉዳይ
ሚኒስቴር አውተንቲኬት ሆኖ የመጣ
ውክልና ማቅረብ፤
የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ
/ፓስፖርት/ ዋና እና 2 ኮፒ፤
የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና እና 2
ኮፒ፤
- ያላገባ ከሆነ
• 6 ወር ያላለፈው የምስክር ወረቀት
- ያገባ ከሆነ
• የትዳር አጋር የታደሰ መታወቂያ ዋና እና 2 ኮፒ፤
ባንክ የቁጠባ ደብተር (ፎቶ ባለው
በኩል) ዋና እና 2 ኮፒ፤
የባንክ ምዝገባ ማረጋገጫ
ከተመመዘገቡበት ባንክ የሚቀርብ ዋና
እና 1 ኮፒ፤
TIN (የግብር ከፋይነት መለያ
ቁጥር) ዋና እና 2 ኮፒ፤
ቅጽ -09 ዋና እና 1 ኮፒ (ከወረዳ
ተሞልቶ ታሽጎ የሚላክ)፤
የጠፋ ሰነድ ካለ የፖሊስ ማስረጃ ዋና
እና 1 ኮፒ፤
4x4 የሆነ ፎቶ ግራፍ 4
- ፍቺ ካለ
• በፍ/ቤት የፀደቀ ፍቺ ዋና እና 2 ኮፒ
ባለ ዕድለኛው በሞት ከተለየ
• የውርስ አጣሪ ሪፖርት ዋና እና 2 ኮፒ
• የወራሽነት ማስረጃ ዋና እና 2 ኮፒ
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ
ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊ ከላይ
የተጠቀሱትን ማሟላት የግድ ሆኖ
የታደሰ ፓስፖርት ወይም የሎ ካርድ
(ቢጫ ካርድ) የታደሰ፤
በውክልና ከሆነ የውክልና ወረቀት
በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በጀርባ
ማህተም የተረጋገጠ ፣ የተወካይ
የታደሰ መታወቂያ ይዞ መቅረብ
ያስፈልጋል፡፡
የውል መዋዋያ ቀን ከሰኞ ጥር
1/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ
ሰዓት ባሉት 60 ቀናት ባለ እድለኛው
ወይም ወኪሉ ቀርበው መዋዋል
ይጠበቅባቸዋል ፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
በመመሪያ ቁ/3/2011 አንቀጽ 1እና 2 መሰረት ባለእድለኞች ወይም ወኪላቸው ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 60 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ቤቱን እንዳልፈለጉት ተቆጥሮ ተመላሽ ይደረጋል ፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟላ የሚመጣ ማንኛውም ባለጉዳይ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ የመወያያ ቦታ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቅፅር ግቢ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ ነው፡
3.3K views13:39