🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-03-01 20:17:48
3.7K views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 07:14:19
ዜና እረፍት!

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆነው አቶ አስማማው ባዬ በድንገት ህይወቱ በማለፉ እጅግ አዝነናል።

በባልደረባችን ድንገተኛ ህልፈት ሀዘናችን ጥልቅ ነው። ለጓደኞቹ  ለስራ ባልደረቦቹ እና ለቤተሰቡም መፅናናትን እንመኛለን።

ነብስ ይማር!
4.7K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 21:28:59
5.2K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 21:28:58
5.0K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 21:28:16 ከማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ውይይት ተደረገ

ቢሮው የ20/80 እና የ40/60 ተመዝጋቢዎች ሆነው ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን በጋራ መኖሪያ ቤት ተደራጅተው ቤት ለመገንባት እንዲችሉ 4518 ሰዎችን መመዝገቡ እና በ57 ቡድን መደልደሉ ይታወቃል፡፡

ለነዚሁ ተመዝጋቢዎች ዛሬ በተዘጋጀው የመጀመሪያ የውይይት መድረክ ቢሮው የማህበር ቤቱን ተግባራዊ ለማድረግ ሲያከናውን በቆየው ዋና ዋና ጉዳዮች ፤ በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ተደራጅተው የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 5/2015 ላይ ግልጽነት የመፍጠር እንዲሁም በቀጣይ በማህበር ተደራጅተው ወደ ግንባታ ሲገቡ ማሟላት ስላለባቸው ጉዳዮች ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

ተመዝጋቢዎቹም ግልጽ ባልሆኑባቸው ጉዳዮች ላይ በተለይም ከመሬት ዝግጅት ፣ ከፋይናንስ ፣ ከዲዛይን እና ከአደረጃጀቱ ጋር ያሉ እና ሌሎችንም በርካታ ጉዳዮች አንስተው የነበረ ሲሆን ከቤቶች ልማት አስተደደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኤጀንሲ በመጡ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶበታል፡፡

የG+9 ተመዝጋቢዎችን በ2 ቡድን በመክፈል ውይይቱ የተካሄደ ሲሆን ነገ ደግሞ ለG + 13 ተመዝጋቢዎች 3ኛው ዙር ውይይት የሚቀጥል ይሆናል፡፡



http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
5.7K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 09:32:41
አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች በሙሉ
4.7K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 08:52:03
ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን  በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር በማደራጀት  የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ  በመመዝገብ የሚጠበቅባቸውን መረጃ ያሟሉ  4518 ግለሰቦች በ57 ቡድን መደልደልደላቸው የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም በቡድን ከተደለደላችሁት ውስጥ  ከዚህ በታች ስማችሁ የተጠቀሰ የማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ከባንክ ባገኘነው መረጃ መሰረት  የ20/80 እና የ40/60 ፕሮግራም ቁጠባችሁን ያቋረጣችሁ መሆኑ ስለተረጋገጠ ከተደለደላችሁበት ቡድን የምትሰረዙ መሆኑን አውቃችሁ  ሆኖም ግን ቅሬታ ካላችሁ ቅሬታችሁን ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

አድራሻችን ከደንበል ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሲሆን ለቤት ልማትና ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት 7ኛ ፎቅ  ቢሮ ቁጥር  704 እየመጣችሁ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ቅሬታ ያለው ተመዝጋቢ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታውን ካላቀረበ ከድልድሉ የሚሰረዝ መሆኑን እና በምትኩ ተጠባባቂ እንደሚተካ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ ፦

ቁጠባችሁን ያላቋረጣችሁ በቅረቡ ወደ ስራ ስለሚገባ የሚጠበቅባችሁን 70  በመቶ ለመቆጠብ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
5.3K views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 21:30:27
ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን  የ14ኛውን ዙር የ20/80 እና የ3ኛውን ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት  እድለኞችን ከጥር 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውል ማዋዋል  መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም እስከአሁን በተቀመጠላቸው  የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቅፅ 09ን የወሰዱ የቤት ባለ እድለኞች ቁጥር 23,373 ሰዎች ሲሆኑ ቅፅ 09 ከወሰዱት መካከል ከሚኖሩበት ቀበሌ የሚጠበቅባቸውን ያሟሉ እና የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03 በመውሰድ ውል የተዋዋሉ 7,855 ያህል ናቸው።

ይሁንና ውል ማዋዋል ከተጀመረ አንድ ወር ያለፈው ቢሆንም ቅፅ 09ን  በመውሰድ ከመኖሪያ ቀበሌያቸው አስፈላጊውን መረጃ በሟሟላት ወደ አንድ ማእከል መመለስ እና የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03 ወስደው መዋዋል ላይ መዘግየት ተስተውላል። 

ስለሆነም ተዋዋዮች የመዋዋያ ጊዜው እየተገባደደ ስለሆነ ከመኖሪያ ወረዳችሁ አስፈላጊውን መረጃ ፈጥናችሁ በማምጣት የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03ን እየወስዳችሁ ውል መዋዋል እንዳለባችሁ እያሳሰብን ወረዳዎችም ለባለጉዳዮቹ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለስራው መቃናት ተገቢውን ትብብር እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.3K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 09:27:40
ጥር 3/2015 ዓ.ም የተጀመረው 4ኛው ዙር የ40/60 የንግድ ቤቶች ጨረታ የካቲት 13/2015 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን ጨረታው ዛሬ መከፈት የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም  ተወዳዳሪዎች በተወዳደራችሁበት ሳይት መሰረት ከታች ባሉት ቀናት ተገኝታችሁ  መከታተል የምትችሉ መሆኑን  እንገልፃለን።

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.3K views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 09:06:30
4.0K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ