Get Mystery Box with random crypto!

ከማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ውይይት ተደረገ ቢሮው የ20/80 እና የ40/60 ተመዝጋቢዎች ሆነ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ከማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች ጋር ውይይት ተደረገ

ቢሮው የ20/80 እና የ40/60 ተመዝጋቢዎች ሆነው ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን በጋራ መኖሪያ ቤት ተደራጅተው ቤት ለመገንባት እንዲችሉ 4518 ሰዎችን መመዝገቡ እና በ57 ቡድን መደልደሉ ይታወቃል፡፡

ለነዚሁ ተመዝጋቢዎች ዛሬ በተዘጋጀው የመጀመሪያ የውይይት መድረክ ቢሮው የማህበር ቤቱን ተግባራዊ ለማድረግ ሲያከናውን በቆየው ዋና ዋና ጉዳዮች ፤ በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ተደራጅተው የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 5/2015 ላይ ግልጽነት የመፍጠር እንዲሁም በቀጣይ በማህበር ተደራጅተው ወደ ግንባታ ሲገቡ ማሟላት ስላለባቸው ጉዳዮች ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡

ተመዝጋቢዎቹም ግልጽ ባልሆኑባቸው ጉዳዮች ላይ በተለይም ከመሬት ዝግጅት ፣ ከፋይናንስ ፣ ከዲዛይን እና ከአደረጃጀቱ ጋር ያሉ እና ሌሎችንም በርካታ ጉዳዮች አንስተው የነበረ ሲሆን ከቤቶች ልማት አስተደደር ቢሮ እና ከህብረት ስራ ኤጀንሲ በመጡ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶበታል፡፡

የG+9 ተመዝጋቢዎችን በ2 ቡድን በመክፈል ውይይቱ የተካሄደ ሲሆን ነገ ደግሞ ለG + 13 ተመዝጋቢዎች 3ኛው ዙር ውይይት የሚቀጥል ይሆናል፡፡



http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial