2023-05-12 11:27:30
ከጋራ መኖሪያ ቤት እደለኞች ጋር በቅርበት በመስራት እና የተመረጡ ስራዎችን በማጠናቀቅ ነዋሪውን ወደ መኖሪያ ቤቱ የማስገባት ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞችን ቤታቸው ለማስገባት ከራሳቸው ከነዋሪዎች ጋር በርካታ ቀሪ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የመሰረተ ልማት ተቋማት ፣ የስራ ተቋራጭ እና የማህበራት እንዲሁም የነዋሪ ተወካዮች በተገኙበት ያለፈው አንድ ወር አፈጻፀም በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡
ከመጋቢት 1 ጀምሮ ላለፈው አንድ ወር በቅርንጫፍ 1 ፣ 4 እና 7 የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በተመረጡ ስራዎች በተለይም ከመሰረተ ልማት አንጻር የውሀ ፣ የፍሳሽ ፣ የመብራት ፣ የመንገድ እና የተረፈ ምርት ማንሳት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና ቀሪ ጥቃቅን ስራዎች በቀሪ ወራት ለማጠናቀቅ ከነዋሪው ጋር ከአሁንም ከምን ጊዜውም በላይ በመቀናጀት መስራት ይገባል ተብሏል፡፡
ስራዎች በተፈለገው ጊዜ ለማከናወን የዋጋ ንረት ፣ የመሰረተ ልማት አፈጻጸም መዘግየት ፣ የስርቆት ፣ የአልሙንየም ገጠማ መዘግየት ፣ የተቋራጮች አቅም ማነስ እና የወሰን ማስከበር ስራዎች እንደ ውስንነት የተነሱ ቢሆንም ያሉ ችግሮች ቢኖሩም አብሮ በመስራት ችግሩንም በጋራ መቅረፍ የገባል ተብሏል፡፡
በውይይቱም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ፅጌወይን ካሳ እና የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽምልስ ታምራትን ጨምሮ ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት ተወካዮች ፣ የስራ ተቋራጭ እና የማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የነዋሪ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
http://www.aahdab.gov.et
https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.4K viewsedited 08:27