Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.98K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-17 14:39:52
ማስታወቂያ ለመኖሪያ እና ንግድ ቤት ተጫራቾች
5.9K views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 22:29:56
ከአፍሪካ ልማት ባንክ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ከትራንስፎርማቲቭ ግባችን አንዱ የሆነው የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶቻችንን በሚደግፉበት ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
6.5K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 12:20:39
ማስታወቂያ ለመኖሪያ እና ንግድ ቤት ተጫራቾች
7.8K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-14 16:52:52
ቢሮው የቤት መረጃን ወደ አንድ  ቋት ለማስገባት በሚያዝያ ወር የተሰራውን ስራ ገመገመ

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ  ከወረዳ እስከ ማዕከል የቤት መረጃን ወደ አንድ ቋት ለማስገባት  ከአስራ አንዱ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች በሚያዝያ ወር የተከናወኑ ስራዎችን ገመግሟል።

የቢሮው የቤት ልማትና  አስራር ስርዓት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙልነህ ፈይሳ የቤት መረጃ ወደ አንድ ማዕከል መረጃ ቋት ሪፖርት ሲስተም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለህዝባችን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በሂደቱ ላይ ለሚስተዋለው መዘግየት ፈጥኖ ምላሽ መሰጠት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የቢሮው ፅ/ቤት  ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶ የቤት መረጃ  ወደ አንድ ማዕከል መረጃ ቋት ሲስተም  ሪፓርት ሲደረግ ችግር ሲከሰት ፈጥኖ የመፍትሔ ምላሽ ለመስጠት በአመራሩ መካከል ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።

ከየክፍለ ከተማ ወደ  አንድ ማዕከል ቤት መረጃ ቋት ሲስተም የቤት መረጃን ሪፖርት ለማድረግ የኢንተርኔት መሰረተ ልማት መቋረጥ ለስራው መሳካት  እንቅፋት እንደሆነ በውይይቱ ተጠቅሷል።
9.4K views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-13 08:43:46
ቢሮው በስነ ምግባርና በመልካም አስተደደር ዙሪያ የግንዛቤ  ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

የቤቶች ልማትና አስተደዳደር ቢሮ በአመራሩና በሰራተኛው መካከል  የሙስና እና ብልሹ አስራር ተጠያቂነትን ለማስፈን ይረዳው ዘንድ ለዳይርክሬቶች ፣ ለቡድን መሪዎችና ለባለሙያዎች የስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው በአቶ ፈይሳ ረጋሳ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር እና በአቶ ሀይለማርያም ለውጥና መልካም አስተዳደር  ዳይሬክተር ሲሰጥ ቆይቶል።

ስልጠናውም በተለያየ ዙር ሲሰጥ የቆየ  ሲሆን በስነ ምግባር ፅንሰ ሀሳብና መልካም አስተዳደር ፣ በህንፃ እና ንብረት አስተዳደር እና የጥቅም ግጭት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ላይ ያተኮረ ነበር።

ከችግሩ የተማረ ተቋማዊ ሪፎርም ትግበራን ለማረጋገጥ የተሰጠው ስልጠና በተግባር መታየት እንዳለበት በአመራሩና በሰራተኛ መካከል መግባባት ላይ ተደርሶ ስልጠናው ተጠናቋል።
5.6K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 16:41:30
3.8K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 16:40:31 በቅንጅት በመስራት እና ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ እጣ ወጥቶላቸው  ወደ ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎችን በቀጣይ ሶስት ሳምንታት  ማስገባት ይገባል ተባለ

በቤቶች የተመረጡ ስራዎችን ማጠናቀቅ እና የአሳታፊ ፕሮጀክት መዝጋት ስራዎች የ15 ቀናት እቅድ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን እጣ ወጥቶባቸው ቤታቸው ያልገቡ ነዋሪዎች ለማስገባት ከተጀመረው ፍጥነት በላይ በመሄድ በቀንም በምሽትም በቅንጅት በመስራት በቀጣይ ሶስት ሳምንታት ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅ ይገባል ያሉት አቶ ሽመልስ ታምራት በቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ናቸው ፡፡

ኃላፊው አክለውም ባለው አጭር ጊዜ ቀሪ ስራዎች ነዋሪውን በማሳተፍ እንዲሰሩ እና  የገባ አና ያልገባ ነዋሪም ተለየቶ እንዲቀርብ ብለዋል፡፡

በግምገማው በዋናነት ለነዋሪ በተላለፉ በ7ቱ ቅርንጫፎች ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪው እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ምቹ ለማድረግ ቀሪ የተመረጡ ስራዎች የተመሩበት ሁኔታ ፤ ለመሰረተ ልማት ተቋማት ከቤቶች በኩል ያሉ ስራዎች በማጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር የተሰሩ ስራዎች እና የመሰረተ ልማት ተቋማት በሚፈለገው ልክ እየሰሩ መሆናቸው በዝርዝር ታይቷል፡፡

በግምገማው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ፣ ም/ስራ አስኪያጆች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
4.1K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 22:16:49
እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞችን ወደቤታቸው ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ የደረሰበት ደረጃ ተጎበኘ

በነባር ግንባታ ኘሮግራም በ40/60  በሰሚት እና በ20/80  በፉሪ ሀና እንዲሁም አዲስ የተጀመሩ የመጀመሪያ ዙር የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶች እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም አጠናቆ ነዋሪውን ወደ ቤቱ ለማስገባት እየተደረገ ያለው ርብርብ በቢሮው እና በኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኘ።

ጉብኝቱ በዋናነት ነዋሪው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፤ የተጓደሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ያለበት ደረጃ ላይ ያተኮረ ሲሆን በጉብኝቱ ማየት እንደተቻለው ቀሪ ጥቃቅን ስራዎችን ቤቶች እያጠናቀቀ መሆኑ ፤ ውሀ እና ፍሳሽ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ እና መብራትም ነዋሪውን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን መመልከት ተችሏል።

ነገር ግን በፉሪ ሀና ሳይት ተደራሽ መንገድ ለነዋሪው ከመፍጠር አኳያ ያለው እንቅስቃሴ ደካማ በመሆኑ መንገዶች ባለስልጣን መፍጠን እንዳለበት በጉብኝቱ ላይ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች አሳስበዋል።

የአቃቂ ተገጣጣሚ ቤቶችን በታሰበለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ወቅቱ የክረምት መሆኑ እና የወሰን ማስከበር ችግር የነበረበት ቢሆንም በተቻለ መጠን የመጀመሪያውን ዙር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በተደረገው ጉብኝት ለመረዳት ተችሏል።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
6.2K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:44:59
5.0K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:43:32 የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ ግንባታ 81 በመቶ ደርሷል

የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ ከሚያከናውንባቸው አካባቢዎች መካከል የጋራ መኖሪያ ቤቶች የተገነቡባቸው መንደሮች ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣኑ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ መፋጠን ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው የመግቢያና መውጫ የአክሰስ መንገዶችን ከመገንባት ባለፈ፣ ለቤት ልማት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውሉ የውስጥ ለውስጥ እና  ወደ ዋና ዋና መንገዶች የሚያደርሱ መጋቢ መንገዶችን በመገንባት ለአገልግሎት ሲያበቃ ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ በከተማዋ ምስራቃዊ ክፍል የመንገድ መሰረተ-ልማት ግንባታ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል የሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር አንዱ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የመንገድ መሰረት ልማት ባልነበረበት የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም እየተገነባ የሚገኘው የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ፣ ለጋራ መኖርያ ቤቶች ነዋሪዎች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ይታመናል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ8 እስከ 15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡ አሁን ላይ 800 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የለበሰ ሲሆን፣ በቀሪው 200 ሜትር ላይ ደግሞ አስፋልት ለማልበስ የሚያስችሉ የግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የዚህ ፕሮጄክት የግንባታ ፊዚካል አፈፃፀም 81 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdaboffic
5.0K viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ