Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.58K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-11 07:54:31



የ14ኛው ዙር የ20/80 እና የ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ውል የማዋዋል ሂደት በማስመልከት በዋልታ ቴሌቭዥን የተናዳ ኘሮግራም
4.1K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 07:54:08



"ስውር ስኬት" በሚል ርእስ የጋራመኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ  ዶክመንተሪ
4.3K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 21:56:20
ማስታወቂያ

ለ14ኛው ዙር የ20/80 እና ለ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእድለኞች በሙሉ
5.4K views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 10:55:50
በበጀት አመቱ ማጠናቀቂያ የተሻለ  ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ መደረግ እንዳለበት ተገለጸ

የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑን የ9 ወር አፈጻፀም የሁለቱም ተቋማት አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በተገኙበት ተገመገመ፡፡

ወ/ሮ ፅጌወይን ካሳ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በግምገማው ላይ እንደገለጹት በዘጠኝ ወሩ ያልተከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት በመስጠት በበጀት አመቱ ማጠናቀቂያ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ መደረግ አለበት ያሉ ሲሆን ስራን በጋራ አቀናጅቶ ለመስራት የአመለካከት ለውጥ ማምጣጥ ይገባልም ብለዋል፡፡

በግምገማው ለአመታት እጣ ወቶባቸው ርክክብ ባልተካሄደባቸው ቤቶች በተመረጡ ስራዎች ላይ በማተኮር ግንባታውን ለማጠናቀቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በጥንካሬ የተነሱ ሲሆኑ በተመሳሳይም በ13ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 ቤት ማስተላለፍ እና ከንግድ ቤት ጨረታ ጋር ሰፊ ስራ መሰራቱ እንዲሁም የመንግስት ቤት መረጃ አያያዝን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ ተነስተዋል፡፡

በቀጣይም በቦንድ ብድር አመላለስ ፣ በህገወጥ የተያዙ ቤቶችን ከማስለቀቅ እና የተቋሙን ሀብት አሰባሰብ ላይ በተለይም በየሳይቱ ስራ ላይ የማይውሉ እና የተካማቹ ንብረቶች መፍትሄ ከማሰጠጥ አንጻር በርካታ ስራዎች ይጠበቃሉ ተብሏል፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ፅጌወይን ካሳ ጨምሮ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ ሰራተኞች እና አመራሮች በግምገማው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
5.1K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 11:38:01
በ54 ቡድን የተደለደሉ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀት ስራ ተሰራ

የከተማው ህብረት ስራ ማህበር ኤጀንሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በማህበር ለመገንባት በ54 ቡድን የተደለደሉትን በማህበር በማደራጀት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰራ ነው።

በ2005  ዓ.ም  በ40/60  እና በ20/80  የቤቶች ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን  ለመገንባት ሲቆጥቡ የነበሩ እና አሁን ግን በፍላጎታቸው በህብረት ስራ ማህበራት ለመደራጀት  ከ70 በመቶ በላይ  ለመቆጠብ  ዝግጁ የሆኑ ማህበራትን  ወደ ስራ  ለማስገባት  የማደራጀት  ህጋዊ እውቅና የመስጠት ስራ ተሰርቷል።

በቀጣይም ሰላሳ በመቶ ብድር ተመቻችቶ 70 ከመቶውን በማህበሩ የዝግ አካውንት ማስገባታቸው ሲረጋገጥ ግንባታው ለሚካሄድባቸው ሳይቶች እጣ የማውጣት እና የማስረከብ እንዲሁም የማስጀመር ስራ የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።


http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial70
7.0K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:24:19
1289 ያህሉ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቅፅ መውሰዳቸው ተገለፀ

ኮርፖሬሽኑ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች ውል እያዋዋለ ሲሆን ውል ከተጀመረ ጀምሮ እስከ 20/08/2015 ዓ.ም ድረስ   በወጣላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ቀርበው የመክፈያ ቅፅ የወሰዱ ተጫራቾች 1289 መሆናቸውን የንግድ ቤት ውል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ደረጀ ገልፀዋል።

በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ክፍያ ከፍለው ከኮርፖሬሽኑ ጋር የሽያጭ ውል የፈፀሙ ተጫራቾች ደግሞ 215 መሆናቸውንም አስተባባሪው ያሳወቁ ሲሆን የንግድ ቤት አሸናፊዎቹን ውል የማዋዋል ሂደትም እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficia
3.4K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:43:42
4.5K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:43:07 ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 20/80  እና 40/60 ነባር ሳይቶችን እና የየካ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም  20/80 ነባር ሳይቶች ለነዋሪዎች ተላልፈው የተወሰኑ ነዋሪዎች የገቡ ሲሆን አንዳንድ መጠናቀቅ ያለባቸው የተንጠባጠቡ ስራዎች ማለትም ሊፍት ገጠማ ፤ የሮቶ ከመስመር ጋር ያለማገናኘት እና ዋተር ፖምፕ አለመገጠም ፤ አንዳንድ ደረጃዎች የብረት ስራ  አለመጠናቀቅ ሲሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ አሳስቧል።

ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር  እየተሰሩ ያሉ  የጋራ መኖሪያ  ነባር ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ  ያሉ ችግሮችን  ተቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሳይቱ የታዩትን ችግሮች በመለየት አመራሩ  ተግቶና ጠንክሮ በመስራት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ተጠናቀው ለነዋሪው መረከብ እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሌላው የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤትን ጉብኝት ሲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው በኮንዶሚኒየም ፣በቀበሌና ንግድ ቤቶች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች አንስቷል። የጽ/ቤት ኃላፊውና የሚመለከታቸው አካላቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

በክ/ከተማው ስር የሚገኙ 17,474 ቤቶች ወደ ሲስተም ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች የሚተላለፉበትን አሰራር የፈተሸ ሲሆን  በልዩ ሁኔታ ከሚሰጣቸው ውጭ የተሻለ አሰራር ተከትሎ እንደሚሰራ ከተቋሙ ዳይሬክተር  እና ከፋይሎች መረዳት ተችሏል ።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ወ/ሮ ኒኢመታላህ ከበደ   የቤቶች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን እና በ13ተኛው ዙር የወጡ ቤቶች ተለይተው መያዛቸው እንደ ጠንካራ ጎን አንስተው ፤ ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ እንደሚገባና የነዋሪው ቅሬታ በአግባቡ መፈታት እንዳለበት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ባህላችንም መሻሻል እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.4K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:24:51
2.4K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:24:26 በቀሪ ወራት በበጀት ዓመቱ  የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ

በቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ለ2015 በጀት ዓመት ቀሪ ወራት የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ከምንግዜውም በላይ  መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በአሥራ አንዱ ክፍለ ከተሞች የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤቶች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ያተኮረ ውይይትም ተካሂዷል፡፡

የአዲሰ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የቤት ልማትና አስተዳደር ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አረጋሽ ቸኮል በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር በቤቶች ልማትና አሠራር ሥርዓት ዘርፍ ለዘንድሮው በጀት ዓመት በዕቅድ የተቀመጡትን ተግባራት በስኬት ለማጠናቀቅ እና በሥራ ሂደት ውስጥ የሚከሰቱትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ማስቀመጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንግዜውም በላይ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

የቢሮው የቤት ጥናትና ስትራቴጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ተዋቡ ቀስቅስ ባቀረቡት የዘጠኘ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ የቤቶችን መረጃ አያያዝ ከማሳደግ አንፃር የተከናወኑ ተግባራን እንዲሁም የመንግስት የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ውል ዕድሳትን በተመለከተ የተገኘውን አበረታች ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ፍትሀዊ የቤት ማስተላለፍን በተመለከተ በመመሪያው መሠረት ለሴቶች 30 በመቶ እንዲሁም 20 በመቶ ለመንግስት ሰራተኞችን እና 5 በመቶ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ  የቢሮው እና የየክፍለ ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.5K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ