🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-21 09:06:28
3.8K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 09:05:45 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የቢሮውን የ2015  በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።

ክብርት ያስሚን ወሀብረቢ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ የተቋሙን የመጀመሪያ ስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለከተማ ልማት ፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።

ኃላፊዋም በሪፖርታቸው የተቋሙን ቁልፍ ግቦች አላማዎች እና ተግባራት ለማሳካት የተከናወኑትን ፤ ከነባር እና ከአዳዲስ ግንባታዎች እንዲሁም ከመሰረተ  ልማት አቅርቦት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ፤ ከመልካም አስተዳደር እና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ  ከማእከል እስከ ወረዳ ተጠያቂ ለማድረግ የተወሰዱ እርምጃዎችን እንዲሁም ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል፡፡

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በግማሽ አመቱ የታዩ በጠንካራ ጎኖችን አድንቀው መሻሻል አለባቸው ባሉት ላይም ውይይት አድርገው የማስተካከያ ሀሳቦችን አስቀምጠዋል።


http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.0K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 20:31:33
የካቲት 6 ይጠናቀቃል የተባለው 4ኛው ዙር የ40/60 የንግድ ቤቶች ጨረታ እስከ የካቲት 13/2015ዓ.ም ድረስ መራዘሙ ተገለፀ።
1.8K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 21:45:21 ለማህበር ቤት ግንባታ በተጓደሉት ምትክ የተተኩ እና የተጠባባቂዎች ስም ዝርዝር ተለቀቀ።

በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት ተመዝግበው በነበሩ ነገር ግን በእጣ እና  በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ  ተመዝጋቢዎችን  የማሟላት እና ተጠባባቂዎችን የመለየት ሥራ በቅርቡ መሰራቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በሁለቱም ዲዛይኖች ማለትም በG+9 እና በG+13 በተጓደሉ ምትክ የተተኩ እንዲሁም ወደፊትም በተለያዩ ምክንያቶች የሚለቁ ካሉ በሚል የተጠባባቂዎችን ስም ዝርዝር ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም አድርሻ መመልከት የሚችሉ መሆኑን የአዲስ አበባ  ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።
2.8K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 15:38:03
እጣ የወጣላቸውን ባለእድለኞች ውል በመዋዋል ሂደቱ ካለምንም ችግር እየተስተናገዱ መሆኑን  ገለጹ፡፡

በ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የወጣላቸውን ነዋሪዎች  ስላለው መስተንግዶ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት ያለምንም ችግር እና እንግልት በሚገባ መስተናገዳቸውን እና ሰራተኞቹም ያለውን የሰው ብዛት እና የስራ ጫና ተቋቋመው በአግባቡ እና በቅልጥፍና እያስተናገዱን ነው ሲሉ ውል ሲዋዋሉ ያገኘናቸው ወ/ሮ ኑራ ኤሊያስ ፤ አቶ ሲሳይ አገዘ ፣ ሻምበል አማረ አደላ እና ሌሎችም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸውልናል፡፡

የአንዳንድ ተገልጋዮች በፕሮግራማቸው መሰረት አለመገኘት ፤ የተጣራ መረጃ ይዞ አለመምጣት እንዲሁም የጋብቻ ሰርተፊኬት እና መታወቂያ ላይ የስም ስህተቶች መኖር ውል በመዋዋል ሂደቱ የተስተዋሉ ክፍተቶች ናቸው ያሉት ደግሞ አቶ ካሳሁን ዘውዱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ተዋዋዮች የተጓደሉ መረጃዎችን አማልተው እንዲያመጡ እና ራሳቸውን ከውጭ ባሉ ህገ ወጥ ደለላዎች መጠበቅ እንደሚገባቸውም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

ጥር1/2015ዓ.ም የተጀመረው እና በቀን ከ1500 በላይ ባለጉዳዮችን እያስተናገደ የሚገኘው የውል ማዋዋያ አንድ ማእከል ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰአት ድረስ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
3.0K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 21:41:22
ቢሮው በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚጠባበቁ ተመዝጋቢዎችን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ  በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ኘሮግራም የተመዘገቡ ሆነው የጋራ መኖሪያ ቤት በማህበር ተደራጅተው ለመገንባት ፍላጎት እና አቅም ላላቸው  እና ትግበራውን የሚጠባበቁ ማህበራትን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በተደረገው የOnline ምዝገባ በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት የሚያስችለውን መሥፈርት በማሟላት በ57 ቡድን መደልደሉ የሚታወስ ሲሆን በ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 እጣ የደረሳቸውን እና በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ  ተመዝጋቢዎችን  የማሟላት እና ተጠባባቂዎችን የመለየት ሥራ ዛሬ ተሰርቷል።

በቅርቡም የተደለደሉትን ተመዝጋቢዎች ከህብረት ስራ ኤጀንሲ ጋር በመሆን በማህበር የማደራጀት እና ወደ ስራ የማስገባቱ ስራ የሚቀጥል ይሆናል።

በእለቱ የቢሮው የቤት ልማትና የአሰራር ስርዓት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ የማሟያ እና የተጠባባቂዎች ልየታ ሂደቱን የመሩ ሲሆን  የዘርፉ አመራሮች ፤ የክፍለ ከተማ የቤቶች ቡድን አስተባባሪዎች እና ተመዝጋቢዎች  በተገኙበት ማከናወን ተችሏል።

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.9K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 22:03:25
ከከተማ አስተዳደሩ በተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ የ6 ወር አፈፃፀም ተገመገመ።

ግምገማው ትኩረት ያደረገው የተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ፤ በመልካም አስተዳደር የተለዩ ችግሮች አፈታት፤ ከግንባታ አፈፃፀም እና ከጋራ መኖሪያ ቤት ማስተላለፍ ጋር የተሰሩ ስራዎች፤ ከመንግስት እና ከጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም ህገወጥ ቤት አያያዝ ጋር ተያይዞ የተወሰደ እርምጃ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች  ላይ ነው።

በግምገማው ክብርት ያስሚን ወሀብረቢን ጨምሮ የቢሮው እና የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና ከከተማ አስተዳደሩ የመጡ የሱፐርቪዥን አባላት ተገኝተዋል።

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.1K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 16:28:25
2.8K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 16:28:25
2.8K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 16:23:46 የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት ተካሄደ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት አካሄዱ፡፡

"በሚተካ ደማችን የማይተካውን የሰው ህይወት እናድን" በሚል መርህ በተካሄደው ሥነ ሰርዓት ላይ የቢሮውና የኮርፖሬሽኑ እንዲሁም የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በየሦስት ወሩ ደም ለመለገስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በዘንድሮው የ2015 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል ፡፡ 

ደም ከለገሱ ሠራተችና የሥራ ኃላፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ደም በመለገስ የሰው ህይወትን ለማዳን እየተደረገ ባለው ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ ለወገኖቻቸው ያላቸውን አጋርነት በተግባር ለመግለፅ ደም ለመለገስ መወሰናቸውን ገልፀው ሌሎችም የእነርሱን አርአያነት በመከተል ደማቸውን በመለገስ ህይወት ለማዳን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.8K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ