Get Mystery Box with random crypto!

እጣ የወጣላቸውን ባለእድለኞች ውል በመዋዋል ሂደቱ ካለምንም ችግር እየተስተናገዱ መሆኑን  ገለጹ፡፡ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

እጣ የወጣላቸውን ባለእድለኞች ውል በመዋዋል ሂደቱ ካለምንም ችግር እየተስተናገዱ መሆኑን  ገለጹ፡፡

በ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የወጣላቸውን ነዋሪዎች  ስላለው መስተንግዶ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት ያለምንም ችግር እና እንግልት በሚገባ መስተናገዳቸውን እና ሰራተኞቹም ያለውን የሰው ብዛት እና የስራ ጫና ተቋቋመው በአግባቡ እና በቅልጥፍና እያስተናገዱን ነው ሲሉ ውል ሲዋዋሉ ያገኘናቸው ወ/ሮ ኑራ ኤሊያስ ፤ አቶ ሲሳይ አገዘ ፣ ሻምበል አማረ አደላ እና ሌሎችም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸውልናል፡፡

የአንዳንድ ተገልጋዮች በፕሮግራማቸው መሰረት አለመገኘት ፤ የተጣራ መረጃ ይዞ አለመምጣት እንዲሁም የጋብቻ ሰርተፊኬት እና መታወቂያ ላይ የስም ስህተቶች መኖር ውል በመዋዋል ሂደቱ የተስተዋሉ ክፍተቶች ናቸው ያሉት ደግሞ አቶ ካሳሁን ዘውዱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ተዋዋዮች የተጓደሉ መረጃዎችን አማልተው እንዲያመጡ እና ራሳቸውን ከውጭ ባሉ ህገ ወጥ ደለላዎች መጠበቅ እንደሚገባቸውም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

ጥር1/2015ዓ.ም የተጀመረው እና በቀን ከ1500 በላይ ባለጉዳዮችን እያስተናገደ የሚገኘው የውል ማዋዋያ አንድ ማእከል ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰአት ድረስ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial