Get Mystery Box with random crypto!

ቢሮው በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚጠባበቁ ተመዝጋቢዎችን ወደ ሥራ ሊያስገ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ቢሮው በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚጠባበቁ ተመዝጋቢዎችን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ  በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ኘሮግራም የተመዘገቡ ሆነው የጋራ መኖሪያ ቤት በማህበር ተደራጅተው ለመገንባት ፍላጎት እና አቅም ላላቸው  እና ትግበራውን የሚጠባበቁ ማህበራትን ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በተደረገው የOnline ምዝገባ በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት የሚያስችለውን መሥፈርት በማሟላት በ57 ቡድን መደልደሉ የሚታወስ ሲሆን በ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 እጣ የደረሳቸውን እና በተለያዩ ምክንያቶች የተጓደሉ  ተመዝጋቢዎችን  የማሟላት እና ተጠባባቂዎችን የመለየት ሥራ ዛሬ ተሰርቷል።

በቅርቡም የተደለደሉትን ተመዝጋቢዎች ከህብረት ስራ ኤጀንሲ ጋር በመሆን በማህበር የማደራጀት እና ወደ ስራ የማስገባቱ ስራ የሚቀጥል ይሆናል።

በእለቱ የቢሮው የቤት ልማትና የአሰራር ስርዓት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ የማሟያ እና የተጠባባቂዎች ልየታ ሂደቱን የመሩ ሲሆን  የዘርፉ አመራሮች ፤ የክፍለ ከተማ የቤቶች ቡድን አስተባባሪዎች እና ተመዝጋቢዎች  በተገኙበት ማከናወን ተችሏል።

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial