Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የቢሮውን የ2015  በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።

ክብርት ያስሚን ወሀብረቢ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ የተቋሙን የመጀመሪያ ስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለከተማ ልማት ፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።

ኃላፊዋም በሪፖርታቸው የተቋሙን ቁልፍ ግቦች አላማዎች እና ተግባራት ለማሳካት የተከናወኑትን ፤ ከነባር እና ከአዳዲስ ግንባታዎች እንዲሁም ከመሰረተ  ልማት አቅርቦት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ፤ ከመልካም አስተዳደር እና ከብልሹ አሰራር ጋር ተያይዞ  ከማእከል እስከ ወረዳ ተጠያቂ ለማድረግ የተወሰዱ እርምጃዎችን እንዲሁም ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች ለቋሚ ኮሚቴው አቅርበዋል፡፡

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በግማሽ አመቱ የታዩ በጠንካራ ጎኖችን አድንቀው መሻሻል አለባቸው ባሉት ላይም ውይይት አድርገው የማስተካከያ ሀሳቦችን አስቀምጠዋል።


http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial