🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-28 13:00:03
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የሚተላለፉ ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች ይጠቀሙ !
4.7K viewsedited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 10:06:31
6.4K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 10:06:09 ''መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህዝብ እርካታን እናረጋግጥ'' በሚል መሪ ቃል  ስልጠና ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከከንቲባ ፅ/ቤት የቅሬታ እና አቤቱታ አፈታት ዘርፍ ጋር በመተባበር በመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታት ዙሪያ በቤቶች ተቋማት ለሚገኙ አመራሮች ስልጠና ሰቷል።

ኢ/ር መኮንን ሚጀና የአማራጭ ቤት ፋይናንስና አቅርቦት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ  በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው የስኬት ማነቆ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታት ስርዓት የሚዘረጋበትን ዕውቀት ሰልጣኙ በሚገባ በመከታተል በቀጣይ ተግባራዊ በማድረግ መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተቋሙ ከግንባታ መዝግየት እንዲሁም ቤት ማስተላለፍ እና ማስተዳደር  ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የተለዩ  የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ የገልፁት ኃላፊው  በተለዩ ችግሮች ዙሪያ የጠለቀ ውይይት በማድረግ መፍትሔ አስቀምጦ መሄድእና ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናው  የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፅንሰ ሃሳብና ልየታ ፤  የመልካም አስተዳደር ችግር ከሌብነትና ብልሹ  አሰራር ችግሮች ጋር ያለው ልዩነትና አንድነት እንዲሁም በአጠቃላይ በመልካም አስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ግንዛቤ በመፍጠር ወጥ የሆነ  የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንዲያስችል ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት  የከንቲባ ፅ/ቤት የመልካም አስተዳደር እና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ቤካ ናቸው።

በስልጠናው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች  ምክትል ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የክፈለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ኃሊፊዎች ተሳትፈዋል።

https://www.facebook.com/aahdabofficial
5.8K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 17:54:01
2.0K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 17:53:33 ውል ማዋዋል ከተጀመረ በ5 ቀናት ውስጥ 14,005 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእደለኞች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በ20/80 14ኛ ዙር እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ ጥር 1/2015 ዓ.ም. በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም ማዋዋል ከተጀመረ  ጀምሮ እስከ ጥር 5/2015 ዓም ድረስ 14,005 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09 ኝን መውሰድ ችለዋል ተብሏል። 

የመኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ካሳሁን ዘውዴ እንደገለፁት እስካሁን ቅፅ 09 ወስደው በመኖሪያ ቀበሌያቸው አስፈላጊውን መረጃ አስሞልተው የመጡ እና ቅፅ 03 የባንክ ክፍያ የመፈፅሙበትን ሰነድ የወሰዱ ተዋዋዬች ብዛት 699 ሰዎች ይሆናሉ ብለዋል።

ከነዚህ መካከል ደግሞ የባንክ ክፍያቸውን አጠናቀው ውል የፈፀሙት 66 ሰዎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ያሳወቁ ሲሆን በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኛ የሆኑ ሳይዘናጉ ወደ አንድ ማእከል በመምጣት ቅፅ 09 ኝን በመውሰድ ከሚኖሩበት ቀበሌ አስሞልተው ሊመጡ እንደሚገባና በወጣው ውል የማወያያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ሊዋዋሉ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
2.0K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:52:08 በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ህንጻ ኅ/ስ/ማህ/ ለመደራጀት ቀደም ሲል በኦን ላይን የተመዘገቡ እና የሚፈለግባቸውን መረጃ አሟልተው በ57 ቡድን የተደለደሉ ተመዝጋቢዎች ዝርዝር:-
4.1K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:45:28
3.4K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 20:45:23 ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ህንጻ ኅ/ስ/ማህ/ ለመደራጀት ቀደም ሲል በኦን ላይን ለተመዘገባችሁ በሙሉ

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ2005 ዓ.ም. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎችን በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2013 መሰረት በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህ/ሥራ ማህበር በፈቃደኝነት አደራጅቶ የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በኦን ላይን መመዝገባችን ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት ቢሮው አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲስራ ቆይቶ በኦን ላይን የተመዝገቡትን በየሚኖሩበት ወረዳ እና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና እተዳደር ቢሮ አስፈላጊውን ጥሪ በማድረግ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በአካል ቀርበው የሚፈለግባቸውን መረጃ ያሟሉትን ተመዝጋቢዎች በ57 ቡድን በመደልደል በማህበራዊ ሚዲያ (A.A. HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU) በሚለው የፌስቡክና የቴሌግራም አድራሻችን የለቀቅን መሆኑን እየገለጽን፣

1. አብሮ የመደራጀት ፍላጎት ያላቸውን እድል ለመስጠት ሲባል፡-

እርስ በርስ የቡድን መቀያየር የሚፈቀደው በተመሣሣይ የህንፃ ከፍታ እና የቤት አይነት ብቻ ይሆናል።

ቅይይሩ የሚፈጸመው በሁለቱ ተስማሚ ተመዝጋቢዎች በአካል ቀርበው ወይም ህጋዊ ውክልና ባላቸው ሠዎች ብቻ ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ተስማሚዎች ያቀረብነውን ቅፅ ሞልተው የታደሠ መታወቂያ ኮፒ ይዘው ከ08/05/15 እስከ 22/5/15 ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ ከደንበል ወደ ባንቢስ በሚወስደው መንገድ ግሪክ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤት ማህበራት አደረጃጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት 6ኛ ፎቅ  ቢሮ ቁጥር 601 እየቀረቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

2. የተጓደሉ የየቡድን አባላትንና ተጠባባቂዎችን ምዝገባ በተመለከተ፡-
 
ከዚህ በፊት በጋራ ህንጻ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት በኦንላይን ተመዝግባችሁ ነገር ግን ከወረዳ አስፈላጊውን መረጃ ሣታሟሉ የቀራችሁ አሁን ለመደራጀት ፍላጎቱ ያላችሁ የሚጠበቅባችሁን መረጃ ከወረዳ ቤቶች አስ/ጽ/ቤት ቀርባችሁ በማሟላት ከ08/05/15 እስከ 15/5/15 ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ በመቅረብ እስፈላጊውን እንድታሟሉ፣

ምዝገባው ሲጠናቀቅም የተጓደሉ የየቡድን አባላትንና ተጠባባቂዎችን በእጣ የምንለይ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

1. ከዚህ በኋለ የሚኖሩ ስራዎች የእርስ በርስ የቡድን አባላት እንዲተዋወቁ ለማድረግ እና የማደራጀቱ ሥራ በህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ በኩል ስለቀጣዩ የማደራጀት መርሃ ግብር የሚገለፅ ይሆናል።

2. በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ተመዝግባችሁ በመረጃ ቋት ስማችሁ የሚገኝና በተከፈተላችሁ የባንክ ሂሳብ ገንዘብ በመቆጠብ ላይ ያላችሁ ቤት ፈላጊዎች ከዚህ በፊት በኦንላይን ሣትመዘገቡ የቀራችሁ ነገር ግን በጋራ ህንፃ የቤት ማህበራት ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት የምትፈልጉ በቅርቡ ምዝገባ ስለምናደርግ ማስታወቂያውን እንድትከታተሉ እናሣውቃለን፡፡
3.8K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 10:29:08
የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በ20/80 14ኛ ዙር  እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ  ከጥር  1/2015 ዓ.ም. መጀመሩ የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም ውል ከጀመረበት ቀን ጀምሮ 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን በሁለቱም የቤት ልማት ኘሮግራሞች መውሰድ ችለዋል ።

ተቋሙም ባለ እድለኞች እንዳይጉላሉ በቂ ቦታ እና የሰው ሃይል መድቦ በማስተናገድ ላይ  የሚገኝ ሲሆን ውሉ ከተጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 60 የስራ ቀናት የሚቆይ ይሆናል ።
4.0K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 15:52:44
ማስታወቂያ የ40/60 ሱቅ መጫረት ለምትፈልጉ በሙሉ:-

የ40/60 4ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች የንግድ ቤት ጨረታ  ከነገ ጥር 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ  የሚጀምር በመሆኑ መጫረት የምትፈልጉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ እና ጊዜ መታችሁ  የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
2.0K viewsedited  12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ