Get Mystery Box with random crypto!

ውል ማዋዋል ከተጀመረ በ5 ቀናት ውስጥ 14,005 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእደለኞች ተመዝግበው ቅፅ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ውል ማዋዋል ከተጀመረ በ5 ቀናት ውስጥ 14,005 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለእደለኞች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን በ20/80 14ኛ ዙር እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ ጥር 1/2015 ዓ.ም. በይፋ መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም ማዋዋል ከተጀመረ  ጀምሮ እስከ ጥር 5/2015 ዓም ድረስ 14,005 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09 ኝን መውሰድ ችለዋል ተብሏል። 

የመኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ካሳሁን ዘውዴ እንደገለፁት እስካሁን ቅፅ 09 ወስደው በመኖሪያ ቀበሌያቸው አስፈላጊውን መረጃ አስሞልተው የመጡ እና ቅፅ 03 የባንክ ክፍያ የመፈፅሙበትን ሰነድ የወሰዱ ተዋዋዬች ብዛት 699 ሰዎች ይሆናሉ ብለዋል።

ከነዚህ መካከል ደግሞ የባንክ ክፍያቸውን አጠናቀው ውል የፈፀሙት 66 ሰዎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ያሳወቁ ሲሆን በሁለቱም የጋራ መኖሪያ ቤቶች እድለኛ የሆኑ ሳይዘናጉ ወደ አንድ ማእከል በመምጣት ቅፅ 09 ኝን በመውሰድ ከሚኖሩበት ቀበሌ አስሞልተው ሊመጡ እንደሚገባና በወጣው ውል የማወያያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀርበው ሊዋዋሉ እንደሚገባም አሳስበዋል ።