🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-07-12 15:50:42 የአቃቂ ቃሊቲ የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ሂደት ጉብኝት ተካሄደ።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች በአቃቂ ቃሊቲ በመገንባት ላይ የሚገኙ ተገጣጣሚ ቤቶችን ግንባታ አፈፃፀም ጎበኙ።

በጉብኝቱ በይገባኛል የባለቤትነት ጥያቄ ምክንያት በህግ ታግዶ የነበረው የግንባታ ሳይቱ እልባት ተሰጥቶት ግንባታው መቀጠሉን አመራሮቹ አብራርተዋል ።

በጉብኝቱ ከኢኮስኮ ሳይት ኘሮጀክት አስተባባሪዎች ጋር በግንባታ አፈፃፀም ባጋጠሙ እና መፈታት በሚገባቸው ችግሮች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አርገዋል።

ግንባታው ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም አጠቃላይ አፈፃፃሙ 2.54 በመቶ መድረሱን እና የ10 ብሎኮች መሰረት መውጣቱን እንዲሁም በቀጣይ ሌሎች ተጨማሪ ግንባታዎች እንደሚጀመሩ የሳይቱ አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

በተጨማሪም የግንባታ ተገጣጣሚ ግብአቶች ማምረቻ ማእከል እና የምርት ሂደቱን ተጎብኝተዋል።
1.0K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:51:26
2.0K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:51:21 ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ይመለከታል::

በከተማችን አዲስ አበባ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንዱ የቤት አቅርቦት እጥረት ሲሆን ይህንኑ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ሂደት አካል የሆነው የነባሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ወስብስብ ችግር ለይቶ በመፍታት ተመዝጋቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና የቤት እጥረት ጫና ለመቀነስ የተደረገው ሰፊ ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡
በዚህ ሂደት በግንባታ ላይ የነበሩ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 25,491 ያህሉ በቅርቡ ለባለ እድለኞች የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የቤት ማሰስተላለፍ ስራ እንደ ከዚህ በፊቱ በቆጣቢወች መካከል አድሎና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ግልፅነት በሚያሰፍን አግባብ ለማስተላለፍ ሲባል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ሂደቱን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ የተደረገው ተነሳሽነትና ጥረት እንዲሁም የባልሙያዎችን ሙያዊ ነፃነት አክብረን አስፈላጊውን ሂደት ተከትለን ተዓማኒነቱን እንዲያረጋግጡልን አድርገን ነበር:: በዚህ ሂደት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲስ ሶፍትዌር እንዲበለፅግ እና ስለሶፍትዌሩ ታአማኒነት የኢኖቬንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር እንዲያረጋግጥልንም ተደርጓል::
በቀጣይም ከሁለት ጊዜ በላይ ታዛቢወች እና ባለሙያወች ፊት ቀርቦ እንዲያረጋግጡልን ተደርጎ ማረጋገጫ ሰጥተዋል::
ይህ ሁሉ ሂደት ከእለት ጉርሱ የቆጠበዉን እና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠባበቀውን ሕዝብ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ቀና ሃሳብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል::
ይሁን እንጂ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል::
በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል::

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ሐምሌ 4/2014 ዓ/ም
2.5K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:51:09
2.1K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:51:04 የ20/80 ባለሶስት መኝታ የጋራ መኖርያ ቤት እጣ አለመውጣትን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራርያ!

እንደሚታወቀው የከተማ አስተዳደሩ ባሳለፍነው ሳምንት የ20/80 የ14ኛ ዙር የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በ20/80 ፕሮግራም የባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች በእጣው አለመካተትን መነሻ በማድረግ ከአንዳንድ ግለሰቦች የደረሰንን የግልፅነት ጥያቄ አስመልክቶ የሚከተለውን ማብራርያ ለማቅረብ እንወዳለን፡-

በዚህ ዙር ለ20/80 የቤት ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ እጣ የወጣባቸውና የተስተናገዱት የ1997 ተመዛጋቢዎች ብቻ ናቸው፡፡
የ2005 የ20/80 ተመዝጋቢዎች ግን ከስቱዲዮ ጀምሮ ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ በሙሉ በእጣ ውስጥ አልተካተቱም፡፡

የ40/60 የቤት ፕሮግራም ግን በ2005 ዓ.ም ብቁ የሆኑ ሙሉ ለሙሉ በእጣ ተካተው በዚህ ዙር የእጣ አወጣጥ በ40/60 ባለአንድ ባለሁለትና ባለሶስት መኝታ ቤቶች እጣ እንደወጣላቸው ልብ ሊባል ይገባል፡፡

ስለሆነም በዚህ ዙር ያልተስተናገዱት 1997 ዓ.ም የተመዘገቡ ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸው፡፡

ይህም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት በ12ኛ ዙር እጣ የ1997 ባለሶስት መኝታ ተመዝጋቢዎችን ሙሉ ለሙሉ አስተናግደናል በሚል መነሻ መረጃቸው የተሟላ የሆኑት ተስተናግደው የባለሶስት መኝታ ፕሮግራም ተዘግቶ ነበር፡፡

ከዚህ በኋላ በ1997 ተመዝጋቢዎች ውስጥ በ20/80 ባለሶስት መኝታ እጣ ሊወጣለት የሚችል ተመዝጋቢ የለም በሚል ቤቶቹን በሚያስተዳድረው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።
በዚህም ምክንያት በዚህኛው(በ14ኛ) ዙር እጣ ማስተናገድ አልተቻለም::
ነገር ግን ከተዘጋ በኋላ ከባንክ የተገኘው መረጃ ጥቂቶች ቢሆኑም ቁጠባ በመቀጠላቸው ብቁ የሆኑ ጥቂቶች ተገኝተዋል::
በአሁን ሰአትም ምዝገባው ከባንክ በሚወሰድበት (በሚከለስበት ወቅት) በተገኘው መረጃ ከ1997 ተመዝጋቢዎች መሃከል ጥቂት ሰዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉና ብቁ የሆኑ የ20/80 ተመዝጋቢዎችን ማግኘት ተችሏል፡፡

ስለሆነም አስተዳደሩ እነኚህን ተመዝጋቢዎች ምንም እንኳን ፕሮግራሙ በይፋ የተዘጋ ቢሆንም ከባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት በአግባቡ እስከቆጠቡ ድረስ ማስተናገድ እንደሚገባ ያምናል፡፡

ነገር ግን ከመረጃ ውስንነትና በሲስተሙ ላይ የሚያስከትለውን ተጨማሪ የመረጃ መመሰቃቀል ለመከላከል ሲባል ወደ በኋላ ተመልሶ ሲስተሙን ለቀሩት ጥቂት ቆጣቢዎች ብቻ መክፈት አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት እነዚህን ተመዝጋቢዎች ለብቻቸው በልዩ ሁኔታ ልናስተናግድ ይገባል የሚል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

ስለሆነም የ1997 ተመዝጋቢ ሆናችሁ ባለሶስት መኝታ ቤቶች በአግባቡ የቆጠባችሁ አስተዳደሩ በሚያወጣው ፕሮግራም በልዩ ሁኔታ የምትስተናገዱ መሆኑን እያሳወቅን ፤ ህብረተሰቡ ይህንን አስመልክቶ አንዳንድ የሚናፈሱ የተሳሳቱ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን!!
በተጨማሪም ዘርፉን የሚመሩ አመራሮች ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ ሚድያዎች የሚያደርሱ መሆኑንም እናሳውቃለን!!
2.6K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:41:56
1.8K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:15:15
2.5K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:15:08 ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲገነቡ ቆይተው ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም አያት 2፤ ቦሌ በሻሌ፤ ቡልቡላ ሎት 2 ሲሆኑ በ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም ደግሞ በረከት፤ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤ ወታደር፤የካ ጣፎ፤ ጀሞ ጋራ፤ ጎሮ ስላሴ፤ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል ናቸው፡፡

ቤቶቹ አስተዳደሩ የግንባታ ጥራት ችግሮችን በመቅረፍ በተሻለ ሁኔታ በመገንባት ያዘጋጃቸው ናቸው፡፡
2.5K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:09:53
2.4K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:09:27 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ለ25,491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ አስተላለፈ!!

የከተማ አስተዳደሩ ሲያስገነባቸው የነበራቸውን ቤቶች የነበረባቸውን የመሰረተ ልማትና የጥራት ችግሮች በመቅረፍ ሌት ተቀን በመረባረብ ለዛሬ እጣ ካበቃቸው በ40/60 ለ3ኛ ጊዜ እና በ20/80 14ኛ ጊዜ በድምሩ 25,491 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በዛሬው እለት በይፋዊ ስነስርዓት ለቆጣቢዎች አስተላልፏል፡፡

ከባንክ በተገኘው መረጃ መሠረት በእጣ ማውጣቱ ሂደት በተወዳዳሪነት የቀረቡት በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 27,195 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 52,599 በአጠቃላይ 79,794 ተመዝጋቢዎች ናቸው፡፡

የእጣ ማውጣቱን ስነስርዓት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና ሌሎች አመራሮች ገለልተኛ ታዛቢዎች የተመዝጋቢዎች ተወካዮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች በተገኙበት በይፋዊ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ሲሆን በተለይም በዕጣ አወጣት ስነስርዓቱ በልዩ ሁኔታ የቅድሚያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችን በአግባቡ የሚለይበትን አግባብ ጭምር ሂደቱን በማብራራት እና በቀጥታ ስርጭት በማከናወን በግልፅነት ተከናውኗል፡፡
እጣ የወጣላቸውንም ስም ዝርዝር ማመሳከር ይቻል ዘንድ እስከመጨረሻው በእጣ የተካተቱትን ሰዎች ስም ዝርዝር ታዛቢዎች ባሉበት ሁኔታ በይፋ ታትሞ ታዛቢዎች በእያንዳንዱ ወረቀት ላይ እንዲፈርሙና ማህተም ተደርጎባቸው የሚቀመጡ ይሆናሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለባለእድለኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን!!
2.3K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ