Get Mystery Box with random crypto!

የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት ተካሄደ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት ተካሄደ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት አካሄዱ፡፡

"በሚተካ ደማችን የማይተካውን የሰው ህይወት እናድን" በሚል መርህ በተካሄደው ሥነ ሰርዓት ላይ የቢሮውና የኮርፖሬሽኑ እንዲሁም የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በየሦስት ወሩ ደም ለመለገስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በዘንድሮው የ2015 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል ፡፡ 

ደም ከለገሱ ሠራተችና የሥራ ኃላፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ደም በመለገስ የሰው ህይወትን ለማዳን እየተደረገ ባለው ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ ለወገኖቻቸው ያላቸውን አጋርነት በተግባር ለመግለፅ ደም ለመለገስ መወሰናቸውን ገልፀው ሌሎችም የእነርሱን አርአያነት በመከተል ደማቸውን በመለገስ ህይወት ለማዳን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

aahdab2021@gmail.com

https://www.facebook.com/aahdabofficial