Get Mystery Box with random crypto!

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aahdabofficial — A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
የሰርጥ አድራሻ: @aahdabofficial
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.94K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-29 11:24:19
1289 ያህሉ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቅፅ መውሰዳቸው ተገለፀ

ኮርፖሬሽኑ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች ውል እያዋዋለ ሲሆን ውል ከተጀመረ ጀምሮ እስከ 20/08/2015 ዓ.ም ድረስ   በወጣላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ቀርበው የመክፈያ ቅፅ የወሰዱ ተጫራቾች 1289 መሆናቸውን የንግድ ቤት ውል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ደረጀ ገልፀዋል።

በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ክፍያ ከፍለው ከኮርፖሬሽኑ ጋር የሽያጭ ውል የፈፀሙ ተጫራቾች ደግሞ 215 መሆናቸውንም አስተባባሪው ያሳወቁ ሲሆን የንግድ ቤት አሸናፊዎቹን ውል የማዋዋል ሂደትም እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficia
3.4K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:43:42
4.5K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:43:07 ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 20/80  እና 40/60 ነባር ሳይቶችን እና የየካ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም  20/80 ነባር ሳይቶች ለነዋሪዎች ተላልፈው የተወሰኑ ነዋሪዎች የገቡ ሲሆን አንዳንድ መጠናቀቅ ያለባቸው የተንጠባጠቡ ስራዎች ማለትም ሊፍት ገጠማ ፤ የሮቶ ከመስመር ጋር ያለማገናኘት እና ዋተር ፖምፕ አለመገጠም ፤ አንዳንድ ደረጃዎች የብረት ስራ  አለመጠናቀቅ ሲሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ አሳስቧል።

ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር  እየተሰሩ ያሉ  የጋራ መኖሪያ  ነባር ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ  ያሉ ችግሮችን  ተቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሳይቱ የታዩትን ችግሮች በመለየት አመራሩ  ተግቶና ጠንክሮ በመስራት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ተጠናቀው ለነዋሪው መረከብ እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሌላው የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤትን ጉብኝት ሲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው በኮንዶሚኒየም ፣በቀበሌና ንግድ ቤቶች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች አንስቷል። የጽ/ቤት ኃላፊውና የሚመለከታቸው አካላቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

በክ/ከተማው ስር የሚገኙ 17,474 ቤቶች ወደ ሲስተም ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች የሚተላለፉበትን አሰራር የፈተሸ ሲሆን  በልዩ ሁኔታ ከሚሰጣቸው ውጭ የተሻለ አሰራር ተከትሎ እንደሚሰራ ከተቋሙ ዳይሬክተር  እና ከፋይሎች መረዳት ተችሏል ።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ወ/ሮ ኒኢመታላህ ከበደ   የቤቶች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን እና በ13ተኛው ዙር የወጡ ቤቶች ተለይተው መያዛቸው እንደ ጠንካራ ጎን አንስተው ፤ ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ እንደሚገባና የነዋሪው ቅሬታ በአግባቡ መፈታት እንዳለበት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ባህላችንም መሻሻል እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.4K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:24:51
2.4K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:24:26 በቀሪ ወራት በበጀት ዓመቱ  የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ

በቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ለ2015 በጀት ዓመት ቀሪ ወራት የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ከምንግዜውም በላይ  መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በአሥራ አንዱ ክፍለ ከተሞች የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤቶች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ያተኮረ ውይይትም ተካሂዷል፡፡

የአዲሰ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የቤት ልማትና አስተዳደር ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አረጋሽ ቸኮል በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር በቤቶች ልማትና አሠራር ሥርዓት ዘርፍ ለዘንድሮው በጀት ዓመት በዕቅድ የተቀመጡትን ተግባራት በስኬት ለማጠናቀቅ እና በሥራ ሂደት ውስጥ የሚከሰቱትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ማስቀመጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንግዜውም በላይ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

የቢሮው የቤት ጥናትና ስትራቴጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ተዋቡ ቀስቅስ ባቀረቡት የዘጠኘ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ የቤቶችን መረጃ አያያዝ ከማሳደግ አንፃር የተከናወኑ ተግባራን እንዲሁም የመንግስት የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ውል ዕድሳትን በተመለከተ የተገኘውን አበረታች ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ፍትሀዊ የቤት ማስተላለፍን በተመለከተ በመመሪያው መሠረት ለሴቶች 30 በመቶ እንዲሁም 20 በመቶ ለመንግስት ሰራተኞችን እና 5 በመቶ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ  የቢሮው እና የየክፍለ ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.5K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 19:22:07
የቢሮው የ3ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ

የቢሮው የ3ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም በቢሮው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ዳይሬከተሮች ጋር ተገምግሟል ።

በተለይም በየስራ ክፍሉ በአፈፃፀም ክፍተት የነበረባቸው ስራዎች ላይ ሁሉም ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት በመውሰድ ማስተካከል ይገባችኋል ያሉት አፈፃፀሙን የገመገሙት የቢሮው ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲሳ አራርሶ ናቸው።

ኃላፊው አክለውሞ በቀጣይም የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በመያዝ ለለውጥ መትጋት እና የታዩ  ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማስቀጠል ድክመቶችን  ደግሞ ማረም ይገባል ብለዋል።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.5K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 23:24:38
የነባር ፕሮጀክት ግንባታ የማጠቃለያ ምእራፍ  ያለበትን ደረጃ  ቋሚ ኮሚቴው ተመለከተ

በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የከተማ ልማት ፣ ኮንስትራክሽንና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በኮየ ፈጬ የጋራ መኖሪያ  ፕሮጀክቶችን ተመልክቷል።

ቋሚ ኮሚቴውም ነዋሪው ቤቱን በራሱ  እያደሰና እያስተካከለ ቢገባም የመሰረተ ልማት ተቋማት ሊያሟሉ የሚገባቸው ቀሪ ስራዎች ማሟላት እንዳለባቸው አሳስቧል።

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጂ አቶ ተካልኝ የመንገድ ስራውን  ኢኮስኮ  እየሰራ እንዳለና የውሃ መስመር ዝርጋታም እንደተጀመረ ገልጸው ነገር ግን ወደ ኢንዱስትሪ መስመር የሚሻገረው ዋና መስመር እንዳልተገናኘ ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ 1071   ህንፃዎች የተሰሩ ሲሆን በ385 ተቋራጭ እና በ1025 ማህበራት  ስራውን  እስከ ሰኔ 30 ለኗሪዎች  ምቹ ለማድረግ  በልዩ ትኩረት እየተሰራ ያለ መሆኑም ተገልጿል።

አሁንም 66 ህንፃዎች ተጠናቀው ከኮንትራክተር ርክክብ ያልተደረገባቸው እንዳሉ የተረጋጋጠ ሲሆን እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ 33 ህንፃዎችን ለመረከብ እየሰሩ መሆኑ አበረታች መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ ገልፀዋል።

ወደ ጋራ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው የሚኖሩ ነዋሪዎች እና የነዋሪ ኮሚቴዎች እንዳሉት የቀሩ የለቀማ ስራዎች እና  ከመሠረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ጋር ተቀራርቦ መስራት ላይ ያለውን ችግር  በጋራ መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
4.7K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:08:00
2.3K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:07:08 አዲስ ከተመደቡት የቢሮ ኃላፊ ጋር የሥራ ርክክብ ተካሄደ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊነት አዲስ የተመደቡት ወ/ሮ ጽጌ ወይኒ ካህሳይ በቤቶች ልማት ዘርፍ የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን አስታወቁ፡፡
ከቀድሞዋ የቢሮ ኃላፊ ወ/ሪት ያስሚን ወሀብረቢ ጋርም የሥራ ርክክብ ተካሂዷል፡፡

አዲስ የተመደቡት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጽጌወይኒ ካህሳይ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስትና የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ቢሮውና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጀመሩትን የለውጥ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉም ወገን ይበልጥ ተቀናጅቶ በጋራ መንቀሳቀስ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በተመደቡበት የኃላፊነት ቦታም የሚጠበቅባቸውን  ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ይበልጥ በማጠናከርና በሥራ ሂደት ውስጥ ለተከሰቱ ክፍተቶችንም ማስተካከል የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የተጀመረውን የልማት ጉዞ ከግብ ማድረስ እንደሚገባም ወ/ሮ ጽጌወይኒ አስገንዝበዋል፡፡

የቀድሞዋ የቢሮ ኃላፊ ወ/ሪት ያስሚን ወሀብረቢ በበኩላቸው ወደ ሌላ ተቋም ተመድበው ቢሄዱም ከቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በበለጠ ቅርበት ተቀናጅተው መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የቢሮው የየሥራ ዘርፉ ኃላፊዎች እና የኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራር አከላት ግልፅ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት በቤቶች ልማት ፕሮግራም የተገኘውን ለውጥ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ከአዲሷ የቢሮ ኃላፊ ጋር በበለጠ ቅርበት እንደሚሠሩ አመልክተዋል፡፡

በሥነ ስርዓቱ ላይ የቢሮው እና የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial
2.3K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:02:35
2.1K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ