Get Mystery Box with random crypto!

በቀሪ ወራት በበጀት ዓመቱ  የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ በቤቶች ልማ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

በቀሪ ወራት በበጀት ዓመቱ  የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ

በቤቶች ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ለ2015 በጀት ዓመት ቀሪ ወራት የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ከምንግዜውም በላይ  መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በአሥራ አንዱ ክፍለ ከተሞች የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤቶች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ያተኮረ ውይይትም ተካሂዷል፡፡

የአዲሰ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የቤት ልማትና አስተዳደር ሥርዓት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ አረጋሽ ቸኮል በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር በቤቶች ልማትና አሠራር ሥርዓት ዘርፍ ለዘንድሮው በጀት ዓመት በዕቅድ የተቀመጡትን ተግባራት በስኬት ለማጠናቀቅ እና በሥራ ሂደት ውስጥ የሚከሰቱትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ማስቀመጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንግዜውም በላይ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

የቢሮው የቤት ጥናትና ስትራቴጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ተዋቡ ቀስቅስ ባቀረቡት የዘጠኘ ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በአሥራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ የቤቶችን መረጃ አያያዝ ከማሳደግ አንፃር የተከናወኑ ተግባራን እንዲሁም የመንግስት የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ውል ዕድሳትን በተመለከተ የተገኘውን አበረታች ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ፍትሀዊ የቤት ማስተላለፍን በተመለከተ በመመሪያው መሠረት ለሴቶች 30 በመቶ እንዲሁም 20 በመቶ ለመንግስት ሰራተኞችን እና 5 በመቶ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ  የቢሮው እና የየክፍለ ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial