Get Mystery Box with random crypto!

1289 ያህሉ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቅፅ መ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

1289 ያህሉ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቅፅ መውሰዳቸው ተገለፀ

ኮርፖሬሽኑ የ4ተኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች ውል እያዋዋለ ሲሆን ውል ከተጀመረ ጀምሮ እስከ 20/08/2015 ዓ.ም ድረስ   በወጣላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ቀርበው የመክፈያ ቅፅ የወሰዱ ተጫራቾች 1289 መሆናቸውን የንግድ ቤት ውል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ደረጀ ገልፀዋል።

በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ክፍያ ከፍለው ከኮርፖሬሽኑ ጋር የሽያጭ ውል የፈፀሙ ተጫራቾች ደግሞ 215 መሆናቸውንም አስተባባሪው ያሳወቁ ሲሆን የንግድ ቤት አሸናፊዎቹን ውል የማዋዋል ሂደትም እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል ።

http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficia