Get Mystery Box with random crypto!

በ54 ቡድን የተደለደሉ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀት ስራ ተሰራ የከተማው ህብረት ስራ ማህ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

በ54 ቡድን የተደለደሉ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን የማደራጀት ስራ ተሰራ

የከተማው ህብረት ስራ ማህበር ኤጀንሲ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በማህበር ለመገንባት በ54 ቡድን የተደለደሉትን በማህበር በማደራጀት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰራ ነው።

በ2005  ዓ.ም  በ40/60  እና በ20/80  የቤቶች ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን  ለመገንባት ሲቆጥቡ የነበሩ እና አሁን ግን በፍላጎታቸው በህብረት ስራ ማህበራት ለመደራጀት  ከ70 በመቶ በላይ  ለመቆጠብ  ዝግጁ የሆኑ ማህበራትን  ወደ ስራ  ለማስገባት  የማደራጀት  ህጋዊ እውቅና የመስጠት ስራ ተሰርቷል።

በቀጣይም ሰላሳ በመቶ ብድር ተመቻችቶ 70 ከመቶውን በማህበሩ የዝግ አካውንት ማስገባታቸው ሲረጋገጥ ግንባታው ለሚካሄድባቸው ሳይቶች እጣ የማውጣት እና የማስረከብ እንዲሁም የማስጀመር ስራ የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።


http://www.aahdab.gov.et

https://www.facebook.com/aahdabofficial70