Get Mystery Box with random crypto!

ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ የአዲስ አበ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ ይገባል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቦሌ ክ/ከተማ ቦሌ ቡልቡላ 20/80  እና 40/60 ነባር ሳይቶችን እና የየካ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴው በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም  20/80 ነባር ሳይቶች ለነዋሪዎች ተላልፈው የተወሰኑ ነዋሪዎች የገቡ ሲሆን አንዳንድ መጠናቀቅ ያለባቸው የተንጠባጠቡ ስራዎች ማለትም ሊፍት ገጠማ ፤ የሮቶ ከመስመር ጋር ያለማገናኘት እና ዋተር ፖምፕ አለመገጠም ፤ አንዳንድ ደረጃዎች የብረት ስራ  አለመጠናቀቅ ሲሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ አሳስቧል።

ኢ/ር ቶማስ ደበሌ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር  እየተሰሩ ያሉ  የጋራ መኖሪያ  ነባር ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ  ያሉ ችግሮችን  ተቋቁመው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሳይቱ የታዩትን ችግሮች በመለየት አመራሩ  ተግቶና ጠንክሮ በመስራት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ተጠናቀው ለነዋሪው መረከብ እንዳለባቸው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ሌላው የየካ ክፍለ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ጽ/ቤትን ጉብኝት ሲያደርጉ ቋሚ ኮሚቴው በኮንዶሚኒየም ፣በቀበሌና ንግድ ቤቶች ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎች አንስቷል። የጽ/ቤት ኃላፊውና የሚመለከታቸው አካላቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

በክ/ከተማው ስር የሚገኙ 17,474 ቤቶች ወደ ሲስተም ገብተው የተመዘገቡ መሆናቸውንም ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ቋሚ ኮሚቴው የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች የሚተላለፉበትን አሰራር የፈተሸ ሲሆን  በልዩ ሁኔታ ከሚሰጣቸው ውጭ የተሻለ አሰራር ተከትሎ እንደሚሰራ ከተቋሙ ዳይሬክተር  እና ከፋይሎች መረዳት ተችሏል ።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳሲ የተከበሩ ወ/ሮ ኒኢመታላህ ከበደ   የቤቶች ፋይል ወደ ሲስተም መግባቱን እና በ13ተኛው ዙር የወጡ ቤቶች ተለይተው መያዛቸው እንደ ጠንካራ ጎን አንስተው ፤ ያልተጠናቀቁ ግንባታዎችን በተጀመረው ፍጥነት አጠናቆ ለነዋሪው ማስረከብ እንደሚገባና የነዋሪው ቅሬታ በአግባቡ መፈታት እንዳለበት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ባህላችንም መሻሻል እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

http://www.aahdab.gov.et

https://t.me/aahdabofficial

https://www.facebook.com/aahdabofficial