Get Mystery Box with random crypto!

ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ እስከ ሰኔ ወር እንዲጠናቀቅ ከንቲባ አዳነች አሳሰቡ የጋ | A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖርያ ቤቶች ግንባታ እስከ ሰኔ ወር እንዲጠናቀቅ ከንቲባ አዳነች አሳሰቡ

የጋራ መኖርያ ቤቶችን ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ያለማጠናቀቅ ክፍተት መኖሩን የገመገሙት ከንቲባ አዳነች ለዚህ ክፍተት የሲሚንቶ እጥረት፣ የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ ልዩነት እንዲሁም የወሰን ማስከበር ችግር መኖሩን ተገንዝበናል ብለዋል

ሆኖም እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ፣ የጋራ መኖርያ ቤቶችን መሰረታዊ ግንባታ መንግስት በአፋጣኝ በማጠናቀቅ፣ ቀሪውን ተጠቃሚው እንዲያሟላ የሚደረግ ሲሆን የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ቀሪ ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን ይህንንም የሚከታተሉ ተቋማትና ኮሚቴዎች በየሳምንቱ የግንባታውን ሂደት ይከታተላሉ ብለዋል።

የተነሱት የግብዓት እጥረትና የዋጋ ልዩነቶችም አፋጣኝ እልባት አግኝተው እስከ ሰኔ ወር ባለው ግዜ ግንባታዎች ተጠናቅቀው ለተጠቃሚው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።