Get Mystery Box with random crypto!

💖የኔ ፍቅር 😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.94K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-02-10 20:49:01 እንግዳዬ

ከሰማይ ጣቃ ጨርቅ
በልክሽ ያጌጠ ፥ ካባ ሰፍቻለሁ
ከቀዥቃዣው ንፋስ
ጠረኑን ዘግኜ ፥ ቤቴን አጥኛለሁ፡፡
በዳመና ጉዝጓዝ
መምጫ መንገድሽን ፥ አሳምሬዋለሁ
ለጎጆ'ችን ድምቀት
ከፀሀይ ቆንጥሬ ፥ ንጋት ሰቅያለሁ፡፡
ታዲያ በምን ሰበብ...
ምን ምክንያት አድርገሽ
እንዲህ ስጠብቅሽ ፥ ልቅር ትይኛለሽ???
ይገርምሻል ውዴ...
ጨለማ እንኳን ባቅሙ
ከልቤ ተረድቶ ፥ እንግዳዬ እንደሆንሽ
ጨረቃዋን ጋርዶ
አካሉን ዘርግቷል ፥ አልጋ ሊያበጅልሽ
ይልቅ ቶሎ መጥተሽ
ጨለማሽ ላይ ተኝ ፥ ኮከብሽን ለብሰሽ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
558 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 19:30:37
#Fekir_1K295

Sigerm beakal balawkhm nstuh lbh lesew asabineth hulu negerh slante endasb adrgogal Mannm wend edate wedje alawkm bandewawelm text banaweram 1dekikam kasabe awtcheh alawkm wedhalehu yene f**

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
596 viewsedited  16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 22:48:01 (አልቻልኩም)

ቃል አቅም የለው ምክን ነው ፊደሉ፣
ሰፍረው ከብራናው ሞልተው የጎደሉ፣

ሳቄ የእምባ ነው ደስታዬ የለቅሶ፣
ፈውሴ የህመም የማይድን ተዳብሶ፣

በቃ እንዲዚ ነኝ ናፍቆት ያቃተኝ ለት፣
ልቤ ማይመለስ በግዝት በስለት፣

አይኔ እየተራበሽ አለ እየኖረ፣
ሌላውን እንዳያይ በፍቅር የታወረ፣

ካንቺ ሌላ ደስታ ሊሰጡኝ ቢጥሩ፣
ለኔ ሀዘን ሆነብኝ እልፍ ቢያማትሩ፣

የለመደሽ ልቤ በናፍቆትሽ ናውዞ ይኸው ይዋልላል፣
ሚመልስሽ ባይኖር እየደጋገመ አንቺን ይጠይቃል፣

ግን አይከብድም ውዴ፣

ሳቄ ደስታ ቢስ ነው፣
እንቅልፌ ረፍት የለው፣
አካሌ የደከመ ናፍቆት ያመነነው፣

ደና ነህ ለሚሉኝ እላለሁኝ ደህና፣
ቁስሌ እየባሰ ናፍቆት እየፀና፣

አንቺ ግን እንዴት ነሽ የልቤ ትርታ፣
የመጀመሪያዬ የፍቅሬ ሀሌታ፣

እኔ አልቻልኩበትም ያነጫንጨኛል፣
በሆነው ባልሆነው ቶሎ ይከፋኛል፣

ያ ያለፍነው ጊዜ ብርታት ባይሆነልኝ፣
እኔ አልችልም ነበር ናፍቆት በገደለኝ፣

ቀኑ ነግቶ እስኪመሽ አንቺው ነሽ ሃሳቤ፣
ውዴ አልቻልኩበትም ነይልኝ ረሃቤ፣

ጨዋታና ሳቅሽን እያሰላሰልኩኝ፣
ካጠገቤ ሳጣሽ በንባ ፅፌ ላኩኝ፣

ቀኑ ይከብደኛል አያልቅም ሰዓቱ፣
ያላንቺ አያምርም ቢመሽም መንጋቱ፣

ደግሜ አይሻለሁ አልተጠራጠርኩም፣
ግን መቼ ነው ውዴ ኸረ እኔ አልቻልኩም፡፡

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
740 views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 18:05:08 አንድ ቀን

አፍቅሪኝ አልልሽም
እኔ እንዳፈቀርኩሽ
ተጎጂ አልልሽም
እኔ እንደተጎዳሁት
አንቺን በኔ ቦታ ማየት አልፈልግም
ከቶ አያረካኝም…
ግን ብቻ አደራ…
ከልብሽ ውደጂኝ ከውስጥሽ አኑሪኝ
ከህሊናሽ ካልራኩ ቢቆጠሩ አመታት
ታፈቅሪኝ ይሆናል አንድ ቀን ምናልባት።

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
652 views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:03:01 ልቤን ተቀየምኩት°°°°

ውዴ,,,..........
ፍቅሬን በመግለፄ ትከፊ ይሆናል
ነገር ግን ተፈርቶ እስከመች ይኖራል
የልቤን አውጥቼ እስኪ ልተንፍሰው
አልኩና ተነሳው ልቤን ላሳርፈው
የውስጤን ህመሜን አምጬ ላፈርጠው
የማይደርስ የለ ደረሰና ወቅቱ
ሀሉንም ነገርኩሽ የልቤን ስሜቱ
ባንቺ እንደሆነ ልቤ መዋተቱ
በቃ አፍቅርሻለው ይሄ ነው እውነቱ
,
,
እስቲ,,, ላስብበት ትንሽ ጊዜ ስጠኝ
ብለሽ የሸኘሽው ልቤ ሰላም ነሳኝ
,
,
ምላሹን በጉጉት ሲጠብቅ የኖረው
ቢሆንም ይሆናል ቢቀርም አይቀርም ብሎ ያሎሰነው
በስተመጨረሻም ይኸው ገላገልሽው
እንደማይሆን ነግረሽ ቁርጡን አሳወቅሽው
,,,
እኔ ግን ልንገርሽ,, እውነቴን ነው ምልሽ
በጭራሽ አላዘንኩ በዛ ቆራጥ ምላሽ
በጣም የታዘብኩት ሁሌም ምቀየመው
እንደማይሆን ሰግቶ ሲኖር የነበረው
ሁሉንም በፀጋ ሊቀበል ያልቻለው
#ልቤን_ተቀየምኩት ሰላምና ደስታ ሊሰጠኝ ያልቻለው

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
846 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 18:04:01 *ጠባቂ*

ትመጫለሽ ሲሉኝ ትመጫለሽ ብዬ፣
ስጠብቅሽ ነበር በሌለኝ ማጌጫ ልስብሽ ተኩዬ፣

ትመጫለሽ ካሉኝ ሰዓታት ተጓዙ፣
ቀናትም ተዳምረው አመትን መዘዙ፣
ከበርቴዎች አጥተው በርሃብ ታረዙ፣

እንዲ ነው ሚመስለኝ አንቺን ስጠብቅሽ፣
ከነጋ ማይታይ ጨልሞ የማይመሽ፣

እኔ ያንቺ ጠባቂ ሰዓት ወር ሆኖብኝ፣
እየጠበኩሽ ነው ትመጫለሽ ቢሉኝ፣

እመጣለሁ ስትይ መች ሰምቼ ቃልሽን፣
ሲሉኝ ጠበኩ እንጂ እንዳየው አይንሽን፣

ብታዪ፣
ስትቆዪ፣
ፍጡራን ነፍስ አልባ ሆነው ይታዩኛል፣
በምድር ብቻዬን የቀረሁኝ ያህል ደርሶ ይሰማኛል፣

አዎ በቃ እንዲ ነኝ እኔ ያንቺ ጠባቂ፣
ማወቄን የተውኩኝ ምሁር አላዋቂ፣

ባልተያዘ ተስፋ ባልታየ ጭላንጭል፣
ባልተሰማ ብስራት እንዲያ ስኮበልል፣

ላግኝሽ ብዬ ነው ትመጫለሽ ሲሉኝ፣
ቀጥረሽኝ እንዳልሆን እያወኩ የቆምኩኝ፣
በማታውቂው ስፍራ አንቺን የጠበኩኝ፣
ባልተቆረጠ ቀን ላይሽ የቸኮልኩኝ፣

እንዲ ነኝ ጠባቂሽ ያሉትን ሰምቼ፣
ከቃላቸው ሰብል ተስፋዬን ሸምቼ፣
በተስፋ ቢስ ልቤ ተስፋሽን ዘርቼ፣
እየጠበኩሽ ነው መምጣትሽን እያሰብኩ የኔን መሄድ ትቼ፣

ያንቺ ነገር ሲሆን ልጅ ነኝ አላዋቂ፣
ቀጣሪ ሳይኖረኝ ባልታወቀ ስፍራ ማትመጪን ጠባቂ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
1.3K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 18:03:01 መተሽብኝ ነበር :
ለሊት ላይ በህልሜ፣
አቤት ብዬም ነበር :
ስምሽ መስሎኝ ስሜ፣
ግና ሳልጨርሰው :
ፍቅርን አጣጥሜ፣
ፍጥን እንደ ንፋስ :
እጥር እንደ #ጳጉሜ፣
..............አልሽብኝ አለሜ ።

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
813 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 18:02:01 """"""ለዘመናት ሳፈቅርሽ""""""

ላንቺ ስኖርልሽ
የኔን ህይወት ትተሽ
ያንቺን ሳደምቅልሽ
በልቤ ተጫውተሽ ጎድተሽኝ ብትሄጂም
እኔ ላንቺ ስኖር ግድ አይሰጠኝም
እውነተኛ ፍቅር ጭራሽ ባይገባሽም
መልካሙን ያጋጥምሽ
ክፋ አልመኝልሽ
እኔ የተጎዳሁትን አንቺ ባትክሺኝ
ሌላ ምን እላለው ልቤን መልሺልኝ

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
699 views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 18:01:01 ስስምሽ ስላየሁ
ትላንትና በህልሜ
ዛሬን ቶሎ ተኛሁ
ልስምሽ ደግሜ
ታድያ ምን ያረጋል
የህልሜ ደራሲ
አትታደል ቢለኝ
ህልሜን ገለባብጦ
ሲስሙሽ አሳየኝ!!!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
1.3K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 18:01:01 #በዝምታዬ

በዝምታዬ ነው ያፈንኩት ስቃዬን፣
ለሰው ሳላወጋ ደብቄ ህመሜን፣
ደብኜ የቻልኩት ካንች መለየቴን፣

በዝምታዬ ነው ሳጣሽ የሸኘሁሸ፣
በልቤ አንብቼ የተሰናበትኩሽ፣
ምልጃም አላሰማው እያልኩኝ ተመለሽ፣

ብቻ እያየሁት የእግርሽን ዳና፣
ተመኘው ምቾትን በመራሽ ጎዳና፣
ስትሄጂ ሸኘሁሽ እኔም ዝም አልኩና፣

አቅሜ እሱ ነበር ያለው በመዳፌ፣
ክደት ከርችሞታል አይናገር አፌ፣
ዝም አልኩኝ ሲዘረፍ ሲከፈት ደጃፌ፣
የኔ ያልኳት ርቃኝ ሀዘኔን ሸክፌ፣
ልቤ ተቀዳዶ ላይጠግነው መርፌ፣
አልከስሽ ለዳኛ የውስጤን ጡር ፅፌ፣
ለፍቅር ተማርኬ ላንቺ ተሸንፌ፣
ዝም አልኩ ስትሄጂ ሲደፈር ደጃፌ፣

ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
እንደው ተብከነከንኩ፣
ትፋሼን አርዝሜ ቁናውን ተነፈስኩ፣
ዕንባዬን ሳላፈስ አምርሬ አለቀስኩ፣
በፍቅር እየኖርኩ ፍቅርን ረገምኩ፣
መሞሸሬ ቀርቶ ይባስ ብቸኛ ሆንኩ፣
ውስጤ እሬታ በዛ ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
ከራሴ ተላተምኩ፣
ለሽንፈት ተሸነፍኩ፣

ዝም ብዬ ልሸኝሽ፣
ቸው እንኳን ሳልልሽ፣
መልካሙን ምኞቴን 'ባፌ ሳልገልፅልሽ፣
ይሄን የማረግው ስለምን መሰለሽ፣
ደጅ ደጁን እንዳይ ነው ብዬ ትመጫለሽ፣

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
189 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ