Get Mystery Box with random crypto!

እንግዳዬ ከሰማይ ጣቃ ጨርቅ በልክሽ ያጌጠ ፥ ካባ ሰፍቻለሁ ከቀዥቃዣው ንፋስ ጠረኑን ዘግኜ ፥ | 💖የኔ ፍቅር 😘

እንግዳዬ


ከሰማይ ጣቃ ጨርቅ
በልክሽ ያጌጠ ፥ ካባ ሰፍቻለሁ
ከቀዥቃዣው ንፋስ
ጠረኑን ዘግኜ ፥ ቤቴን አጥኛለሁ፡፡
በዳመና ጉዝጓዝ
መምጫ መንገድሽን ፥ አሳምሬዋለሁ
ለጎጆ'ችን ድምቀት
ከፀሀይ ቆንጥሬ ፥ ንጋት ሰቅያለሁ፡፡
ታዲያ በምን ሰበብ...
ምን ምክንያት አድርገሽ
እንዲህ ስጠብቅሽ ፥ ልቅር ትይኛለሽ???
ይገርምሻል ውዴ...
ጨለማ እንኳን ባቅሙ
ከልቤ ተረድቶ ፥ እንግዳዬ እንደሆንሽ
ጨረቃዋን ጋርዶ
አካሉን ዘርግቷል ፥ አልጋ ሊያበጅልሽ
ይልቅ ቶሎ መጥተሽ
ጨለማሽ ላይ ተኝ ፥ ኮከብሽን ለብሰሽ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir