💖የኔ ፍቅር 😘 — Telegrami kanal

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
Mitteaktiivne
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.58K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Kanali statistika
12.2% Kaasatuse määr
1,048 Vaatamisi / postitus
0 Postitusi / päev

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

18 veebr 2023
አጭር የፍቅር ታሪክ (ካነበብኩት)


እሷ= ናፍቀህኛል!?

እሱ= ኧረ ባክሽ?

እሷ= የምሬን ነው!

እሱ= እሽ።

እሷ= ይቅርታ..?

እሱ= ለምኑ?

እሷ= እኔ ጋር ለመቅረብ በጣም ጥረት ስታደርግ
ስለዘጋዉህ…

እሱ=ችግር የለዉም… ከጊዜ ጋር ለመድኩት…እናም ደከመኝ… መሞከሬን ትቸ መርሳት ጀመርኩ…

እሷ= እኔ…እኔ…ስለ አንት አለማሰብ ሞክሬ ነበር…እና…አብረን ልንሆን…

እሱ= ችግር የለዉም!

እሷ= ማለት?

እሱ= ለምጀዋለሁ..አንድ ቀን ወደኔ ትመጫለሽ እያልኩ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን አልመጣሽም ነበር እና እኔ እዉነቱን መጋፈጥ ጀመርኩ…እና ወደፊት መራመድ እንዳለብኝ አመንኩ…

እሷ= ቆይ…እና በጣም ረፍዶብኛል?

እሱ= ለምኑ ነው በጣም የረፈደብሽ?

እሷ= ካንተ ጋር ለመሆን..?

እሱ= ታዉቂያለሽ? ይህን ካንች መስማት እፈልግ ነበር ግን ከአመት በፊት ነበር…በተስፋ አንችን ስመኝ… ግን ሊሆን እንደማይችል ተረዳሁ ከዛ ተስፋ ማድረጌን መመኘቴን አቆምኩ…

እሷ= በጣም ይቅርታ… አትጨነቅ… አሁን ግን ምኞትን ሁሉ አሳካልሃለው:)

እሱ= ያ ሊሆን እማይችል ነው… ሌላ ሰው በሂወቴ ገብቷል…

እሷ= ላንተ ጥሩ ነው…ማን ናት? መቼስ ነው እምገናኛት?

እሱ= መቼም ቢሆን ልታገኝሽ አትፈልግም!!

እሷ= ለምን? ምን አድርጊያት አለሁ?

እሱ= በቃ ልታይሽ አትፈልግም!

እሷ= ቆይ እሽ ለምን?

ልጁም ቀስብሎ መለሰላት…

እሱ= በቃ በጣም የጎዳችኝን ሴት ልታገኛት አትፈልግም…
አሁን ይቅርታ ማያው ተራው የኔ ነው… ጊዜ በኔ ላይ ስለሆነ…ልቤን ሲጀመር ሰብረሽዋል እና ያን ድጋሚ ማሳለፍ ፣ ልቤን አደጋ ላይ መጣል አልችልም… ለማንኛዉም አመሰግናለሁ… ከአመታት ዝምታ በኋላ ስላናገርሽኝ…።

እሷም አንገቷን ደፍታ በዝምታ ሄደች

ከሄደች በኋላ እሱም ከዋሌቱ የነበረዉን የሷን ፎቶ አዉጥቶ አነባ
እናም ፎቶዉን ወደአፉ ጠጋ አርጎ
"አሁንም አንች ነሽ" አለ።


ልጁ ያልተቀበላትም የካንሰር በሽታ እንዳለበት እና በሁለት ወራት ዉስጥ እንደሚሞት ስለተነገረው ነበር።



ተፈፀመ


በዚች አለም ትልቁ እና ዋጋ ያለው ነገር ጊዜ ነው! ለዝች አለም ሁላችንም እንግዶች ነን መቼ እና እንዴት እንደምንሞት አናዉቅም! ስለዚህ በቻለነው መጠን ጊዜችን በአግባቡ እንጠቀም ልቦናችንን እንክፈት…በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል!!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
411 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
7 jaan 2023
Picture 1 from 💖የኔ ፍቅር 😘 2023-01-07 19:10:40
#Fekir_1K277

#Yene fikir fexari anchin silesexey ameseginalew hulem hulem kelibe afekrishalew @@ hulem bexewat sinesa inde maleda tsehay yemitaberi birhane mesh gene fikir neffffffffffff amet nuriliy kiya made gene bite binageer qal aygeltsewim silezih zim biyee liwdedishhhh
Ke. She.
Le.Kal

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
758 viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
15 nov 2022
ሴት ልጅ ባንተ ላይ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳዩ 7 ምልክቶች

የማትወድህ የማትፈልግህ ሴት ጋር ሄዶ መጣበቅ አውሮፕላን ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው፡፡ መርከቧ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ መጥታ ልታገኛት እንደማትችል ሁሉ የማትወድህ የማትፈልግህ ልጅም እጅህ ልትገባ አትችልም፡፡ ስለዚህ አውሮፕላን ማረፊያ ቁጭ ብለህ መቼም የማትመጣዋን መርከብ ከመጠበቅ ይልቅ መርከቧ ወደምትመጣበት ወደብ መሄዱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡

ደስ ያለችህ የወደድካት ልጅ ከዚህ ቀጥለው ከተዘረዘሩት ምልክቶች በአብዛኛው ካሳየችህ ፍላጎት የላትም ማለት ነው፡፡

1. ካላስታወሰችህ

የሆነ ጊዜ የሆነ ቦታ ላይ ተዋውቃችሁ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስታገኛት ስምህን ከረሳችው አንተ ላይ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ ስምህ አበበ ሆኖ ሳለ በቀለ ብላ ከጠራችህም እንደዛው፡፡ ምክንያቱም ስምህን እንኳን አጥርታ ለማወቅ ያልፈለገች ልጅ አንተን ትፈልግሃለች ተብሎ አይታሰብም፡፡

2. ካልመለሰችልህ

ከአንድም ሁለት ጊዜ ስልክ ደውለህላት፣ ቴክስት አድርገህላት፣ ፌስቡክ ላይ ኢንቦክስ አድርገህላት፣ ኢሜይል ልከህላት ካልመለሰችልህ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ፍላጎት የላትም፡፡

3. በደምብ የማታወራህ ከሆነ

ከምትወዳት ልጅ ጋር ስትገናኝ ጥያቄዎች እያቀረብክ እሷ እንድታወራ በማድረግ ሁለመናህን ጆሮ አድርገህ እንድታዳምጥ ነው የሚመከረው፡፡ አንተም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን እየጠየቅህ ለማዳመጥ የመስማት የስሜት ህዋስህን ዘርግተህ ስትጠብቅ አጫጭር መልስ እየሰጠችህ ዝም የምትል ከሆነ ችግር አለ፡፡ ለጥያቄዎችህ አጫጭር መልስ ከመስጠት በተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ጨዋታውን ለማራዘም ምንም አስተዋፅኦ የማታደርግ ከሆነ ኤርፖርት ላይ መርከብ እየጠበቅህ መሆንህን አውቀህ ኤርፖርቱን ለቀህ ወደ ወደቡ ተንቀሳቀስ፡፡

4. ድንገት እቸኩላለሁ ካለችህ

አግኝተሃት ደስ ብሎህ አብረሃት ቁጭ ብለህ ጨዋታ ስትጀምር ድንገት “እቸኩላለሁ” ብላህ ተነስታ ከሄደች እርምህን አውጣ፡፡

5. የማያሳምን ምክንያት የምትሰጥህ ከሆነ

ልታገኛት ልትጋብዛት ፈልገህ ስትጠይቃት የማያሳምን ምክንያት ነግራ እንደማይመቻት የምትነግርህ ከሆነ ፍላጎት የላትም፡፡ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ፊልም ሲመረቅ ልትጋብዛት ፈልገህ ጥያቄ ስታቀርብላት “በጣም ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን ዛሬ ማታ አባየ ቀዶ ህክምና ስለሚያደርግ ከእርሱ ጋር መሆን አለብኝ” የሚል አይነት ምክንያት ልትነግርህ ሲገባ “አይመቸኝም፡፡ ብዙ የሚታጠብ ሳህንና ድስት አለኝ” የሚል ዓይነት ምክንያት ከሰጠችህ ከአንተ ጋር አዲስ ፊልም ከማየት ይልቅ ቆሻሻ ሳህንና ድስት ማጠብ መርጣለች፡፡ ስለዚህ “አዲዮስ አሚጎ” ልትላት ይገባል፡፡

6. የምትደበቅ ከሆነ

መንገድ ላይ ስታይህ መንገድ የምትቀይር ከዛም አልፎ ለመደበቅ የምትሞክር ከሆነ ሁለተኛ እንዳታስባት እዛው ለራስህ ቃል ግባ፡፡

7. ሌሎች ምክንያቶች

ብዙ ጊዜ ልታገኛት ስትፈልግ “ቢዚ” ነኝ የሚል ምላሽ የምትሰጥህ ከሆነ፤ ስልክ ስትደውልላት “አሁን ማውራት አልችልም” እያለች የምታሳጥርብህ ከሆነ፤ በጨዋታችሁ መሀል በተደጋጋሚ ስለሌሎች ወንዶች የምታነሳብህ ከሆነ፤ ከሌሎች ሴት ጓደኞቿ ጋር ልታያይዝህ የምትጥር ከሆነ፤ ፍቅረኛ የመያዝ ፍላጎት እንደሌላት ከነገረችህ ካንተ ጋር የፍቅር ግንኙነት የመጀመር ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
1.8K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
9 nov 2022
#ባለታሪክ_2

እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

ለስራ መስክ በወጣሁበት አንድ አጋጣሚ ከአንድ ልጅ ጋር ተዋውቀን በጊዜ ሂደት ተግባባን፤ ውሎ ሲያድርም መግባባቱ ተቀይሮ አፈቀርኳትና የፍቅር ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡

ይሁን እንጅ እርሷ እንዲህ አይነት ግንኙነት እንዲኖራት እንደማትፈልግ ገልፃ ለጥያቄየ ይሁንታን ነፈገችኝ፤ እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ እሷን የእኔ ለማድረግ ለወራት በጥያቄየ ገፋሁ፤ ይሁን እንጅ አሁንም በእምቢታዋ ጸናች።

ቀድሞ የነበራት ህይወት ያሳደረባት ተፅእኖ እና የልጅ እናት መሆኗ ደግሞ የእኔን የፍቅር ጥያቄ ላለመቀበሏ ምክንያት ነበር።

ልጅ እንዳላት በነገረችኝ ወቅት ለጊዜው ባመነታም ባል ስለሌላት ተደስቼ ችግር እንደሌለው በመግለጽ ይሁን አልኳት። በተደጋጋሚ እንዳስብበት ብትነግረኝም ስለማፈቅራት አብረን መሆን እደምንችልና ልጁንም በጋራ እንደምናሳድግ ነገሬያት ተስማማን።

የምንኖርበት ቦታ ርቀት ቢኖረውም ርቀቱ ፍቅራችንን ሳይገድበው መተሳሰባችን ሳይላላ ከአመት በላይ ቆየን፤ ጋብቻ አሰብንና ልንጋባ ሽማግሌ ለመላክ ተስማማን።
ለቤተሰቤ ላሳውቅ ብዬ ሽማግሌ ከመላኬ በፊት ላገባ መሆኔን ነገርኳቸው፤ ጥያቄየን ቢወዱትም ለትዳር የመረጥኳት ፍቅረኛየ ልጅ እንዳላት ስነግራቸው አምርረው ተቃወሙኝ፡፡

በፍፁም ልጅ ያላት ሴት ማግባት የለብህም በማለት ሃሳቤን እንድሰርዝ ነገሩኝ፤ እሷን ካገባህ ልጃችን አይደለህም መቃብራችን ላይም እንዳትቆም በማለት እሷን ወይም እኛን ምረጥ በማለት መስቀለኛ ጥያቄ አቀረቡልኝ።

በዚህ መሃል እኔ አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ።

ፍቅሬ ላይ ፈርጄ ቤተሰቦቼን እንዳልመርጥ ሳትፈልግ ገፋፍቼ የገባሁላትን ቃል ማፍረስ ከበደኝ፤ በዛ ላይ እወዳታለሁ ከእርሷ ጋር መጋባትም እፈልጋለሁ፡፡

ልቤን ተከትዬ የቤተሰቦቼን ቃል ትቼ ፍቅሬን እንዳልመርጥ ደግሞ በችግር አሳድገው ለዚህ ያበቁኝንና ጧሪ ቀባሪ ይሆነናል ብለው ተስፋ ያደረጉብኝ ቤተሰቦቼ ጋር እናዳልቆራረጥ
ሰጋሁ፤ መንታ መንገድ ላይ ቆሜ ተቸገርኩ።

ምን ባደርግ ይሻለኛል? እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

@yenefekir
1.2K views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
8 nov 2022
ስልክ ቁጥር የመቀበል ጥበብ

ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር መቀበልና ከአውሮፕላን በፓራሹት መዝለል አንድ ናቸው፡፡ መቶ ጊዜ ከአውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ የመዝለል ልምድ ቢኖርህም ለመቶአንደኛ ጊዜ ስትዘል መፍራትህ አይቀርም፡፡ ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር ስትቀበልም ተመሳሳይ ነው፡፡ አስር ሺ የሴቶች ስልክ ቁጥር የያዘ ማውጫ መጽሐፍ (ዳይሬክተሪ) ለማሳተም የአንዲት ሴት ስልክ ቁጥር ቢቀርህ እንኳን አንዷን ስልክ ቁጥር ለማሟላት ወደ አዲስ ሴት ስትራመድ ልብህ ድው ድው ማለቱ አይቀርም፡፡ ከአውሮፕላን ስትዘል የሚያስፈራህ የመከስከስ አደጋ ሲሆን ከሴት ልጅ ስልክ ቁጥር ለመቀበል ስትራመድ የሚያስፈራህ ደግሞ “እምቢ ልትለኝ ትችላለች” የሚል ስጋት ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል?

1. ልብ በል… ጨዋታው ጣፍጦህ ተንከርፍፈህ እስክትሰለች ድረስ ካወራሃት፣ የመለማመጥ ስሜት ካሳየህ፣ ከተርበተበትክ ስልኳን የማግኘት እድልህ ከዜሮ እስከ እጅግ በጣም በጣም አነስተኛ ድረስ ይሆናል፡፡

2. ደስ የምትልህን ሴት ቀርበህ ማነጋገር፣ መተዋወቅና ስልክ ቁጥር መቀበል ወደ ጦር ሜዳ እንደመዝመት አድርገህ አትየው፡፡ ቀለል አድገው፡፤

3. አያቶቸህ ምናልባት ወላጆችህ የሞባይል ስልክ፣ የቴክስት፣ የኦንላይን ዴቲንግ፣ የፌስቡክና የትዊተር ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ጊዜ ተዋውቀው ተቀጣጥረው ተፋቅረው መርፌና ክር ሆነው አንተን ወልደዋል፡፡ አንተ በዚህ ሁሉ የዘመኑ ቴክኖሎጂ እየታገዝክ የህይወትህ ውበትና ጣዕም የምትሆን ሴት እንዴት ማግኘት ያቅትሃል? በል ተንቀሳቀስ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
817 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
22 sept 2022
​​ ጣፋጭ የፍቅር አገላለፅ

ውዴ ልብሽ እስር ቤት ቢሆንና የእድሜ ልክ  እስራት ቢፈረድብኝ ምን ያህል ደስተኛ እሆን ነበር ታቂያለሽ ሺ ሆህያት ቢፈጠሩ ሽ ቃላት ቢሰደሩ አንቺነትሽን የሚገልፅቃል አጣሁ፡፡ ብቻ ያንን ቃል እስከማገኝ ዝም ብየ ልውደድሽ፡፡ አ ፈ ቅ ር ሻ ለ ሁ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
7.7K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

Korduma kippuvad küsimused

Levinumad küsimused 💖የኔ ፍቅር 😘 kohta

💖የኔ ፍቅር 😘 on Telegrami kanal, millel on 8.58K tellijat. Sellel lehel saate lugeda viimaseid postitusi, vaadata arvustusi ja üksikasjalikku statistikat.
Klõpsake sellel lehel nuppu „Mine kanalile" või otsige @yenefekir Telegrami rakenduses. Samuti saate kanali kasutajanime kopeerida ja Telegrami otsinguribale kleepida.
Jah, 💖የኔ ፍቅር 😘 on tasuta Telegrami kanal. Saate tellida ja lugeda kõiki postitusi tasuta.
Kanalil 💖የኔ ፍቅር 😘 on praegu 8.58K tellijat. Tellijate arvu uuendatakse regulaarselt.
💖የኔ ፍቅር 😘 avaldab sisu peamiselt አማርኛ keeles. Saate viimaseid sõnumeid sellel lehel eelvaadata.
Jah, sarnaseid ብሎጎች kanaleid leiate allpool jaotisest „Sarnased kanalid". Näitame ka seotud Telegrami gruppe, botte ja kleebiseid.
Saate sellel lehel kontrollida kasutajate arvustusi ja hinnanguid. Kanali hinnang on 3.5 5-st, mis põhineb 2 arvustusel.
Jah, saate 💖የኔ ፍቅር 😘 viimaseid sõnumeid eelvaadata siin Telegram Store'is ilma kanalit Telegramis tellimata.
💖የኔ ፍቅር 😘 avatar
💖የኔ ፍቅር 😘 @yenefekir
Ava Telegramis