Get Mystery Box with random crypto!

አጭር የፍቅር ታሪክ (ካነበብኩት) እሷ= ናፍቀህኛል!? እሱ= ኧረ ባክሽ? እሷ= የምሬን | 💖የኔ ፍቅር 😘

አጭር የፍቅር ታሪክ (ካነበብኩት)


እሷ= ናፍቀህኛል!?

እሱ= ኧረ ባክሽ?

እሷ= የምሬን ነው!

እሱ= እሽ።

እሷ= ይቅርታ..?

እሱ= ለምኑ?

እሷ= እኔ ጋር ለመቅረብ በጣም ጥረት ስታደርግ
ስለዘጋዉህ…

እሱ=ችግር የለዉም… ከጊዜ ጋር ለመድኩት…እናም ደከመኝ… መሞከሬን ትቸ መርሳት ጀመርኩ…

እሷ= እኔ…እኔ…ስለ አንት አለማሰብ ሞክሬ ነበር…እና…አብረን ልንሆን…

እሱ= ችግር የለዉም!

እሷ= ማለት?

እሱ= ለምጀዋለሁ..አንድ ቀን ወደኔ ትመጫለሽ እያልኩ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን አልመጣሽም ነበር እና እኔ እዉነቱን መጋፈጥ ጀመርኩ…እና ወደፊት መራመድ እንዳለብኝ አመንኩ…

እሷ= ቆይ…እና በጣም ረፍዶብኛል?

እሱ= ለምኑ ነው በጣም የረፈደብሽ?

እሷ= ካንተ ጋር ለመሆን..?

እሱ= ታዉቂያለሽ? ይህን ካንች መስማት እፈልግ ነበር ግን ከአመት በፊት ነበር…በተስፋ አንችን ስመኝ… ግን ሊሆን እንደማይችል ተረዳሁ ከዛ ተስፋ ማድረጌን መመኘቴን አቆምኩ…

እሷ= በጣም ይቅርታ… አትጨነቅ… አሁን ግን ምኞትን ሁሉ አሳካልሃለው:)

እሱ= ያ ሊሆን እማይችል ነው… ሌላ ሰው በሂወቴ ገብቷል…

እሷ= ላንተ ጥሩ ነው…ማን ናት? መቼስ ነው እምገናኛት?

እሱ= መቼም ቢሆን ልታገኝሽ አትፈልግም!!

እሷ= ለምን? ምን አድርጊያት አለሁ?

እሱ= በቃ ልታይሽ አትፈልግም!

እሷ= ቆይ እሽ ለምን?

ልጁም ቀስብሎ መለሰላት…

እሱ= በቃ በጣም የጎዳችኝን ሴት ልታገኛት አትፈልግም…
አሁን ይቅርታ ማያው ተራው የኔ ነው… ጊዜ በኔ ላይ ስለሆነ…ልቤን ሲጀመር ሰብረሽዋል እና ያን ድጋሚ ማሳለፍ ፣ ልቤን አደጋ ላይ መጣል አልችልም… ለማንኛዉም አመሰግናለሁ… ከአመታት ዝምታ በኋላ ስላናገርሽኝ…።

እሷም አንገቷን ደፍታ በዝምታ ሄደች

ከሄደች በኋላ እሱም ከዋሌቱ የነበረዉን የሷን ፎቶ አዉጥቶ አነባ
እናም ፎቶዉን ወደአፉ ጠጋ አርጎ
"አሁንም አንች ነሽ" አለ።


ልጁ ያልተቀበላትም የካንሰር በሽታ እንዳለበት እና በሁለት ወራት ዉስጥ እንደሚሞት ስለተነገረው ነበር።



ተፈፀመ


በዚች አለም ትልቁ እና ዋጋ ያለው ነገር ጊዜ ነው! ለዝች አለም ሁላችንም እንግዶች ነን መቼ እና እንዴት እንደምንሞት አናዉቅም! ስለዚህ በቻለነው መጠን ጊዜችን በአግባቡ እንጠቀም ልቦናችንን እንክፈት…በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል!!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir