Get Mystery Box with random crypto!

💖የኔ ፍቅር 😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.94K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-07 21:54:51
#Fekir_1K278

የኔ ማር ያንቺን ፍቅር ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል ye ጋና ባሃል ላኔ እና ላንቺ የመጀመሪያ በሃላችን እንዴ ሆነ ሁሉ እስከ ህዎቴ ፍፃሜ ካንቺ ጋር ለመሆን በምወዳት እናቴ ስም ቃል እገባልሻለዉ አንቺ ማለት የልቤ ንግስት ነሽ ላታሺም እንዲታጭኝም አልፈልግም... በጣም አፈቅርሻለሁ እሺ...
Ke ቡራክ
Le ሰና

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
441 viewsedited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 19:10:40
#Fekir_1K277

#Yene fikir fexari anchin silesexey ameseginalew hulem hulem kelibe afekrishalew @@ hulem bexewat sinesa inde maleda tsehay yemitaberi birhane mesh gene fikir neffffffffffff amet nuriliy kiya made gene bite binageer qal aygeltsewim silezih zim biyee liwdedishhhh
Ke. She.
Le.Kal

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
758 viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 17:24:52
#Fekir_1K276

Yene leyu yene merx ante malet lene fetari yesetegni tsega neh fetari kante ga eskezelalem endianoregni etseleyalew bexam ewedehalew yene hiwet melkam yeledet Ken yehunelehi ewedhalew

Ke mesi
le nati

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
873 viewsedited  14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 07:29:04
#Fekir_1K275

enateye endet endemafekereshe lemeneger betammm yekebedegnale fekeren salenager bezu gizeyatn asalefiyalehu ahun gn fetari yemesegen yene honeshale enem richye mechem kanchi teleyecha menoren alasebewem ema temut ena yene tefekari hulem afekereshalew hulem yanchiw negn eshi yelebe negest

ke.. D
le... R

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
726 viewsedited  04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 18:53:02 አትውቀሷት
እኔ ችለዋለው የሆንኩትን ልሁን:
ይቅር ማዘናቹ አትውቀሷት እሷን፡
ብትሆንም ምክንያት እንዲህ ለመሆኔ፡
ሁሉን እረስቼ ከሷ ቢቀር አይኔ፡
ትቼው የኔን መማር ደጇ ስመላለስ፡
አጅቤ ወስጃት አጅቤ ስመልስ፡
ሰው አይኔ ባይገባ ከሷ አልመጥን ብሎ፡
ልቤም ሄዶ ቢቀር እሷን ተከትሎ፡
ብቻዬን ባወራ ያለች ጎኔ መስሎኝ፡


ያሰብኩት ቢጠፋኝ ቀልቤ ከኔ ርቆኝ፡
ብጓዝ በለሊቱ በማረፊያው ሰአት፡
ብቀመጥ ከሳቱ ከማብሰያው ማጀት፡
ብተኛ አባይ ላይ ብሮጥ ከሰማዩ፡
ደመናንም ባቅፈው ወጥቼ ከላዩ፡
ማይሆነውን ባረግ ያልሆንኩትን ብሆን፡
እኔው ችለዋለው አትውቀሷት እሷን፡
አናቴ ቢናውዝ በፍቅሯ ተነክቶ፡
እርቃኔንም ብሆን ልብስ ከኔ ወልቆ፡
የጫቱን ገራባ ሀይላንዱንም ይዤ፡
ብታዩኝ አብጄ በፍቅሯ ደንዝዤ፡
በሷ ነው ብላቹ ስሟን እንዳጠሯት፡
እኔ ምንም ልሁን ውዴን አትውቀሷት፡፡

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
262 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 14:01:10 መልካም መኞት መግለጫ

የኔ ውድ ጓደኛዬ
የኔ ሁሉ ነገር
አንተን/ቺን/ በመተዋወቄ በጣም ደስተኛ ነኝ
የዘንድሮው የ ገና በዓል
የደስታ
የጤና
የብልጽግና
መልካም ነገሮች ሁሉ ወዳንተ/ቺ/ ሚመጡበት
ስኬታማ ምትሆንበት/ኝበት/
ይሁንልክ/ሽ/



ይህን የመልካም ምኞት መግለጫ ለሚወዱት ሰው ሁሉ ያካፈሉ ከነዛ ሠዎች መሃል እኔ አንዱ ከሆንኩ forward ማድረግ ይቻላል
ምኞቱን ከላክላቸው/ሽላቸው/ ሰዎች =
ዕሩቡን መለሰክ/ሽ/ ካገኘህ/ሽ/
ግማሹን " "
ሙሉውን " " በጣም እድለኛ ሰው ነህ/ሽ/

መልካም እድል

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
822 views11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 18:53:02 ፍቅሬን_ተረጀልኝ

ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ
በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ
ፈሪ ነህ ተብየ በሀሰት ስሰደብ
በቃላቶች ጅረት እውነቴ ሲታጠብ
:
አደዩ ልብሽን በቃላት ባልቀስመው
ጠላት ምቀኛሽን በነገር ባልነድፈው
ቃሌ ባያረካሽ ውስጥሽን ባይነካው
ዝምታየ ጥልቅ ነው ማንም ያተረዳው
:
የቃላት ጥርቅም የሀገሬ ስብጥር
የዓንቀፅ ጋጋታ የድርሰቶች ክምር
ፍቅርን ላያፀና በቃል ለሚሰበር
ዝምታ ሀቅ ነው ምንም የማይበገር
:
ልብሽን ባገኘው በቃላት ደልየ
የሞተ አስነስቼ ያለውን ገድየ
ልብሽ ላይ ከምሰፍር ውስጤን አታልየ
መኖር ይሻለኛል እራሴን በድየ
:
ግን ልብሽ ጆሮ ሁኖ ውስጤን አድምጠሽው
የዝምታ ገዳሜን ቆርበሽ ጎብኝተሽው
የልቤ ኪዳኑን በልብሽ ከትበሽው
ፍቅሬ ላይ ኮብልይ ሀቄን ተረድተሽው






           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
789 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 18:52:02 #ከንፈርሽ ነው የግሌ



አንቺ ስታለቅሺ ከአይኖችሽ መሀል
እንባ ስታቀሪ እኔን ሆድ ከባሰኝ፤

የእንባሽ ዘለላ ጉንጭሽን ሲነካው
አንቺንም አልፎ እኔንም ካስለቀሰኝ፤

ከንፈርሽ ጋር ሲደርስ እብደት ይሰማኛል፤

ፍቅሬ እሱን ከኔ ውጪ ሲነኩት ያመኛል።

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
216 views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 19:52:01 በወጣትነት ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች:-
=====================
በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች በጋብቻ ህይወታቸው ከሌሎቹ ይልቅ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገቡ ወንዶች ካላገቡ ወንዶች ይልቅ ሃብት የማፍራት ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ ያገቡ ወንዶች ገቢና ሃብት እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ለጤንነት አስጊ ለሆኑ ነገሮች የመጋለጥ ዕድል ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ በወጣትነታቸው ወቅት ያገቡ ወንዶችና ሴቶች ጤንነታቸውን ጠብቀው የመኖር መልካም አጋጣሚዎችን ያገኛሉ፡፡

በወጣትነት (20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ) የሚያገቡ ጥንዶች መልካም የወሲብ ህይወት ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ የትኩስ ወጣትነት ጊዜ ወሲብን ሁልጊዜ የማግኘትና በፍቅር ውስጥ ሆነው የመለማመድ ዕድል አላቸው፡፡ ዕድሜ ሲጨምር የሰውነት ኃይልም እየቀነሰ ስለሚሄድ እንደ ትኩስ የወጣትነት ጊዜ ወሲብን የመለማመድ ዕድሉ ይቀንሳል፡፡

ጥንዶቹ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች (ከተቃራኒ ጾታ ጋር ባለው የግንኙነት መፍረስ) ህይወታቸው ሳይቆስል ወደ ጋብቻ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ግንኙነቶች ወደ ጋብቻ ይዘው የሚመጡት ‹‹ኮተት›› ላይኖር ይችላል፡፡

አንዱ ሌላውን የመቅረጽ ዕድሉ ይሰፋል፡፡ በዚህ የወጣትነት ጊዜ ሁለቱም ተሰርተው ስላላለቁ፣ ይቀራረጻሉ፣ በረጅም ርቀት መልካም ጓደኛሞች ይሆናሉ፡፡

ጤናማ ልጆችን በጊዜ ወልዶ በጊዜ ለማሳደግ መልካም ዕድል ይፈጥራል፡፡ ዕድሜ ከገፋ በኋላ ልጆችን መውለድ የሚቻል ቢሆንም ወላጆች ልጆቹን ለማሳደግ የሚኖራቸው ጉልበት ይቀንሳል፡፡ በወላጆችና በልጆች መካከል የዕድሜ መራራቅም የትውልድ ክፍተትን በጣም ይፈጥራል፡፡

ወጣቶች ጊዜውን ካላወቁስ?
====
አንዳንድ ጊዜ ወጣቶች ተገቢ በሚባለው ዕድሜ ወደ ጋብቻ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ ለዚህ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ይኖራሉ (ወደፊት በሌላ ጽሑፍ ውስጥ እናያለን)፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ዙሪያ ያሉ ተገቢ ሰዎች አንዳንድ በጎ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፡፡
• ግንዛቤን መፍጠር፡ ወጣቶች በተገቢ ዕድሜ ወደ ጋብቻ እንዲገቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማስተማር ወይም ትምህርት የሚያገኙበትን መንገዶች መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡ ልጆች ወደ ታዳጊ ወጣትነት ዕድሜ ክልል ሲገቡ ከህይወት ክህሎት ስልጠና ጋር በማያያዝ ስለጋብቻና መቼ ወደ ጋብቻ መግባት እንደሚቻል ትክክለኛ የሆነ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
• ማንቃት፡ አንዳንድ ወጣቶች በሌሎች የህይወት ተግባራት ከመጠመድ ወይም እንዲሁ አሁን ያሉበት ኑሮ ስለተመቻቸው ዕድሜያቸው እየሄደ መሆኑን አያስተውሉም፤ ስለወደፊትም እምብዛም አያስቡም፡፡ ስለዚህ ወላጆች፣ ወንድሞች፣ እህቶች፣ ጓደኞች ወይም መንፈሳዊ አገልጋዮች ሊያነቁአቸው ይገባል፡፡ ይህ የማንቃት ስራ በተለያዩ መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ስለጋብቻ በማንሳት መነጋገር፣ መምከር ወይም ታሪኮችን በማውራት ወይም መጽሐፍ እንዲያነቡ በመስጠት ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች ከዚህ ከተኙበት ሁኔታ ሲባንኑ፣ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በመውሰድ ህይወታቸውን በሚጎዳ ግንኙነት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በስብዕናቸው ንቁ ያልሆኑ፣ በዓላማና በዕቅድ የማይመሩ፣ ስለወደፊት ከማሰብ ይልቅ በዕለታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ወጣቶች ደውል በመደወል የሚያነቃቸውን ሰው ይፈልጋሉ፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
850 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 19:51:01 7 የፍቅር ማጣፈጫ ቅመሞች
==============
የበርካታ ጥንዶች ልምድ እንደሚያሳየው ፆታዊ ፍቅር መጀመሪያ በነበረው ግለት እስከመጨረሻው ላይዘልቅ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሁሌም ቢሆን በፍቅራችን መካከል የተወሰኑ ማጣፈጫ ቅመሞችን ጣል በማድረግ አስደሳችና ጤናማ የፍቅር ህይወት እንዲኖረን ማድርግ እንደምንችል የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

1. ተንከባከባት
====
የትኛዋም ሴት ብትሆን ከወንድ ልጅ የሚደረግላትን እንክብካቤ አትጠላውም፡፡ ዓይን አፋር ሴት ደግሞ በማፈሯ የተነሳ ከብዙ ሰዎች የመራቅ ዝንባሌዋ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አንተ ፍፁም የሆነ እንክብካቤ ልታደርግላት ይገባል፡፡ እንክብካቤ እያደረክላት ስትመጣ ለካ ወንድ ልጅ እንዲህ ያስብልኛል ልትል ሁሉ ትችላለች፡፡ በዚህም የመጀመሪያውን ጥያቄ በውስጧ ማሰላሰል ትጀምራለች፡፡ ይህ ደግሞ በቀጣይነት ለምታደርገው ነገሮችህ የልቤን መንገድ አስቀድመህ የምታንኳኳበት ይሆናል፡፡ ስለ እሷ ባሰብክና በተጨነቅላት ቁጥር ምንም ይሁን ምን ስለአንተ ሁኔታ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ የፍቅርን ምንነት በአንተ እንክብካቤ መነሻነት እንድታውቀው ያስገድዳታል፡፡ ስለዚህም አንተን ፈጽሞ የማትለይበት አይነት እንክብካቤ አድርግላት፡፡

2. ስለ ሌሎች ሰዎች የፍቅር ህይወት አጫውታት
====
ዓይን አፋር ሴት ራሷን ከብዙ ነገር እንደማራቋ መጠን ከፍቅር ጋር ያላት ግንዛቤም የቀነሰና ጥሩ አመለካከት ላይኖራት ስለሚችል ስለ ፍቅር ምንነት በቀልድና በጨዋታ እያዋዛህ ለማሳወቅ ሞክር፡፡ በተለይም ነጻና ዘና የምትልበትን ጊዜ ጠብቀህ የተለያዩ ሰዎችን የፍቅር ታሪክና አስደሳች የፍቅር ህይወታቸውን አጫውታት፡፡ እዚህ ጋር በቃ አንተ ፍፁም የፍቅር አስተማሪዋ እንደሆንክ መንገዶችን አመቻች፡፡ ከዚህ በፊት የነበራትንም ህይወት ለማወቅ በቀስታ እያወጣጣሀት ታሪኳን ለማወቅ ሞክር፡፡

3. ደስ የሚል ጊዜን አብራችሁ ለማሳለፍ ሞክር
===
የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ወጣ ባለ መልኩ ከእሷ ጋር መዝናናትና መደሰትን ተግብረው፡፡ በእያንዳንዷ አስደሳች የመዝናኛ ሰዓቶቹ አንተ አፍ አውጥተህ ከምትናገረው ይልቅ የውስጥህን ምኞት ነገሮችህና እንቅስቃሴዎችህ እንዲያሳውቃት አድርግ፡፡ አስደሳች ጊዜን እያሳለፋችሁ ስትመጡ ዓይን አፋርነቷን እየተወችው ስለ አንተ ፍቅር አቀራረብ ማሰብ ትጀምራለች፡፡ ስለዚህም ባገኘኸው አጋጣሚ ይህን ለመተግበር የእሷን አመቺ ጊዜ ልትጠብቅ ይገባሃል፡፡

4. የሚያስደምሙ ስጦታዎችን አበርክትላት
===
ከአንተ ጋር ያለች ሴት ዓይን አፋርና ለወንድ ልጅ በፍቅር በቀላሉ የማትሸነፍ ከሆነች በጣም የሚማርኩ ስጦታዎችን በተለይም የተለያዩ በዓላትንና የልደቷ ቀንን ጠብቀህ ስጣት፡፡ ስጦታዎችህ በራሳቸው የውስጥህን ፍላጎት የሚናገሩልህ አድርገህ ምረጣቸው፡፡ ስትመርጣቸው ግን የእሷንም ፍላጎት የጠበቀና በጣም ሊያስደስታትና በመደምም ሌላ ነገር እንድታስብ የሚያደርጋት ይሁን፡፡ ታዲያ ስጦታዎችህን መሳሪያ አድርገህ በውለታ ፍቅሯን ለማግኘት እንዳይሆን ተጠንቀቅ፡፡ ይልቁንስ ስጦታዎችህ የውስጥህን ስሜትና ፍላጎት ከማሳወቅና የመልካም ነገር አቅርቦትህ ብቻ እንዲሆኑ ልታውቅም ልታሳውቃትም ይገባል፡፡ ያኔ የአንተን ማንነት የበለጠ ትረዳለች፡፡ ሳትወድ በግዷም ዓይን አፋርነቷ የበለጠ ሊጎዳት ስለሚችል ያንተን ዕድል ልታሳልፍ አትችልም፡፡

5. የጓደኛነት አቀራረብህን ቀይርባት
===
እሷን ከማወቅህ ጀምሮ ያሉ አቀራረቦችህን የጓደኝነት ወይም ደግሞ የወንድምነት መምሰሉ እየበዛ ሲመጣ አንተን እየጎዳህ ስለሚመጣ ጊዜውንና አመቺ ሁኔታዎችን አይተህ ወደ ፍቅር ፈላጊነት ራስህን ልትቀይርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ከአንተ ስለ ፍቅር ምንነት እንደዚሁ በመቅረብህ ብቻ እያገኘች እንጂ በአንተ ልብ ውስጥ ፍቅር መፈለጓን በደንብ ላትገነዘበው ትችላለች፡፡ ምክንያቱም የዓይን አፋር ሴቶች መገለጫ ነውና፡፡ ልቧን በማትጠብቀው ሁኔታ ፍፁም በፍቅር አስደንብረው፡፡ በፍቅር የደነበረ ልብ ደግሞ ልጓሙና መያዣው በአንተ እጅ ውስጥ እንዲሆን አድርገው፡፡

6. ፍፁም አማላይ ሁንባት
===
የተለያዩ የፍቅር መግቢያ ቴክኒኮችን እየተጠቀምክ በመጣህ ቁጥር አንተ የፍቅር አማላይነትም አብሮ የሚታይ ነው፡፡ ነገር ግን ራሱን በቻለ መልኩ አማላይነትህ በየጊዜው እንዲታያት አድርግ፡፡ የፈለገ ዓይን አፋር ብትሆንም እንኳን የአንተ የአማላይነት አቀራረብህ ውስጡን ሊገዛው ይችላል፡፡ አንተ ያለምንም ፍራቻ በቀረበችህ ሰዓት ደባብሳት፣ እጇን ጭምቅ እያደረግክ ያዛት፣ አሳሳሞችህ ደስ የሚላትና የምትናፍቀው አይነት አድርግባት፣ እያቀፍካት ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ እየሳምካት ፍቅር ውስጥ ክተታት፡፡ ነገር ግን አሁንም የዓይን አፋርነቷ ባህርይ ስለሚታወሳት ፀባይዋ ሊለዋወጥ ስለሚችል ሰው በተሰበሰበበት ልትስማትም ሆነ ልታቅፋት አትሞክር፡፡ ቀስ በቀስ ግን የምታደርጉት ነገር ምንም እንዳልሆነ በራስ መተማመንም እንድታዳብር አድርጋት፡፡ ይህን መፈፀም ከቻልክ ልቧ ውስጥ ትልቅ ፍቅር ማስቀመጥ ተችላለህ፡፡

7. በፍቅርህ ክንፍ እንድትል አድርግ
===
ከላይ ያሉትን ሁሉ ከተገበርካቸው አንተ በቃ የፍቅር ሰው ነህና ፍቅር መስጠት ተችላለህ፡፡ ታዲያ ፍቅርህን ስትሰጣት እሷንም በአንተ ፍቅር ክንፍ እንድትል አድርጋት፡፡ በፍቅር የነካካኸውና የቆሰቆስከውን ልቧን መጋረጃና ማረፊያው አንተው ጋር እንዲሆን አድርግክ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ታዲያ የምን ማፈር ማለት ትጀምራለች፡፡ ምክንያቱም በአንተ የፍቅር ሰው መሆን አይን አፋርነቷን ገልጠህላታልና አንተ የእኔ “የፍቅር ላምባዲናዬ” ነህ ማለት ትጀምራለች፡፡ ከዚህ በኋላ ድንቅ የፍቅር ሽሚያ ውስጥ ታስገባትና እሷው ፍቅር ላስተምርህ ሁሉ ማለት ትጀምራለች፡፡ ፍቅራችሁም በምሽት እንደጨረቃና ከዋክብት በቀን ደግሞ እንደ ፀሐይ እየበራ ይታያቸዋል፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
392 views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ