Get Mystery Box with random crypto!

💖የኔ ፍቅር 😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘 የ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.94K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-12-18 21:48:37
#Fekir_1K268

Yene feqer anchin lemglst qaltoch yansunyal becha anchi malet lene lek endnat kestete metmlshny lek end ehet mekriye becha bacru lek ende semesh hiwete nesh feqer endanchi bayhonem ewdshalew ema becha fexari yenenm edeme cemro yesxash endi sel men asbo new letyi techyalesh enko kanchi befit menoren guguchat alqem yane tesfa beqorxkubet seat anchi nebersh menorn yastmrshny ema anchin bemdan wesex rasen adnkut tadya lanchi yihe yanseshal aynsem ema bedesta seqesh nurilngn feqern ke qalem belay lasyesh eflglew guagualhum cemer enat beqa zem beye ewdshalew feqer lanchi new

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
771 viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 19:39:02


           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
264 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 11:22:03 ከፍቅረኛዎ ጋር ምን ያክል ሰዓት በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ያሳልፋሉ:-
============
እስኪ ይህን ጥያቄ ለራስዎ ይመልሱ፣ ከፍቅረኛዎ ጋር ምን ያክል ሰዓት በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ያሳልፋሉ? በርግጥ መልሱን እኛም መገመት እንችላለን፡፡ በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አብረው የሚኖሩ ጥንዶች በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ በቀን በአማካኝ የሚያሳልት ጊዜ 4 ሰዓታትን ብቻ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በአጠቃላይ ደግሞ አብረው የሚያሳልፉት ጊዜ ሲሰላ ወደ 7ተኩል ገደማ እንደሆነ በጥናቱ ላይ ተያይዞ ተጠቅሷል፡፡

ምንም እንኳን ጥንዶቹ በአንድ ጣሪያ ውስጥ ቢኖሩም የተለያየ የእንቅልፍ ጊዜ፣ የተለያዩ የስራ ሰዓቶች እንዲሁም የጥቅም ግጭቶች ስላሏቸው አብረው እየኖሩ እንኳን ሰፊ ጊዜያቸውን ተለያይተው እንዲያሳልፉ ሳያስገድዷቸው አልቀሩም፡፡ ጥናቱ አያይዞም ጥንዶች በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ሲሆኑ ሊጨቃጨቁባቸው የሚችሉባቸውን ርዕሶች ሁሉ አስፍሯል፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች መካክል ማን በየትኛው የሶፋው መቀመጫ መቀመጥ እንዳለበት፣ የክፍሉን ሙቀትና የሚስፈልገውን የብርሃን መጠን ማን እንደሚወስን በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

እንደ ስነልቦና ባለሙያውች ገለጻ ግንኙነትዎ ጤናማ እና ጠንካራ እንደሆነ ለማረጋገጥ ከፍቅረኛዎ ጋር ብዙና ምርጥ ጊዜ አብራችሁ ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡ ጥቂት ምክሮች፣

ምልክቶቹን ይወቁ
====
በመጀመሪያ ለምን አሪፍ ጊዜ አብራችሁ እንደማታሳልፉ የሚያሳዩ ምልክቶችን ይለዩ፡፡ እነዚህን ምልክቶች በተደጋጋሚ ከአስተዋሉ ግንኙነትዎ መሻሻል እንደሚፈልግ ሊረዱ ይገባል፡፡
• ስልክዎ ላይ የበለጠ ጊዜ ያጠፋሉ ጊዜዎን ከፍቅረኛው ይልቅ ከጓደኞችዎ ጋር ማሳለፍን ይመርጣሉ
• ብዙ ጊዜ ትጨቃጨቃላችሁ
• ለእራት አልያም ማኪያቶ ለመጠጣት ወደ ውጭ መውጣት አቁማችኋል

አዳዲስ ነገሮች በጋራ ሞክሩ
====
እስኪ እንደ ዳንስ፣ ጂም ቤት መሄድ፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መማር የመሳሰሉ አንዳንድ አዳዲስ ነገሮችን አብራችሁ ለማድረግ ሞክሩ፡፡ ይህ አሪፍ ጊዜ ለማሳለፍ ምርጡ መንገድ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነት ድርጊቶች ጥንዶች አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ያላችን ስሜታዊና አካላዊ ድፎች ያጠናክራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ግንኙነቱን በጊዜ ሂደት እያጠናከረው ይሄዳል ማለት ነው፡፡

የቴክኖሎጂ ጣልቃገብነትን ያስወግዱ
=====
ስልክዎ በእርስዎና በአጋርዎ መካከል እንደማይባ ያረጋግጡ፡፡ ብቻዎትን ሲሆኑ የሚወዷቸውን ሙዚቃዎች ማድመጥ፣ የሚፈልጉትን ፊልም መመልከት ስለሚችሉ ይህን ድርጊት አጋርዎ በአቅራቢያዎ በሚኖሩበት ጊዜ ከማድረግ ይቆጠቡ፡፡ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ በሚሆኑበት ወቅት ሙሉ ትኩረትዎን ለአጋርዎ ይስጡ፡፡

ምግብ አብረው ያብስሉ
=====
በጋራ ምግብ ማብሰል ምርጥ ጊዜ ለማሳለፍ እጅግ ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ ምግብ በምታበስሉበት ወቅት ወይን በመጠጣት አልያም አንዳች ሙዚቃ በመጨዋት ጊዜውን አስደሳችና ተናፋቂ ማድረግ ይችላሉ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
690 views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 18:38:01 #የኔ_ዉድ

የመጀመሪያ ቀን አንችን ያየሁኝ 'ለት
ደርቄ ቀረሁኝ ቆምኩኝ ባለሁበት
ከዛች ቀን በኋላ አፍቃሪሽ ሆንኩልሽ ሳላውቅሽ ተሸነፍኩ ገና ሳልጠይቅሽ
ያሸነፍሽኝ አንች በኔ ልብ ተቀምጠሽ
ሳልሰማው መልስሽን እላለሁ የኔ ነሽ
ያንች ልብ ማለት የራሴ ነው ብዬ
ልብሽን በልቤ በሚገባ ስዬ
ልብሽን ወስጄ እኔ ውስጥ ከትቸ
የኔን ምላሽ ሰጠሁ ያንችን ልብ ተክቸ
ከዛ በኋላማ ሳላፍር ስላንቸ ብዙ አወራለሁ
አንችን ሳላሞግስ መቼ ውየ አድራለሁ
ጠዋት ማታ ሁሌም ስላንች አስባለሁ
ስላንች በድፍረት ሳወራ የሰሙኝ
የኔን መውደድ አይተዉ ስላንች ጠየቁኝ
ቆይ እስኪ ምንህ ናት? እያሉ አዋከቡኝ
የነሱ ጥያቄ ሲደጋገም ጊዜ ረፍት ስለነሳኝ ያበጠው ይፈንዳ ምን ይመጣል ብየ
ፍቅሬን ተናገርኩኝ ''እሷ ማለት እኮ በፍቅሬ የተረታች
ምንም የማትመኝ ከሰማዩ በታች
ከኔ ውጭ ወንድ ያለ የማይመስላት
በጣም የምትወደኝ በጣም የምወዳት
በቁንጅና ብዛት ጉድ የተባለላት
ሁሉም ሰው ለራሱ ከልብ የተመኛት
ከማንም ሰው በላይ የምታፈቅረኝ ናት
አልኳቸው በድፍረት የኔ ብቻ ሴት ናት
አደራ የኔ ውድ ይሄንን ስትሰሚ
ከቶም እንዳይከፋሽ እንዳትቀየሚ
የጠየቁኝ ሰወች መጥተው ከጠየቁሽ
ምንህ ናት እንዳሉኝ ምንሽ ነው?
ካሉሽ ያንችንም ጨምረሽ በያቸው በድፍረት
እሱ ማለት እኮ የተረታሁለት
ከምንም በላይ እኔ 'ምሳሳለት
ከሰማዩ በታች ምንም የማልመኝ
ከሱ ውጭ ወንድ ያለ የማይመስለኝ
በጣም የምወደው በጣም የሚወደኝ
እቅፍ ድግፍ አርጌ በእኔ ልቤ ያኖርኩኝ
እሱን ብቻ እኮ ነው ሁሌም እኔ ምመኝ
በያቸው ጨማምረሽ እንደምታፈቅሪኝ
ስላንች የነገርኳቸውን ደግመሽ ንገሪልኝ
አደራ የኔ ውድ እንዳታሳፍሪኝ
አደራ በኔ ሞት እንዳታሳፍሪኝ


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
1.2K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 17:37:01 በፍቅር መካከል ለሚከሰቱ ግጭቶች መፍትሄ
==============
አልፎ አልፎም ቢሆን ከፍቅረኛችን ጋር መጨቃጨቃችን ወይም መጣላታችን አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ በፍቅረኛችሁ መበሳጨቱም ሆነ መናደዱ፣ ጭቅጭቁን እንዴት ማስተናግድ እንዳለብን እስካወቅን ድረስ፣ የፍቅር ግንኙነቱን ሊንደው አይገባም፡፡

1. ሁለት አይነት ችግሮች መኖራቸውን መገንዘብ
====
ከፍቅረኛችን ጋር ባለን ግንኙነት ስንበሳጭ ወይም ስንናደድ አብዛኛውን ጊዜ ሁለት የተለያዩ ችግሮች ይኖራሉ፤ እነኚህም ችግሮች ስሜታችንና ችግሩ ራሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ ፍቅረኛሽ የተበላባቸውን ሳህኖች ባለማጠቡ ተበሳጭተሻል እንበል፡፡ ይህን ጊዜ መፍታት ያለብሽ ሁለት ችግሮች አሉ፤ ሳህኖቹ መታጠብ ያለባቸው ሲሆን፣ ፍቅረኛሽ ይህን ባለማድረጉ መበሳጨትሽንም ማቆም አለብሽ፡፡

በአብዛኞቹ ሌሎች የህይወት ዘርፎች ለችግሮችን ቅድም ተከተል በመስጠት በተናጠል ልንፈታቸው ይገባል፡፡ የፍቅር ግንኙነታችንን በተመለከተ የሚፈጠሩ ግጭቶችንም ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ ማስተናግዱ ተገቢ ይሆናል፡፡ ‹‹ስለ… ብለህ አንዴ እንኳን ሳህኖቹን ብታጥባቸው ምን አለበት?›› የሚለውን የመሰለ ጥያቄ ከመሰንዘራችን በፊት ውጤታማ ውይይቶችን አስቸጋሪ የማናደርግ ምክንያታዊ ሰው መሆናችንን ማረጋገጥ አለብን፡፡

በፍቅረኛችን ምግባር ወይም አድራጎት ተበሳጭተን ቅሬታችንን ከመግለፅ መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ፣ በመሳጨትና ንዴታችንን መግለፅ የተለመደ ነው፤ ምንም ነገር ሳናደርግ ያለማቋረጥ በችግሮቻችን ዙሪያ መቆዘሙ ግን ይበልጥ እንድንናደድ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ስሜታችን መፍትሄ የሚያስፈልገው ነገር እንደሆነና የጭቅጭቁ መንስኤ ከሆነው ጉዳይ የተለየ እንዲሆን መቀበሉ ወደ መፍትሄው የሚያቀርበን እርምጃ ነው፡፡

2. በቀዳሚነት ስሜታችንን ማስተናገድ ንዴት፣ መቆጣጠር በተመለከተ ማንኛችንም ብንሆን የምንረጋጋበት የየራሳችን መንገድ አለን፡፡
=====
ከፍቅረኛችን ጋር ለመጣላት ከደረሰን፣ ሁኔታው በውስጣችን የፈጠረውን ውጥረት ለማስተናግድ ፋታ ልናገኝ ይገባል፤ ሌላኛውም ወገን እንዲሁ በተመሳሳይ ሂደት በኩል ማለፍ ይኖርባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ውጥረት ለብቻ ማስተናገዱ የተሻለ ነው፤ ይሁንና፤ በአንዳንድ ስሜትን የሚነኩ ሁኔታዎች ባለንበት ቦታ ሆነን ለረዥም ጊዜ መተንፈሱ እገዛ ሊኖረው ይችላል፡፡ ለማንኛውም በውስጣችን የተፈጠረውን ውጥረቱን የሚያቃልሉ ነገሮችን እናድርግ፤ የእግር ጉዞ ማድረግ፤ ሞቅ ያለ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ አሊያም ንዴታችንን በወረቀት ላይ አስፍረን ቀድደን መጣል እንችላለን፡፡ ይህ አካሄድ የተሻለ ውጤት የሚያስገኘው ፍቅረኛችን ቀደም ብለው ውጥረትን በምን አይነት መንገድ እንደምናስተናግድ ካወቁ ነው፡፡ መቆናጠር፣ እንዲሁም ማጉረምረም የሌላኛውን ሰውን ስሜት በቀላሉ የሚጎዱ ናቸው፡፡ ራሳችንን በጭቅጭቅ መሃል ውስጥ ከማግኘታችን በፊት ፍቅረኛችን ንዴትን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱ ማወቅና ምን እንደምንፈልግ እንደሚያውቁ ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ እንዲያውም፣ ‹‹የፈለግሽውን…›› ከማለት ይልቅ፣ ‹‹የእግር ጉዞ ማድረግ አለብኝ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እናወራለን›› ማለቱ ይበልጥ ጠቃሚ ነው፡፡

ከሁሉም የበለጠ አንዴ ከተረጋጋን ወደነበርንበት ቦታ መመለሳችን ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፣ ጭቅጭቅ ሲፈጠር ሁለት የተለያዩ ችግሮችን እያስተናገድን ነው፡፡ መረጋጋቱ አንዱን ችግር ሲፈታ ሁሉም ነገር ከበፊቱ የተሻለ ነው የሚለው ስሜትም በቀላሉ ይከተላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ቀለል ቢሉልንም፣ ከፍቅረኛችን ጋር ያለን ችግር ችክ ያለ ከሆነ ስለተረጋጋን ብቻ ይጠፋል ማለት አይደለም፡፡

3. ከሄድንበት ስንመለስ ሁኔታውን ማስተናገድ አንዴ ከተረጋጋን ችግራችንን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መመልከት ልንጀምር እንችላለን፡፡
===
በመጀመሪያ ረገድ ሁኔታውን የምናስተናግድበት ጥሩና የተሻለ ስሜት ላይ እንገኛለን፡፡ ፍቅረኛሽ አድካሚ ቀን ካሳለፈ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የበላበትን ሳህን ባለማጠቡ መጨቃጨቁ ጥቅም የለውም፡፡ በሌላ በኩል፣ ምሽቱን አብራችሁ ሳታሳልፉ አስራ ሁለት ቀናት ካለፉ መነጋገሩ አይከፋም፡፡

ከፍቅረኛሽ ጋር ለመነጋገር ከሄድሽበት ቦታ ስትመለሺ ሁኔታዎችን በትብብር መንፈስ ተመልከቻቸው፡፡ በመካከላችሁ የተፈጠረውን ችግር አንዳችሁ ከሌላኛው አንፃር ከተመለከታችሁት፣ ደስተኛ የፍቅር ግንኙነት መመስረቱን ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ከስሜታችን ጋር የተያያዘ ብቻ ይሆናል፡፡ ‹‹እራት ስንበላ ሞባይል ስልክህን መነካካትህ ችላ የተባልኩ ሆኖ እንዲሰማኝ ያደርገኛል›› ማለቱ በቤት ውስጥ ስራ ሳቢያ የሚፈጠሩ ጭቅጭቆችን ያህል ምክንያታዊ ችግር ነው፡፡ ዋናው ነገር ጉዳዩን ሁለታችሁም ልትፈቱት የምትችሉት ነገር እንደሆነ አድርጎ መግለፁ ነው፡፡

በችግሩ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት እንዳበቃ እርምጃ መውሰዳችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል፡፡ የመግባባት ችሎታችሁ ጠቃሚ ከመሆኑም ሌላ፣ ከፍቅረኛችን ጋር የበለጠ መተሳሰርን ለመፍጠር ያግዛል፡፡ ሁኔታዎች እንደ በፊቱ ሆነው ካልተለወጡ ግን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያንኑ ንግግር መድገም ሊኖርባችሁ ነው፡፡ ሁለታችሁም መለወጥ ያለበት ነገር ምን እንደሆነ ከስምምነት ላይ ከደረሳችሁ፣ ጥሩ ልምዶችን ለማዳበር የምትጠቀሙባቸውን ስልቶች ተግባራዊ አድርጉ፡፡ ፍቅረኛሽ እንዲደመጥ የሚፈልገውን በተመለከተ ራስሽን ከማስታወስ አትቦዝኚ፡፡ በማስታወስ ችሎታሽ ላይ ብቻ አትተማመኚ፡፡

4. መታረቅ
====
ተናድደን ነበር፡፡ በቀጣይነት ከተረጋጋን በኋላ በችግሩ ዙሪያ ከተወያየን በኋላ መለወጥ ስላለበት ነገር እቅድ እናወጣለን፡፡ ይህን ጊዜ ነገሮች ጥሩ መስለው ይታዩናል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ጥሩም ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ሂደቱን እዚህ ላይ አቁመን እጆቻችንን አጣጥፈን ብንቀመጥ እርስ በርስ መጯጯኹ ምን እንደፈየድልን በቅጡ ለመረዳት እንቸገር ይሆናል፡፡ ስለዚህም፣ ሂደቱ የዘወትር ልማድ መሆኑን ለማረጋገጥ ራሳችንን እንሸልም፡፡

መተቃቀፍ፣ ፊልም ማየት፣ አሊያም ወሲብ መፈፀም ጭቅጭቁን በጥሩ መንፈስ ከፍፃሜ እንዲደርስ የሚያግዙ አዎንታዊ ዘዴዎች ናቸው፤ ይሁንና፤ ችግሩ መፍትሄ ሳያገኝ ወሲብ መፈፀም የፍቅር ግንኙነቱን አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ የፍቅረኛችን ከአጠገባችን መኖር ያስደስተናል፡፡ ሁለቱም ወገኖች በጉዳዩ ዙሪያ ጤናማ ውይይት ካካሄዱ፣ አብረው የተወሰነ ጊዜ ማሳለፍ ይኖርባቸዋል፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
652 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 13:34:02 #ሀኪሜን_አትውቀሷት
እኔ ችለዋለው የሆንኩትን ልሁን:
ይቅር ማዘናቹ አትውቀሷት እሷን፡
ብትሆንም ምክንያት እንዲህ ለመሆኔ፡
ሁሉን እረስቼ ከሷ ቢቀር አይኔ፡
ትቼው የኔን መማር ደጇ ስመላለስ፡
አጅቤ ወስጃት አጅቤ ስመልስ፡
ሰው አይኔ ባይገባ ከሷ አልመጥን ብሎ፡
ልቤም ሄዶ ቢቀር እሷን ተከትሎ፡
ብቻዬን ባወራ ያለች ጎኔ መስሎኝ፡


ያሰብኩት ቢጠፋኝ ቀልቤ ከኔ ርቆኝ፡
ብጓዝ በለሊቱ በማረፊያው ሰአት፡
ብቀመጥ ከሳቱ ከማብሰያው ማጀት፡
ብተኛ አባይ ላይ ብሮጥ ከሰማዩ፡
ደመናንም ባቅፈው ወጥቼ ከላዩ፡
ማይሆነውን ባረግ ያልሆንኩትን ብሆን፡
እኔው ችለዋለው አትውቀሷት እሷን፡
አናቴ ቢናውዝ በፍቅሯ ተነክቶ፡
እርቃኔንም ብሆን ልብስ ከኔ ወልቆ፡
የጫቱን ገራባ ሀይላንዱንም ይዤ፡
ብታዩኝ አብጄ በፍቅሯ ደንዝዤ፡
በሷ ነው ብላቹ ስሟን እንዳጠሯት፡
እኔ ምንም ልሁን ውዴን አትውቀሷት፡፡
ሀኪሜ ናት እና

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
984 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 17:33:02 #የኔ_ዉድ

የመጀመሪያ ቀን አንችን ያየሁኝ 'ለት
ደርቄ ቀረሁኝ ቆምኩኝ ባለሁበት
ከዛች ቀን በኋላ አፍቃሪሽ ሆንኩልሽ ሳላውቅሽ ተሸነፍኩ ገና ሳልጠይቅሽ
ያሸነፍሽኝ አንች በኔ ልብ ተቀምጠሽ
ሳልሰማው መልስሽን እላለሁ የኔ ነሽ
ያንች ልብ ማለት የራሴ ነው ብዬ
ልብሽን በልቤ በሚገባ ስዬ
ልብሽን ወስጄ እኔ ውስጥ ከትቸ
የኔን ምላሽ ሰጠሁ ያንችን ልብ ተክቸ
ከዛ በኋላማ ሳላፍር ስላንቸ ብዙ አወራለሁ
አንችን ሳላሞግስ መቼ ውየ አድራለሁ
ጠዋት ማታ ሁሌም ስላንች አስባለሁ
ስላንች በድፍረት ሳወራ የሰሙኝ
የኔን መውደድ አይተዉ ስላንች ጠየቁኝ
ቆይ እስኪ ምንህ ናት? እያሉ አዋከቡኝ
የነሱ ጥያቄ ሲደጋገም ጊዜ ረፍት ስለነሳኝ ያበጠው ይፈንዳ ምን ይመጣል ብየ
ፍቅሬን ተናገርኩኝ ''እሷ ማለት እኮ በፍቅሬ የተረታች
ምንም የማትመኝ ከሰማዩ በታች
ከኔ ውጭ ወንድ ያለ የማይመስላት
በጣም የምትወደኝ በጣም የምወዳት
በቁንጅና ብዛት ጉድ የተባለላት
ሁሉም ሰው ለራሱ ከልብ የተመኛት
ከማንም ሰው በላይ የምታፈቅረኝ ናት
አልኳቸው በድፍረት የኔ ብቻ ሴት ናት
አደራ የኔ ውድ ይሄንን ስትሰሚ
ከቶም እንዳይከፋሽ እንዳትቀየሚ
የጠየቁኝ ሰወች መጥተው ከጠየቁሽ
ምንህ ናት እንዳሉኝ ምንሽ ነው?
ካሉሽ ያንችንም ጨምረሽ በያቸው በድፍረት
እሱ ማለት እኮ የተረታሁለት
ከምንም በላይ እኔ 'ምሳሳለት
ከሰማዩ በታች ምንም የማልመኝ
ከሱ ውጭ ወንድ ያለ የማይመስለኝ
በጣም የምወደው በጣም የሚወደኝ
እቅፍ ድግፍ አርጌ በእኔ ልቤ ያኖርኩኝ
እሱን ብቻ እኮ ነው ሁሌም እኔ ምመኝ
በያቸው ጨማምረሽ እንደምታፈቅሪኝ
ስላንች የነገርኳቸውን ደግመሽ ንገሪልኝ
አደራ የኔ ውድ እንዳታሳፍሪኝ
አደራ በኔ ሞት እንዳታሳፍሪኝ


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
694 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 21:05:03 ከባለቤቴ ጋር ከትዳር በፊትም በትዳራችንም ደስተኛ ነን ፡፡ ኑሮን ለማሻሻል እና ለልጆቻችን ጥሪት ለማፍራት ግን ብዙ መስራት ነበረብን፡፡ ከመደበኛ ስራችን ጎን ለጎን የተለያዩ ንግዶችንም ጀመርን፡፡
ጋብቻችን የተፈፀመው የሷ ቤተሰቦች ባልነበሩበት ነበር፡፡ እኔ የማውቀው እናቷ ፀበል እንደሆኑና ሲወጡ አንድ ፕሮግራም አዘጋጅተን እንጠራቸዋለን እያልን ቀን ስንቆጥር እሳቸው ፀበል ሳይሆን እስር ቤት ቆይተው ኖሮ ድንገት ሲፈቱ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው መሄድ ስለማይችሉ እኛ ጋር መምጣት ግድ ሆነ፡፡ በባህላችን መሰረት ቤተሰብ ለቤተሰብ በድግስ ከማስተዋወቅ በፊት እሳቸውን ማግኘት ስለማይቻል ለጊዜው ከቤቴ ወጥቼ ሆቴል ያዝኩኝ፡፡
ከዛሬ ነገ ዝግጅት እንጀምር እያልኩ ከባለቤቴ ጋር እየተነጋገርኩ ጭራሽ እናት አሻፈረኝ ጋብቻውን አልፈቅድም አሉ፡፡ ባለቤቴ ነፍሰጡር ነበረች እንዳትወልድ ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ዱላ እስከማንሳት ደርሰው ጎረቤት ገላገላቸው፡፡ አለመግባባቱ እየከረረ ሲመጣ ትታቸው እኔ ጋር መጣች ፡፡ አካባቢ ቀይረን አብረን መኖር ጀመርን ፡፡ ልጃችን ተወለደ፡፡ ምግብ ቤት ከፈትን፡፡ ስኬታማ ኑሮ ቀጠልን ፡፡

ቤተሰቦቿ ሽማግሌ ላኩ እርቅ ተቀበለች፡፡ እኔንም ካንገት በላይ ታረቁኝ፡፡ ወደ ምንኖርበትም መለስ መለስ እያሉ መምጣት ጀመሩና ጭራሽ መኖር ጀመሩ፡፡ መኖራቸው ባልከፋ ነበር ግን አዛዥ ሆኑ ገንዘብ ይባክን ጀመር ከሰርን ፡፡ እነሱን እዛው ትተን አካባቢ ቀየርን ፡፡

ኑሮን ሀ ብለን ጀመርን ጥቂት እንደኖርን አሁንም ተከትለውን መጡ ፡ እሷ መወሰን እንዳለባት ብቻችንን መኖር እንዳለብንና በቤታችን መወሰን እናዳለብን ስንነጋገር ደስተኛ አልሆነችም፡፡ መወሰን አልቻለችም ፡፡ እንዋደዳለን ግን እሷ ከቤተሰቦቿ ተፅዕኖ መላቀቅ አልቻለችም፡፡

ሌላ ልጅ ወለድን ፡፡ ትንሽ እንደቆየን ያለምንም ጥል ድንገት በመሀል ጥላኝ ሄደች ፡፡ልጆቼ መጎዳታቸውን ሰዎች እየነገሩኝ ሀሳቧን ቀይራ እንድትመጣ ብለምናትም አልተመለሰችም ልጆቼን እንድታሳየኝ ብጠይቃትም ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡
ከወራት በኋላ ተስፋ ቆርጨ ከሀገር ልወጣ እንደሆነ ስትሰማ ልጆቼን ይዛ ተመለሰች፡፡ ነገር ግን የቤተሰቦቿ ተፅዕኖ እንዳለ ነው፡፡እንዳልፈታት እወዳታለሁ ልጆቼንም ማጣት አልፈልግም አብሬ ለመኖር ደግሞ የቤተሰቦቿን ጣልቃ ገብነት መቋቋም አልቻልኩም፡፡እሷም ልታግዘኝ አልቻለችም ፤ምን ባደርግ ይሻለኛል ?

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
613 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 21:02:17
ልብ የሚሰርቅ ገራሚ ታሪክ እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ????

ከደቂቃዎች ብኋላ ይቀርባል።

እናንተም እንድንወያይበት ይጠቅማል እኔም መፍትሔ እፈልጋለሁ የምትሉት ጉዳይ ካለ #በአማርኛ ፅፋችሁ በዉስጥ መስመር @Yenefekirbot ላይ አድርሱን መልሰን ወደ እናንተ እናቀርባለን።

ሚስጥራችሁን እንጠብቃለን።

@yenefekir
588 views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 17:27:01 ከሁለት አፍቃሪዎችሽ እንዴት አንዱን መምረጥ ትችያለሽ?
====================
አንዳንድ ሰዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለሁለት ሰዎች የፍቅር ስሜት ሊፈጠርባቸው ይችላል፡፡ በርግጥ ይህ የሚያጋጥም ነገር ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥያቄው ግን ለዘላቂ ፍቅር ቁርጠኛ የሆነውን ከሁለቱ መካከል አንዱን እንዴት መምረጥ እንችላለን? የሚለው ነው፡፡ ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች ጥቂት ነጥቦችን እንንገራችሁ፣

በደምብ እወቂያቸው
====
መቼም ሁለቱም ሰዎች በትክክል ምንነታቸውን እሳላወቅን ድረስ ማንን መምረጥ አለብን የሚለው ውሳኔ ላይ መድረስ አይቻልም፡፡ ስለዚህ የሚጠሏቸውን የሚወዷቸውን፣ ልምዶቻቸውን እና የመሳሰሉትን ሁሉንም ስለእነርሱ ማወቅ አለብኝ ብለው የምታስቢያቸውን ነገሮች ሁሉ ጠንቅቀሽ እወቁ፡፡

ስለነገ ምን ያስባሉ?
====
እነዚህ ሰዎች ከህይወት ምንድን ነው የሚጠብቁት? ህይወታቸው ወዴት እየሄደ ነው?

ስለዚህ ምርጥ የምይውን አፍቃሪ ለመለየት የማናቸው የወደፊት ህልም ከአንቺ ጋር ስምም እንደሆነ ማወቅ ያሻል፡፡

ስለስሜቶሽ አስቢ
====
እርግጥ ነው ሁለት ሰዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ልታፈቅሪ ትችያለሽ፡፡ ነገር ግን ሁለቱንም በእኩል የስሜት ደረጃ ላታፈቅሪ ትችያለሽ፡፡ ምናልባትም ለሁሉቱም ጠንካራ ስሜት ይኖሽ ይሆናል ነገር ግን ለአንደኛው በተለየ ሁኔታ ሀይለኛ የሆነ ፍቅር እንደሚኖርሽ አያጠራጥርም፡፡ እስኪ ረጋ ብለሽ በደምብ ስለስሜቶችሽ አስቢ፤ ማነው ከአንቺ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያለው?

ከማን ጋር ስትሆኝ ነው ራስሽን ምትሆኝው
====
አብረሽው በፍቅር አልያም በሌላም ግንኙነት ከምትጣመሪው የትኛውም ሰው ፊት ማስመሰል እና ራስሽን አለመሆን ትልቅ አደጋ ነው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ከእርሱ ጋር ስትሆኝ ራስሽን ሆነሽ ለመቅረብ ቀለል የሚልሽ ከሆነ ምርጫሽ መሆን ያለበት ይህ ሰው ነው፡፡

ማን ይበለጥ እየጣረ ነው?
====
መቼም ከሁለት አንዱ ልብሽን ለማሸነፍ አጥብቆ እየለፋ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያሉ አፍቃሪዎች ከአንቺ ጋር ረዥም ጊዜ መቆየት ህይወት መመስረት የሚልጉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች እንግዲህ ፍቅር ረቂቅና ምስጢራዊ ነገር ነው፡፡ የትኛው ፍቅር ዘላቂና በደስታ የተሞላ ይሆናል የሚለውን ለማወቅ ግን ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ራስን መፈተን ያፈቀረንነውን ሰው በጥልቀት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
844 views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ