Get Mystery Box with random crypto!

💖የኔ ፍቅር 😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.94K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-12-27 07:35:24
#Fekir_1K270

Beliye yene liyu setota
Yene astewaye ehte betame new yemewedshi anchine lemegletse kalatoch yatrugnle ema fetari kezehe belaye edmena tena yadlsh kere zemensh be desta ena be fikire emtnorebet yarglshi wude enkwan teweledshilegn yene Konjo
HAPPY BIRTHDAY TO YOU

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
244 viewsedited  04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 17:42:02 #ለራቅሽኝ ............
............ #ለናፈቅሽኝ
~~~~


እኔስ ናፍቀሽኛል

ናፍቀሽኛል ብልሽ ቃሉን አሳንሼ፤
ቃላት ቢቸግረኝ መዛግብት አስሼ፤

እንዳትቀየሚኝ

ቋንቋ ባጣ ኖሯል ፤
እንዲ እንደዋዛ
ያልኩት ናፍቀሽኛል፡፡

ናፍቀሽኛል ስልሽ ናፍቀሽኝ ከልቤ
ሳቁ፡ ጨዋታሽን፡ ኩርፊያሽን ተርቤ

ያ የዋርካ ዛፍ ፥ ፍቅር ያወጋንበት
ያ ውብ ጎዳና፥ ዘውትር ምንሄድበት
ያዳመጥነው ዘፈን
የፈጠርነው ዜማ ፤
ያካለልነው ሰፈር
ያ ሰፊ ከተማ...

አብረን ያሳለፍነው ያንን ሁሉ ጊዜ
እኔ አልጠራልሽም ፤
'ትዝታሽ ትዝ አለኝ' ብዬ አላደክምሽም፡፡

ግና ብቻ ውዴ
የፍቅርሽን ጦም፥ የፍቅሬን ሁዳዴ ፤
ልባችን ውስጥ ያለ
ባዳ የማያውቀው ፤
'ሆድ ይፍጀው' ብያለው
ሆድሽ ስለሚውቀው፡፡

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
329 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 17:57:31 #ላንቺ_ስል_ተኛለው



አይኖቼን ከድኜ ላንቺ ስል ተኛለው፣
ትመጪ እንደው ውዴ ህልሜን ከጅላለው፣

መተኛት ሳያሻኝ ሳይደክም አካሌ፣
ፈጥኜ ተኛለው ድንገት ባይሽ ብዬ፣

የቀኑ ርዝማኔ የሰዓቱ ጉዘት፣
በፈጠነ እላለው ላይሽ የጓጓው ለት፣

ላንቺ ስል ተኛለው ትመጪ እንደው ብዬ፣
መገናኛ ሆኖ መደብ መተኛዬ፣

ፀሀይ በይ ተከለይ ተከተች ከቤትሽ፣
ጉዳይ አለኝና ቀኑ ደርሶ ሲመሽ፣
ለፅልመት ልቀቂ እባክሽን ፈጥነሽ፣

ፀጥ ባለው ምሽት ከቤቴ ወጥቼ፣
በህልም ጋልቤ እርቄ ከደጄ፣
ልሂድ ወደሷ ጋ ወደ ልብ ወዳጄ፣

አባቷም አይሰሙ እናቷም አይነቁ፣
ገባለው ከቤቱ አንዳቸው ሳያውቁ፣

በሩ ሳይንኳኳ ኮቴ ሳይሰማ፣
ሄዳለው ሆዴ ጋ በደረቅ ጨለማ፣
በህልም አለም ሽምጥ ሆኜ ባለግርማ፣

አንቺም አታውቂውም ካንቺ ጋር ማደሬን፣
ለሰው አላወጋው የሰመመን ህልሜን፣

ከህልሜ ሜዳ ላይ ሰርክ አስስሻለው፣
ካንቺ ጋ ቦርቄ አብሬሽ አድራለው፣
ሳቅሽ ሳቄ ሆኖ እኔም እስቃለው፣
ውዴ ስትናፍቂኝ ላንቺ ስል ተኛለው፡፡
#ከባህር_ዳር_ለአንቺ_ይድረስ



           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
736 views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 12:47:25 ምናልባት አሁን እናንተ የምታስቡት ሰው ስለእናንተ እያሰበ ቢሆንስ....

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
927 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 18:58:14 #ላንቺ_ስል_ተኛለው



አይኖቼን ከድኜ ላንቺ ስል ተኛለው፣
ትመጪ እንደው ውዴ ህልሜን ከጅላለው፣

መተኛት ሳያሻኝ ሳይደክም አካሌ፣
ፈጥኜ ተኛለው ድንገት ባይሽ ብዬ፣

የቀኑ ርዝማኔ የሰዓቱ ጉዘት፣
በፈጠነ እላለው ላይሽ የጓጓው ለት፣

ላንቺ ስል ተኛለው ትመጪ እንደው ብዬ፣
መገናኛ ሆኖ መደብ መተኛዬ፣

ፀሀይ በይ ተከለይ ተከተች ከቤትሽ፣
ጉዳይ አለኝና ቀኑ ደርሶ ሲመሽ፣
ለፅልመት ልቀቂ እባክሽን ፈጥነሽ፣

ፀጥ ባለው ምሽት ከቤቴ ወጥቼ፣
በህልም ጋልቤ እርቄ ከደጄ፣
ልሂድ ወደሷ ጋ ወደ ልብ ወዳጄ፣

አባቷም አይሰሙ እናቷም አይነቁ፣
ገባለው ከቤቱ አንዳቸው ሳያውቁ፣

በሩ ሳይንኳኳ ኮቴ ሳይሰማ፣
ሄዳለው ሆዴ ጋ በደረቅ ጨለማ፣
በህልም አለም ሽምጥ ሆኜ ባለግርማ፣

አንቺም አታውቂውም ካንቺ ጋር ማደሬን፣
ለሰው አላወጋው የሰመመን ህልሜን፣

ከህልሜ ሜዳ ላይ ሰርክ አስስሻለው፣
ካንቺ ጋ ቦርቄ አብሬሽ አድራለው፣
ሳቅሽ ሳቄ ሆኖ እኔም እስቃለው፣
ውዴ ስትናፍቂኝ ላንቺ ስል ተኛለው፡፡
#ለአንቺ_ይድረስ



           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
67 viewsedited  15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 16:41:02 ​​#ዝም_ብዬ_ላፍቅርሽ
.
እኔና ዝምታ ስናወራ ብታይ
ጉድ ይላል ማዕበል ይደነቃል ሠማይ
ዝናም ይደመማል ግር ይላታል ፀሀይ
እውነት ነው የምልሽ
ማመን እስኪያቅትሽ
እኔና ዝምታ ስናወራ ብታይ
ድሮ ይለወጣል ይሆናል ዘመናይ
:
ዝምታን ቀዝፌ
እሽታን ታቅፌ
ጎርፉን እየታገልኩ ስመላለስ ካየሽ
ምን አስባ ይሆን? ከሚል ጉብታ ላይ ቁጭ ብዬ ካየሽ
አደራ ጥሻ እንዳጥሺ
ፍቅሬ የሚለውን አመፅሽን አትቀስቅሺ
ባላወራሺው ተረት አፌን አታብሺ
:
ግን እኔና ዝምታ ስናወራ ካየሽ
በድኔ ነው ያለው! በድኔን ነው ያየሽ!
በቡቃያው ዓለም ባሰስነው አዝመራ
ባቦካነው አፈር በረጨነው አቧራ
ጩኸት ብቻ ፍቅር
አዳማጭ ያጣ ህብር
:
ከክፋት ችግኝ ላይ ደስታ ሲሆን ዓረም
እንቦጭ ነቃይ ጠፍቶ ሲበቅል በኛ ዓለም
ነቅተሽ ሆኖ እንደሆን ተመኝተሽ ዋይታ
ትላንት ከናፈቀሽ ከገባሽ ዝምታ
ነይ አብረን ዝም እንበል እናውራ ትዝታ
:
ትላንት ግን ደክማለች አትስቅም ከቶ
ጥርሷ ዛሬ የለም ትላንቷ ላይ ወቶ
ነግሬሽ ከሰማሽ
እኔና ዝምታ ስናወራ ካየሽ
ከቶ እንዳይመስልሽ
በኔና አንቺ ፍቅር
እግሬ እሚተሳሰር

ተይ ልንገርሽ ዝምታሽን ኑሪ
በህባሬ ቅኔ ድርሽን አትድሪ
ግን እውነት እውነት ስልሽ
እኔና ዝምታ ስናወራ ካየሽ
በጩወቴ ዘመን ጮኬ ያልነገርኩሽ
ያ ፍቅርሽ አውሎ ሠማይ ቅኔ
ምድር ጥልቀት ሠጥሞ በኔ
ዝብርቅርቃን ክስተት አውሎ በቀኔ
የሴት ሴቴ ሆነሽ ተላምጄሽ እኔ

እንደ አካሌ ክፋይ
እንደ ልቤ ጉዳይ
ጉም እንደሚጋልብ እንደ ገነት ጉዳይ
ፍፁሜ ነበርሽ እንደሌለው ስህተት
ታሪኬ ነበርሽ እንደ ዕድሜዬ ርዝመት

……ያኔ ስንጮኽ ያልነገርኩሽ!
ልቤ ላይ መቅኔ ቀስቃሽ
ውድ ፍቅር አለሽ
……ያኔ ስንጮኽ ያልነገርኩሽ!
ደፋ ቀና ብሎ ዝምታዬ የከለለሽ
ዝቅ ብዬ ከማፍር ቀና ብዬ የደበኩሽ
ውድ ፍቅር አለኝ ጊዜ ሄዶ ያልነገርኩሽ
:
ናናዬ የትላንቴ ጣፋጭ ከረሜላ
መጥጬሽ ልደሰት ጩኸቴ ይቀላ
ዝምታችን ያውራ
ይኑር ፍቅር እየሰራ
ውስጣችን ያፍቅር ውስጣችን ይናገር
ጩኸቱ ይቅርና ዝምታ ይፋቀር
:
:
:
አንቺም ዝም በይ ዝምታ ላልምድሽ
ዝምታ ሰብስቤ ዝም ብዬ ላፍቅርሽ


           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
705 views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 19:40:07 #ማይንገርሽ


ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ

ገና ገና ሳይሽ

ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር

ጉልበቴም ይዝላል
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል
ልቤም ያው ይፈራል

ታዲያ የኔ ፍቅር

የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ

ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ​


           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
694 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 18:41:42 #አንቺን_ላለማሰብ


አንቺን ላለማሰብ እኔማ በኔ ቤት፣
ከውስጤ አውጥቼ አብዝቼ ለመርሳት፣

ሲጋራውን ለኮስኩ ጢሱ እንዲጋርደኝ፣
ምስልሽን ከዓይኔ ወዲያ እንዲወስድልኝ፣

ደግሜ ደግሜ ልረሳሽ ባጤሰው፣
ከንፈርሽ ናፈቀኝ ከንፈሬን ሲነካው፣

እሱን ወዲያ ትቼ መጠጡንም ብጋት፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺኑ ለመርሳት፣

እያንገዳገደ ደጅሽ ይወስደኛል፣
ልረሳሽ ስደክም ትዝታሽ በልጦኛል፣

ፀሀይንም ሳያት አስታውስሻለሁ፣
ትዝ ይልሽ እንደሆን ውበቷን ካንቺ ጋር አመሳስያለሁ፣

ጨረቃንም ሳያት እነኚያ ምሽቶች ይከሰቱብኛል፣
ከባዶነት ነጥቀው ካለፈው ምናኔ ወስደው ይከቱኛል፣
አንቺን ላለማሰብ ለኔ አንቺኑ ማሰብ እጅግ ይቀለኛል፣

ያላረኩት የለም ከውስጤ ላወጣሽ፣
ግና፣
ልረሳሽ ያልኩለት የባሰ ወደድኩሽ፣

አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን እያለምኩኝ፣
ትዝታን ለመቅበር ብዙ ብዙ ጣርኩኝ፣

የሄድንበት መንድ እኔና አንቺ አብረን፣
ያወራኛል ደርሶ ይጠይቃል አንቺን፣

ከፀሀዯ ንዳድ የተከለልንበት፣
ያ የሾላ ዛፍም አነሳሽ በድንገት፣

አንቺን ላለማሰብ ማሰብ ባላቆምም፣
ትዝታሽ አስሮኛል የትም አላመልጥም፣

ብራመድ ጎዳናው፣
ብቀመጥም ጥላው፣

ማለዳ ንጋቱ፣
ድጋሜም ምሽቱ፣
ያንቺ ወዳጅ ናቸው አንቺን ሚተርቱ፣

ይገርምሻል ውዴ እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ላለማሰብ አንቺን እያሰብኩኝ፣
ለመርሳት ፈልጌ ሁሌ እያስታወስኩኝ፣
ትዝታን አግብቼ የተሰቃየሁኝ፣

እኔኮ እንዲ ነኝ፣
አንቺን ካለማሰብ መሞት የሚቀለኝ፣
ምንድነው ግን ቅኔው ፍቺና ንገሪኝ፣
አንቺን ለመርሳት ስል አንቺን ሚያሳስበኝ፣

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
790 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 07:24:56
#Fekir_1K269

Habibiti ye ena sat zare ketgnagnen 9 wer moltonal gizawe hadwal bezu negrm asalfnal hulam ke gona nesh bedsatyem beaznkubtm gize altlyeshgnm be kalat yemaygls kebr algn lanechi telyalesh tenshm benrarak fekrachn chmerwal enji alnesm neff amet amtem ke esu ga I love you so much

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
730 viewsedited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 17:40:06 #አትራቂ_ከጎኔ


አንዳንዴ ሲያስብ ያንቺን መራቅ፣
የሆዴን የቅርቤ ሰው ባያውቅ።
ይተናነቃል እንባዬ ያዝናል ልቤ፣
ባትሪቅኝ እያልኩ ሁሌም ካጠገቤ።
ያንቺ ሆኜ በስምሽ ተጠርቼ፣
መኖር ይሻለኛል ካንቺ ተጠግቼ።
ማን አለኝ እኔ ካንቺ ወዲያ፣?
ያንቺው ልብ ነው ውሎ ማደሪያ።
ልብሽን ክፈቺ ልኑርበት ከልብሽ፣
እኔ ያንቺው ነኝ አርጊኝ የራስሽ።
ብቸኝነቴን አይቶ ቢያነባም አይኔ፣
እወድሀለው በይኝ አትራቂ ከጎኔ።

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
762 views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ