Get Mystery Box with random crypto!

💖የኔ ፍቅር 😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenefekir — 💖የኔ ፍቅር 😘
የሰርጥ አድራሻ: @yenefekir
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.94K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ @yenefekirbot ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን።
⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @yenefekir ይላኩለት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-01-02 19:48:01
#Fekir_1K274

​​​ናፍቀሽኛል ሆዴ

                  መንገድሽ መንገዴ
                     ሆኖ የዘለቀው
                   ፍቅርሽ ስለገዛኝ
               ባሪያሽ ስለሆንኩ ነው

                   ሆዴ ናፍቀሽኛል
                  ምፈልገው ቢሟላ
                 የጠየኩትንም ባገኝ
                  አልጠግብም እኔ
                 አይንሽ ነው የራበኝ

                   ፍቅር ናፍቀሽኛል
                   ሆዴ ናፍቀሽኛል
                  አንቺን ለማግኘት
              ልቤ አጥብቆ ይመኛል


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
394 viewsedited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 18:13:59
#Fekir_1K273

Yene fikr tawkalhi anti behowt west selalki batam edlag ng fikr men endhun astmrhigal anti eko len fikr bechi aydelhim hulu nagr nk yalnti hewotin sasbi yemr yeskifagal mar awkalw yene tsbay batam kebdi new gen lanti Normal new yemjamry lalhun echilalw gen hula meguta yemchrishi lemhun new yene ebdi yehn mechim endtrsa hulam afkrhalw

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
546 viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 18:50:07 አካላዊ ንክኪዎችና ትርጉሞቻቸው

የሰውነት ቋንቋን መረዳት እንዲህ ቀላል የሚባል ነገር አይደለም፡፡ እንደውም የሰውነት ቋንቋዎን ከአውድ ጋር አጣምሮ መረዳት ካልተቻለ ስህተትነቱ ያመዝናል፡፡ የአንድን ሰው ፍላጎት ቀድሞ መረዳት ከበርካታ ችግሮች ሊጠብቀን እንደሚችለው ሁሉ በህይወታችን ውስጥ አወንታዊ ለውጦችን እንድናደርግ ሊያበረታታንም ይችላል።

አካላዊ ንክኪ በየእለቱ ኑሯችን ውስጥ የሚያጋጥመን ክስተት ነው፡፡ ያው ሰዎች እንደመሆናችን መጠን እርስበርስ ይበልጥ ለመግባባት በምናደርገው ጥረት አካላዊ ንክኪን መጠቀማችን አይቀርም፡፡ ደግሞም አካላዊ ንክኪዎች ከንግግር በተሻለ ጠንካራ ስሜታዊ ግንኙነት መፍጠርንም ይችላሉ፡፡ ታዲያ እንደስነልቦና ባለሙያዎች ጥናት ከሆነ ደግሞ የተለያዩ አካላዊ ንክኪዎች የተለያየ ትርጓሜን ያንፀባርቃሉ፡፡ እስኪ ጥቂቶችን እንመልከት

#ማቀፍ

ይህ አካላዊ ንክኪ ሰላምታ፣ የመቀራረብ ጥያቄ፣ ወይም ማጽናኛን የሚያመለክት ምልክት ነው። ማቀፍ ቅርብ በሆኑ ሁለት ሰዎች መካከል ወይም በእንግዶች መካከል ሰላምታ ለመግለጽ ሊከወን ይችላል፡፡

#ክንድን_መያዝ

ውጫዊ ሀይልን መፍራት ለማሳየት፡፡ ተቀመጥ ለማለት አልያም ደህንነትን እና መመሪያን ለማግኘት የሚያስችል መንገድ መፈለግን ያመለክታል፡፡ ይህ አይነት ንክኪ በቀላሉ ወይም ጠንከር ባለመንገድ ሊንፀባረቅ ይችላል፡፡

#ክንድን_ማሻሸት

የአካላዊ ቅርበት ምልክት ነው፣ ሞቅ ለማለት ያለን ፍላጎት ያሳያል፣ ርኅራኄ ማሳየት፣ ወይም ከተቀባዩ እርካታን መጠየቅ ሊሆን ይችላል፡፡

#ጥብቅ_አድርጎ_ማቀፍ

የመቀራረብ ፍላጎትን፣ የመተሳሰብ ፍላጎትን፣ ጭንቀትን፣ የጥበቃ ጥያቄን እና መፅናናትን ያሳያል።

#ከትከሻ_በላይ_ክንድን_ማሳረፍ

ጥበቃ፣ ፍቅር፣ የመቀራረብ ፍላጎት

#ክንድን_ወገብ_አካባቢ_ማሳረፍ

ይህ አይነቱ ንክኪ ጥበቃ፣ ፍቅር፣ መተዋወቅ፣ ወሲባዊ ፍላጎት እና ማሽኮርመም ያሳያል።

#ሁለት_እጆችን_ትከሻ_ላይ_ማሳረፍ

ጽናት እና አንድን ሰው ለማሳመን መፈለግን ያመላክታል፡፡

#ግንባር_ለግንባር_መነካካት

ፍቅር እና የመቀራረብ ልመና፡፡

#ፊትን_በእጅ_መዳሰስ

ፍቅርን ያለ ቃል ለማስተላለፍ መፈለግ።

#ክንዳቸውን_ከእርስዎ_ጋር_በማያያዝ

ጓደኝነት፣ ደህንነት ወይም መመሪያ መፈለግ፡፡

#ፀጉርን_መነካካት

መተዋወቅ ወይም ለመቅረብ ያለን ፍላጎት መግለጽ።

#ፊትን_ወይም_ጭንቅላትን_ትከሻ_ላይ_ማሳረፍ

መተዋወቅን እና መፅናናትን መግለጽ፣ መቅረብ መፈለግ እና ፍቅርን መጠየቅ።

#እንባን_መጥረግ

ይህ በጣም ከሚነኩ አካላዊ ንክኪዎች አንዱ ነው። ከመሳም በላይ እንባን መጥረግ ማለት መተማመን እና ተጋላጭነት አለ ማለት ነው።

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
724 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 13:48:02
#ፀናለሁ

ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ
ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ

አንቺ ግን
በናፍቆትሽ ገመድ ታስሮ 'ሚጠብቅሽ
በእንባ 'ሚታጠበው ያው ቡቡው አድናቂሽ

እንዲሉሽ ፈልገሽ
ልክ እንደመስቀል ወፍ ታይተሽ ትጠፊያለሽ

አበቦች ሲፈኩ ደምቀሽ ትመጪና ሲከስሙ ስትከስሚ
ስጠብቅሽ ውዬ ተስፋዬ ተሟጦ ጠርቼ ገጣሚ

"በል እንግዲህ ሆዴ ካለው ተላመድ
ቢያስሩበት አያጠብቅ በስባሳ ገመድ"

የሚለውን ስንኝ ከነፍሴ እንዲያዋህድ

እንድረሳሽ ብሎ ቅኔ እየዘረፈ ስንኝ ቢያሰናኝም
እንኳንስ ሊያስረሳኝ ትዝ አልሽኝ ሲገጥም

እናም እርሳኝ ካልሽኝ መርሳቱን አልችልም
ቀሰሩብኝ ብዬ ዓለሜን አልሰጥም
አስበኝ ካልሽኝ ግን አስታውሰኝ ካልሽኝ ግን እጠብቅሻለሁ ጊዜው ለ'ኔ እስኪቆም

ዓለሜን አፅድቆ የወል ሀቅ እስኪያረግ
ውጣ ቢሉኝ ገደል ውረድ ቢሉኝ 'ረግረግ
እከተልሻለሁ ዳንኤል ነኝ አልፈራም
እወድቅ ቢሆን እንጂ ከቶ አልሰበርም ...

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
126 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 22:05:41
#Fekir_1K272


ዛሬ ለእኔ ይቺ እለት እጅግ በጣም ልዩ ቀን ናት አንድም አምላክ ያዘጋጀልኝን ስጦታ ወደ ምድር የላከልኝ እለት ናትና።የኔ ፍቅር እግዚአብሔር አዳም ብቻውን ይሆን ዘንድ አልወደደምና ፍቅሩን ከጎኑ አበጀለት። እንዲሁ ለእኔም በቸኝነቴን ያፈርስ ዘንድ በዝች በተቀደሰች እለት አንቺ ፍቅሬን ውብ አድርጎ አበጅቶ ላከልኝ እኔም ባንቺ ፍቅር ልታደስ ተወለድሺልኝ። የኔ ውብ መልካም ልደት!!!!!!
H
A
P
P
Y
B
I
R
T
H
D
A
Y

የኔ ፍቅር በዚች እለት ወደ ምደር ስትመጪ ያለቀሺበት ምክንያት ምን እንደሆነ ታውቂአለሽ
እንድም እኔ እያዘንኩ ለብዙዎች ደስታ እሆናለሁ እያልሽ ነው።
እኔ ባዝንም ሌላን አላሳዝን ያልሽበት እለት ናት።
ደስታዬ ሆነሻል አመሰግናለሁ ህልም እንዲኖረኝ አድርገሺኛል እጅግ አመሰግናለሁ ፍቅርን ሰተሺኛል የኔ ፍቅር ከሁሉም አብልጬ አመሰግናለሁ።

መልካም ልደት
HAPPY BIRTHDAY


ይድረስ ለፍቅሬ

ከፍቅሯ

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
458 viewsedited  19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 18:06:50 #እኔ ጠላሻለሁ፣


እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ

እኔ ጠላሻለሁ፣

እንደ ረጅም መንገድ
ላብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በኃላ እንደ መንገዳገድ

እኔ ጠላሻለሁ

ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት

እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)...

ግን አሁን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል
ጠላሁሽ ያበዛው ወድጄሽ ነው መሰል።

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
221 views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 19:47:02 #ልርሳ'ታውስ

ልቤ መነኮሰ ዓለም ውስጥ መነነ
አንቺን ተከትሎ እኔነት ተነነ
የማገኝሽ መስሎኝ
እሺታሽ ሚደርሰኝ
ቀን ሌቱን ባስብሽ ምንም አልተረፈኝ
ሀሩር ትዝታሽን መሸከም ቢያቅተኝ
በየኪዩስኪው ቤት መነኮሳት ይዤ
የምረሳሽ መስሎኝ አፌን አያይዤ
ብገባም ደንዝዤ
መርሳት እንደምነው
በጨፈንኩኝ ቁጥር ምስልሽ ቤት ሙሉ ነው
ቢመክሩኝ እንድቅም እንድረሳሽ ብለው
ትንሽ ስነካክስ ትዝ ትይኛለሽ ምርቃናዬ እሱ ነው
ማጤስም ብጀምር ያወጣሻል ብዬ ከጢሱ አዋህዶ
ያስታውሰኝ ጀመር የረሳሁትንም ወደ ኋላ ሄዶ
እናማ ሆድዬ
የምረሳሽ መስሎኝ
ያስረሳል ያሉትን ሁሉ እየሞከርኩኝ
እንኳንስ ልተውሽ
እንኳንስ ልረሳሽ
በሞከርኩኝ ቁጥር ይበልጡን አሰብኩሽ
በትዝታሽ እሳት እየተገረፍኩኝ
ትናንትናን ስኖር ዛሬዬን አቆምኩኝ

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
531 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 17:43:01 #እናቴ ልዩ ናት

ልቧ ሢቀጠቀጥ ደረቷን ደግፋ
አንጀቷ ሢታጠፍ ጉልበቷን ደግፉ
ምርኩዟ ሢሠበር እንዳይወድቁ ወድቃ
ሠውነቷ ሢዝል ማክሌቷ ሢጠፍ
ብሦቷን በሙዳይ በመላ ቆልፋ
በዘመን ሸራ ላይ
በእንባ ቀለሟ ብዙ ታሪክ ፅፋ
እርሷ ማለት ለኔ ከፈጣሪ በታች
መገደን አስልታ ቀኔን ያሣመረች

እናቴ

ባማንም በምንም የማልተካት ሀብቴ
የኔ ጀግና እርሧነች ልዩ በህይወቴ

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
623 views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 07:21:22
#Fekir_1K271

ታውቂያለሽ አንቺን አለማሰብ
አንቺን አለመናፈቅ ለእኔ ፈተና ነው

የማገኝሽ ድጋሚ ፊት ለፊት ተቀምጠን የምንገናኝ መስሎኝ በጣም ተደስቼ ነበር ግን አልሆነልኝም ምናልባት እኔ እንደማስብሽ አንቺ አታስቢኝም ይሆናል እኔ ግን እናትዬ ሁሌም እንደምነግርሽ ሁሌም እየደወልኩ እንደምጨቀጭቅሽ እንደነበረው ዛሬም የልጅነት ፍቅሬን አናፍቅሻለሁ።

ዛሬ ደሞ ከቀኖች ሁሉ ለእኔና ላንቺ ልዩ ቀን ነው ለእኔ የማፈቅራትን ልጅ  የተወለደችት ቀን ሲሆን!
ላንቺ ደሞ ወደዚች ምድር የመጣሽበት ቀን ነው።
ብዙ የመልካም ምኞት ፍላጎቶች ውስጤላይ አሉ ምናልባት አንድ ቀን ከተገናኘን በአካል ተቀምጠን እነግርሻለሁ።

#መልካም_ልደት_ለልቤ_ናፍቆት
#ከሠምዬ

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir
1.0K viewsedited  04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 19:42:02 #አለቀ ተሰፋዬ:

ልብሽ እውነት አለው ፣
አይን ወረተኛ ነው
ልብሽን ተከተይ ፣ ጠሪሽ አክባሪሽ ነው ።
ተሰፋዬን ሳባብል
ጠዋትና ማታ ፣
በፍቅርሽ ታስሬ ፣ስቋጠር ስፈታ ።
እንደ ፀሀይ ደምቀሽ ፣ከምስራቅ ስቶጭ ፣
ትሞቂ እንደሁ ብዬ
ሣንጋጥጥ ወደላይ ፣
ምነው? ተጋርደሽ ሄድሽ ፣ከደመና በላይ ።

ግርዶሹም ጥቁር ነው
ሲሻውም ይነጣል ፣
ቁልቁል ይዘብና ፣ ብዙ ሰው ያድጣል ።
ልብሽ እውነት አለው ፣
አይን ወረተኛ ነው
ልብሽን ተከተይ ፣ ጠሪሽ አክባሪሽ ነው ።
ማጥና ደረቁን መለየት ልመጂ ፣
ጭቃው እሾህ አለው
በደረቁ ሂጂ ።
ባይንሽ ፊት እያየሽ ፣
በልብሽ አስተውለሽ
ከማጡ ውጭና ፣ ከድጡ ላይ ድረሽ ።
አይንሽ መሀል ቢሻም ፣
ከልብሽ አይበልጥም
ዳሩ ይሻልሻል ፣ ቢድጥም አልማጠም ።

እየጠበኩሽ ነው ፣
ደረቁ ላይ ቆሜ ፣
የቀረኝ ተስፋ አለ ፣ውሰጂ በቁሜ ።
ትንሽ ስለቀረኝ
ትንሽ ልጠብቅሽ ፣
ያንቺን እየቆጠብሽ
የኔን ተስፋ ጨረሽ።

ልብሽ እውነት አለው ፣
አይን ወረተኛ ነው
ልብሽን ተከተይ ፣ ጠሪሽ አክባሪሽ ነው ።

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir
283 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ