2023-01-29 17:54:40
ከ"ሀ" -"ፐ"
# ይገርምሻል ውዴ
፡
ከፊደላት ደጃፍ ስከጅል ውብ ቃላት፣
ከብራናው ኑረው ቁልቁል ከሰፈሩት፣
፡
"ሀ" ብዬ "ለ"ን አየው አይኔንም ሳልከድን፣
ድጋሜ "ሐ" መጣች ደሞ አላለፍኩ "መ"ን፣
ቃል አጣሁኝ እንጂ ላንቺ የሚመጥን፣
፡
ከፊደላት ዋርካ ከበዛው ጠል ስር፣
የልቤን ላሳካ ዙሪያው ብዘዋወር፣
"ሠ" "ረ" እያልኩኝ ሳልሰለች ስቆጥር፣
፡
"ሰ"ም ድጋሜ መጣች እሳት ለብሳ ጎርሳ፣
እኔ ቃል አጥቼ ከቃላቶች ማሳ፣
፡
ይገርምሻል ውዴ፣
#የኔታ ካስያዙኝ ከነኚያ ንባባት፣
አጣሁ አንድ ቅኔ አንቺን ማወሳበት፣
፡
ካብሯደግ ጓዶቼ በዜማ አንብቤ፣
በራፊ ጨርቅ ቦርሳ ደብተሬን አንግቤ፣
የቆጠርኩት ፊደል የት ሄደብኝ ዛሬ፣
፡
"ሸ" ብዬ በቅኔ ስዘርፍ እንዳልነበር፣
አቅም አጣሁ ዛሬ ሲሆን ስለፍቅር፣
፡
"ቀ" ና "በ"ም ያዩኛል እኔ ተዳክሜ፣
ላንቺ ቃልን ሳጣ ከእርሻው ቃርሜ፣
ሚባርክ ሳይመጣ ሳልሰለች ካድሜ፣
፡
ይገርምሻል ውዴ በቃ እንዲ ነው የሆነው፣
"ተ" "ቸ" "ኀ"ም ዝም አሉ የፍቅር ቃል የት ነው፣
፡
ያልጠራሁት ፊደል ያልዳበስኩት የለም፣
ዳሩ ከብራናው ማንም ባይሰማኝም፣
"ነ" "ኘ" "አ" አዙረው ጀርባ ቢሰጡኝም፣
"ከ" "ኸ" "ወ" አድመው ከብደው ቢሸኙኝም፣
ይገርምሻል ውዴ እኔ ዝም አላልኩም፣
፡
ፅፌ ሰርዛለው፣
ስርዝ ድልዝ በዛው፣
የፍቅር ስንክ ሳር መላ አካሌን መታው፣
የቃላት ቸነፈር ልቤን አቆሰለው፣
የብራናው ባዶ ውስጤን አራቆተው፣
፡
ይገርምሻል ውዴ፣
ካንዱ ፊደል አንዱ ከተሻለ ብዬ፣
"ዐ" "ዘ" "ዠ"ን ልጠይቅ ሄድኩልሽ አንቺዬ፣
እነሱም ዝመም አሉ ዝምታን መረጡ፣
ምንም ሳይለግሱኝ ይበብስ ፈረገጡ፣
፡
"የ" "ደ" "ጀ"ም ያው ናቸው መፍትሔ የተራቡ፣
ከአሀዱ ክልቱ በከንቱ የተጋቡ፣
፡
የነ "ገ" "ጠ" "ጨ" ን ደጅ እዛም ጠንቻለው፣
ይገርምሻል ውዴ የፍቅሬን መግለጫ አንዳች አላገኘው፣
፡
እስከ በብራው ጥግ እነ "ጰ" "ጸ" "ፈ" መንደር፣
አልቀረው ታክቼ አረ ስዞር ነበር፣
አንደበቴ ሆነው ምንም ላልናገር፣
፡
"ፐ"ም ከማድነቅ ውጪ አልበጀኝ ለሌላ፣
እኔ ከፈፊት ስሄድ ቃሌ ወደ ሗላ፣
፡
ከብራናው ንጣፍ ከሰስከኩት ፊደል ጥግ፣
አንዳች አላገኘው ስዋትት ስፈልግ፣
፡
እናምልሽ ውዴ የማፍቅሬን ጥጉን በቃል አጠይቂኝ፣
የተፈታ አንደበት ልግም አታድርጊኝ፣
፡
ከብራናው ንጣፍ ከ"ሀ" እሰከ "ፐ" ፊደል፣
የለም ሚገልፅልኝ ላንቺ ያለኝን ፍቅር፣
፡
እናም አጠይቂኝ ውዴ ስለምንሽ፣
እንደ ፊደሎቹ ዝም ብዬ ላፍቅርሽ፣
┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
#Share
@Yenefekir
@Yenefekir
2.0K views14:54