Get Mystery Box with random crypto!

#ስወድሽ# ፡ የውልሽ ውዴ ሆይ ከዚ ሁሉ ፍጡር፣ እኔና አንቺ ብቻ በምድር ላይ ብንቀር፣ በራሳችን | 💖የኔ ፍቅር 😘

#ስወድሽ#


የውልሽ ውዴ ሆይ ከዚ ሁሉ ፍጡር፣
እኔና አንቺ ብቻ በምድር ላይ ብንቀር፣
በራሳችን አለም በራሳችን ቅጥር፣
ብዬ ተመኘሁኝ በዝቶ የኔ ፍቅር፣

ከምድር ጥግ ጫፍ ከሰማይ አፍላጋት፣
ለማንም ያልታየ ደግሞም ለነብያት፣
እኔ ልብ ውስጥ አለ እጅግ እልፍ ናፍቆት፣

ቴዎድሮስ ገብርዬን ሚያምነውን ያህል፣
እኔ አምንሻለው ለስትንፋሴ ጣዖት የሆንሻት ይመስል፣

ቃሎቼ ቢያወሩሽ አንቺ ማለት ለኔ፣
የናርዶስ ሽቱ ነሽ የመስዋዕት ከርቤ፣

እኔ አንቺን ስወድሽ እልፍ ነው መዘዙ፣
አመዳም ተራሮች አብረቅርቀው ወዙ፣

እኔ ነኝ የማውቀው ይብስ አንዳንዴማ፣
ናፍቆትሽ ሲያዞረኝ እንደ ክፉ ገልማ፣
እንኳን ሌላ ቀርቶ ራሴንም አልሰማ፣

ብቻ የምነግርሽ እኔ አንቺን ስወድሽ፣
አለም ትቀናለች ምን ብዬ ልንገርሽ፣

የፏፏቴ ድምፀት ይሁን ላንቺ ሆታ፣
ከአንደበት አልባው ከአለት እልልታ፣
ከተመረጡቱ ከፃድቃን ተርታ፣
ነፍሴ ታጥንልሽ ለፍቅርሽ ተገዝታ፣

ፀሃይ ነሽ ለኔ አለም ሁልጊዜም አንዳንዴ፣
ቃል አይገልፀው ፍቅሬን እልፍ ነው መውደዴ፣

ማህሌቱን ሲደግም ከአትሮኖስ ቆሞ፣
ስምሽን ቢያነሳው ቅር አይለኝ ደግሞ፣

እንደ በተስኪያን ደጅ ግንባርሽን ስሜ፣
እንደ ቀሲስ መስቀል አንቺን ተሳልሜ፣
ብኖር እመኛለሁ አርጌሽ አለሜ፡፡



┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir