Get Mystery Box with random crypto!

#ሁለት ዓለም ፡ አንቺን እስካወኩሽ እስከዛች ቅፅበት፣ ብቻዬን ለመኖር ነበረ ያሰብ | 💖የኔ ፍቅር 😘

#ሁለት ዓለም



አንቺን እስካወኩሽ እስከዛች ቅፅበት፣
ብቻዬን ለመኖር ነበረ ያሰብኩት፣

ፍቅርን አላለምድም ከእንግዲህ ለልቤ፣
ሰው አላምንም ከቶ ሞት ቢሆን ቀለቤ፣

ብዬ ወስኛለሁ፣
እካገኝሽ ድርስ እንዲ ነኝ አውቃለሁ፣

ያለፍኩት ስንክሳር፣
ሰው አምኖ መጎዳት
ቁስሉን ለማከም ብቻዬን ስጣጣር፣
ላላፈቅር ማልኩኝ ድጋሜ ብፈጠር፣

ብታዪ ያን ሰሞን፣
ለኔም እግዳ ነው እንዴት እንደምሆን፣

በደል እየመጣ የእንባ ቋቴን ወገቶ፣
ክህደት እያመመኝ መራር እውነት ግቶ፣
ነበር ያገኘሽኝ፣
ከፍቅር ስጣላ ፍቅር ያሳየሽኝ፣

ታዲያ ምን ያደርጋል፣
የኔ ልብ ሲድን ያንቺ ያገረሻል፣

ለካስ አንቺም ኖረሽ የፍቅር ታማሚ፣
ድንገት ተገጣጠምን
ፍቅርን ስጀምረው አንቺ ስትፈፅሚ፡፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir