Get Mystery Box with random crypto!

#በዝምታዬ ፡ በዝምታዬ ነው ያፈንኩት ስቃዬን፣ ለሰው ሳላወጋ ደብቄ ህመሜን፣ ደብኜ የቻልኩ | 💖የኔ ፍቅር 😘

#በዝምታዬ


በዝምታዬ ነው ያፈንኩት ስቃዬን፣
ለሰው ሳላወጋ ደብቄ ህመሜን፣
ደብኜ የቻልኩት ካንች መለየቴን፣

በዝምታዬ ነው ሳጣሽ የሸኘሁሸ፣
በልቤ አንብቼ የተሰናበትኩሽ፣
ምልጃም አላሰማው እያልኩኝ ተመለሽ፣

ብቻ እያየሁት የእግርሽን ዳና፣
ተመኘው ምቾትን በመራሽ ጎዳና፣
ስትሄጂ ሸኘሁሽ እኔም ዝም አልኩና፣

አቅሜ እሱ ነበር ያለው በመዳፌ፣
ክደት ከርችሞታል አይናገር አፌ፣
ዝም አልኩኝ ሲዘረፍ ሲከፈት ደጃፌ፣
የኔ ያልኳት ርቃኝ ሀዘኔን ሸክፌ፣
ልቤ ተቀዳዶ ላይጠግነው መርፌ፣
አልከስሽ ለዳኛ የውስጤን ጡር ፅፌ፣
ለፍቅር ተማርኬ ላንቺ ተሸንፌ፣
ዝም አልኩ ስትሄጂ ሲደፈር ደጃፌ፣

ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
እንደው ተብከነከንኩ፣
ትፋሼን አርዝሜ ቁናውን ተነፈስኩ፣
ዕንባዬን ሳላፈስ አምርሬ አለቀስኩ፣
በፍቅር እየኖርኩ ፍቅርን ረገምኩ፣
መሞሸሬ ቀርቶ ይባስ ብቸኛ ሆንኩ፣
ውስጤ እሬታ በዛ ዝም ስል ዝም አላልኩ፣
ከራሴ ተላተምኩ፣
ለሽንፈት ተሸነፍኩ፣

ዝም ብዬ ልሸኝሽ፣
ቸው እንኳን ሳልልሽ፣
መልካሙን ምኞቴን 'ባፌ ሳልገልፅልሽ፣
ይሄን የማረግው ስለምን መሰለሽ፣
ደጅ ደጁን እንዳይ ነው ብዬ ትመጫለሽ፣

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir