Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅሬን_ተረጀልኝ ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ ፈሪ ነህ ተብየ | 💖የኔ ፍቅር 😘

ፍቅሬን_ተረጀልኝ

ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ
በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ
ፈሪ ነህ ተብየ በሀሰት ስሰደብ
በቃላቶች ጅረት እውነቴ ሲታጠብ
:
አደዩ ልብሽን በቃላት ባልቀስመው
ጠላት ምቀኛሽን በነገር ባልነድፈው
ቃሌ ባያረካሽ ውስጥሽን ባይነካው
ዝምታየ ጥልቅ ነው ማንም ያተረዳው
:
የቃላት ጥርቅም የሀገሬ ስብጥር
የዓንቀፅ ጋጋታ የድርሰቶች ክምር
ፍቅርን ላያፀና በቃል ለሚሰበር
ዝምታ ሀቅ ነው ምንም የማይበገር
:
ልብሽን ባገኘው በቃላት ደልየ
የሞተ አስነስቼ ያለውን ገድየ
ልብሽ ላይ ከምሰፍር ውስጤን አታልየ
መኖር ይሻለኛል እራሴን በድየ
:
ግን ልብሽ ጆሮ ሁኖ ውስጤን አድምጠሽው
የዝምታ ገዳሜን ቆርበሽ ጎብኝተሽው
የልቤ ኪዳኑን በልብሽ ከትበሽው
ፍቅሬ ላይ ኮብልይ ሀቄን ተረድተሽው






           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir