Get Mystery Box with random crypto!

በወጣትነት ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች:- ===================== በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ | 💖የኔ ፍቅር 😘

በወጣትነት ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች:-
=====================
በሃያዎቹ አጋማሽ አካባቢ የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች በጋብቻ ህይወታቸው ከሌሎቹ ይልቅ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገቡ ወንዶች ካላገቡ ወንዶች ይልቅ ሃብት የማፍራት ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ ያገቡ ወንዶች ገቢና ሃብት እየጨመረ ይሄዳል፡፡
ለጤንነት አስጊ ለሆኑ ነገሮች የመጋለጥ ዕድል ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ በወጣትነታቸው ወቅት ያገቡ ወንዶችና ሴቶች ጤንነታቸውን ጠብቀው የመኖር መልካም አጋጣሚዎችን ያገኛሉ፡፡

በወጣትነት (20ዎቹ አጋማሽ አካባቢ) የሚያገቡ ጥንዶች መልካም የወሲብ ህይወት ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ የትኩስ ወጣትነት ጊዜ ወሲብን ሁልጊዜ የማግኘትና በፍቅር ውስጥ ሆነው የመለማመድ ዕድል አላቸው፡፡ ዕድሜ ሲጨምር የሰውነት ኃይልም እየቀነሰ ስለሚሄድ እንደ ትኩስ የወጣትነት ጊዜ ወሲብን የመለማመድ ዕድሉ ይቀንሳል፡፡

ጥንዶቹ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች (ከተቃራኒ ጾታ ጋር ባለው የግንኙነት መፍረስ) ህይወታቸው ሳይቆስል ወደ ጋብቻ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ግንኙነቶች ወደ ጋብቻ ይዘው የሚመጡት ‹‹ኮተት›› ላይኖር ይችላል፡፡

አንዱ ሌላውን የመቅረጽ ዕድሉ ይሰፋል፡፡ በዚህ የወጣትነት ጊዜ ሁለቱም ተሰርተው ስላላለቁ፣ ይቀራረጻሉ፣ በረጅም ርቀት መልካም ጓደኛሞች ይሆናሉ፡፡

ጤናማ ልጆችን በጊዜ ወልዶ በጊዜ ለማሳደግ መልካም ዕድል ይፈጥራል፡፡ ዕድሜ ከገፋ በኋላ ልጆችን መውለድ የሚቻል ቢሆንም ወላጆች ልጆቹን ለማሳደግ የሚኖራቸው ጉልበት ይቀንሳል፡፡ በወላጆችና በልጆች መካከል የዕድሜ መራራቅም የትውልድ ክፍተትን በጣም ይፈጥራል፡፡

ወጣቶች ጊዜውን ካላወቁስ?
====
አንዳንድ ጊዜ ወጣቶች ተገቢ በሚባለው ዕድሜ ወደ ጋብቻ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ ለዚህ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ይኖራሉ (ወደፊት በሌላ ጽሑፍ ውስጥ እናያለን)፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ዙሪያ ያሉ ተገቢ ሰዎች አንዳንድ በጎ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፡፡
• ግንዛቤን መፍጠር፡ ወጣቶች በተገቢ ዕድሜ ወደ ጋብቻ እንዲገቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማስተማር ወይም ትምህርት የሚያገኙበትን መንገዶች መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡ ልጆች ወደ ታዳጊ ወጣትነት ዕድሜ ክልል ሲገቡ ከህይወት ክህሎት ስልጠና ጋር በማያያዝ ስለጋብቻና መቼ ወደ ጋብቻ መግባት እንደሚቻል ትክክለኛ የሆነ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡
• ማንቃት፡ አንዳንድ ወጣቶች በሌሎች የህይወት ተግባራት ከመጠመድ ወይም እንዲሁ አሁን ያሉበት ኑሮ ስለተመቻቸው ዕድሜያቸው እየሄደ መሆኑን አያስተውሉም፤ ስለወደፊትም እምብዛም አያስቡም፡፡ ስለዚህ ወላጆች፣ ወንድሞች፣ እህቶች፣ ጓደኞች ወይም መንፈሳዊ አገልጋዮች ሊያነቁአቸው ይገባል፡፡ ይህ የማንቃት ስራ በተለያዩ መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ስለጋብቻ በማንሳት መነጋገር፣ መምከር ወይም ታሪኮችን በማውራት ወይም መጽሐፍ እንዲያነቡ በመስጠት ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች ከዚህ ከተኙበት ሁኔታ ሲባንኑ፣ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በመውሰድ ህይወታቸውን በሚጎዳ ግንኙነት ውስጥ ይገባሉ፡፡ በስብዕናቸው ንቁ ያልሆኑ፣ በዓላማና በዕቅድ የማይመሩ፣ ስለወደፊት ከማሰብ ይልቅ በዕለታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ወጣቶች ደውል በመደወል የሚያነቃቸውን ሰው ይፈልጋሉ፡

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir