Get Mystery Box with random crypto!

አትውቀሷት እኔ ችለዋለው የሆንኩትን ልሁን: ይቅር ማዘናቹ አትውቀሷት እሷን፡ ብትሆንም ምክንያት እ | 💖የኔ ፍቅር 😘

አትውቀሷት
እኔ ችለዋለው የሆንኩትን ልሁን:
ይቅር ማዘናቹ አትውቀሷት እሷን፡
ብትሆንም ምክንያት እንዲህ ለመሆኔ፡
ሁሉን እረስቼ ከሷ ቢቀር አይኔ፡
ትቼው የኔን መማር ደጇ ስመላለስ፡
አጅቤ ወስጃት አጅቤ ስመልስ፡
ሰው አይኔ ባይገባ ከሷ አልመጥን ብሎ፡
ልቤም ሄዶ ቢቀር እሷን ተከትሎ፡
ብቻዬን ባወራ ያለች ጎኔ መስሎኝ፡


ያሰብኩት ቢጠፋኝ ቀልቤ ከኔ ርቆኝ፡
ብጓዝ በለሊቱ በማረፊያው ሰአት፡
ብቀመጥ ከሳቱ ከማብሰያው ማጀት፡
ብተኛ አባይ ላይ ብሮጥ ከሰማዩ፡
ደመናንም ባቅፈው ወጥቼ ከላዩ፡
ማይሆነውን ባረግ ያልሆንኩትን ብሆን፡
እኔው ችለዋለው አትውቀሷት እሷን፡
አናቴ ቢናውዝ በፍቅሯ ተነክቶ፡
እርቃኔንም ብሆን ልብስ ከኔ ወልቆ፡
የጫቱን ገራባ ሀይላንዱንም ይዤ፡
ብታዩኝ አብጄ በፍቅሯ ደንዝዤ፡
በሷ ነው ብላቹ ስሟን እንዳጠሯት፡
እኔ ምንም ልሁን ውዴን አትውቀሷት፡፡

           ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
                @Yenefekir
                     @Yenefekir