Get Mystery Box with random crypto!

*ጠባቂ* ፡ ትመጫለሽ ሲሉኝ ትመጫለሽ ብዬ፣ ስጠብቅሽ ነበር በሌለኝ ማጌጫ ልስብሽ ተኩዬ፣ ፡ ትመ | 💖የኔ ፍቅር 😘

*ጠባቂ*


ትመጫለሽ ሲሉኝ ትመጫለሽ ብዬ፣
ስጠብቅሽ ነበር በሌለኝ ማጌጫ ልስብሽ ተኩዬ፣

ትመጫለሽ ካሉኝ ሰዓታት ተጓዙ፣
ቀናትም ተዳምረው አመትን መዘዙ፣
ከበርቴዎች አጥተው በርሃብ ታረዙ፣

እንዲ ነው ሚመስለኝ አንቺን ስጠብቅሽ፣
ከነጋ ማይታይ ጨልሞ የማይመሽ፣

እኔ ያንቺ ጠባቂ ሰዓት ወር ሆኖብኝ፣
እየጠበኩሽ ነው ትመጫለሽ ቢሉኝ፣

እመጣለሁ ስትይ መች ሰምቼ ቃልሽን፣
ሲሉኝ ጠበኩ እንጂ እንዳየው አይንሽን፣

ብታዪ፣
ስትቆዪ፣
ፍጡራን ነፍስ አልባ ሆነው ይታዩኛል፣
በምድር ብቻዬን የቀረሁኝ ያህል ደርሶ ይሰማኛል፣

አዎ በቃ እንዲ ነኝ እኔ ያንቺ ጠባቂ፣
ማወቄን የተውኩኝ ምሁር አላዋቂ፣

ባልተያዘ ተስፋ ባልታየ ጭላንጭል፣
ባልተሰማ ብስራት እንዲያ ስኮበልል፣

ላግኝሽ ብዬ ነው ትመጫለሽ ሲሉኝ፣
ቀጥረሽኝ እንዳልሆን እያወኩ የቆምኩኝ፣
በማታውቂው ስፍራ አንቺን የጠበኩኝ፣
ባልተቆረጠ ቀን ላይሽ የቸኮልኩኝ፣

እንዲ ነኝ ጠባቂሽ ያሉትን ሰምቼ፣
ከቃላቸው ሰብል ተስፋዬን ሸምቼ፣
በተስፋ ቢስ ልቤ ተስፋሽን ዘርቼ፣
እየጠበኩሽ ነው መምጣትሽን እያሰብኩ የኔን መሄድ ትቼ፣

ያንቺ ነገር ሲሆን ልጅ ነኝ አላዋቂ፣
ቀጣሪ ሳይኖረኝ ባልታወቀ ስፍራ ማትመጪን ጠባቂ፡፡


┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir