Get Mystery Box with random crypto!

ልቤን ተቀየምኩት°°°° ውዴ,,,.......... ፍቅሬን በመግለፄ ትከፊ ይሆና | 💖የኔ ፍቅር 😘

ልቤን ተቀየምኩት°°°°


ውዴ,,,..........
ፍቅሬን በመግለፄ ትከፊ ይሆናል
ነገር ግን ተፈርቶ እስከመች ይኖራል
የልቤን አውጥቼ እስኪ ልተንፍሰው
አልኩና ተነሳው ልቤን ላሳርፈው
የውስጤን ህመሜን አምጬ ላፈርጠው
የማይደርስ የለ ደረሰና ወቅቱ
ሀሉንም ነገርኩሽ የልቤን ስሜቱ
ባንቺ እንደሆነ ልቤ መዋተቱ
በቃ አፍቅርሻለው ይሄ ነው እውነቱ
,
,
እስቲ,,, ላስብበት ትንሽ ጊዜ ስጠኝ
ብለሽ የሸኘሽው ልቤ ሰላም ነሳኝ
,
,
ምላሹን በጉጉት ሲጠብቅ የኖረው
ቢሆንም ይሆናል ቢቀርም አይቀርም ብሎ ያሎሰነው
በስተመጨረሻም ይኸው ገላገልሽው
እንደማይሆን ነግረሽ ቁርጡን አሳወቅሽው
,,,
እኔ ግን ልንገርሽ,, እውነቴን ነው ምልሽ
በጭራሽ አላዘንኩ በዛ ቆራጥ ምላሽ
በጣም የታዘብኩት ሁሌም ምቀየመው
እንደማይሆን ሰግቶ ሲኖር የነበረው
ሁሉንም በፀጋ ሊቀበል ያልቻለው
#ልቤን_ተቀየምኩት ሰላምና ደስታ ሊሰጠኝ ያልቻለው

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir