Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.60K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-08-17 13:14:40
7.8K viewsNatnael Gecho, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 13:14:36 ባለትዳር ለሆነች የስራ ባልደረባው ያቀረበውን የፍቅር ጥያቄ ባለመቀበሏ የገደላት ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

የዐቃቤ ህግ መዝገብ ላይ እንደተገለጸው ጌታቸው አለምፀሃይ ክፍሉ የተባለው ተከሳሽ ጥር 2/2011ዓ.ም ከረፋዱ 5፡30 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ሳባ ህንፃ ውስጥ በሚገኘው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 01 ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ የስራ ባልደረባው የነበረችውን ሟች ወ/ሮ መዓዛ ካሳ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ባለትዳር እንደሆነች ብትገልፅለትም የግድ አብረው መሆን እንዳለባቸው ቢወተውታትም ፈቃደኛ ባለመሆኑዋ ምክንያት በስራ ገበታዋ ላይ እያለች በቢላ እያባረረና ለማምለጥ ከቢሮ ስትሮጥ በወደቀችበት በቀኝና በግራ ሆድዋ ላይ ደጋግሞ በመውጋት የሆድ ዕቃዋ ወደ ውጪ ወጥቶ ህይወትዋ እንዲያልፍ በማድረጉ በፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ክስ ተመስርቶበታል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶበት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በከባድ የሰው መግደል ወንጀል በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በዐቃቤ ህግ ክስ ቀርቦበታል ነገር ግን ተከሳሽ በምርመራ ላይ እያለ ከእስር በማምለጡ ምክንያት ክሱ በሌለበት እንዲታይ ተደርጎል፡፡

ተከሳሹ ሆነ ብሎ የተሰወረ በመሆኑ ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ በሚያሰማበት ጊዜ የዐቃቤ ህግን ማስረጃ የመጠየቅ እና የመመርመር መብቱ ታልፎ ፍ/ቤቱ በዐቃቤ ህግ የቀረበው ማስረጃ በበቂ ሁኔታ ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመ መሆኑን ያስረዳ በመሆኑ እንዲሁም መብቱን ጠብቆ የዐቃቤ ህግን ክስ እና ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆኑ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት ነሀሴ 4/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ጌታቸው አለምፀሃይ ክፍሉ ከላይ በምስሉ ላይ ያለው ሰው ሲሆን በምርመራ ወቅት ከእስር አምልጦ ተደብቆ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ያለበት አድራሻ የሚያውቅ ካለ ጥቆማውን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ለፍትህ ሚኒስቴር እንዲያሳውቅ ተጠይቋል፡፡
@wolaitatimes
7.3K viewsNatnael Gecho, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:55:41
ኬንያ ከምርጫ ውጤት መገለጽ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት ተስተውሏል።
7.5K viewsAnt B, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:33:39
ኬንያ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠች

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዊሊያም ሩቶ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን በጠባብ ውጤት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ውጤት ያመላክታል።

በምርጫው ሩቶ ከ50 በመቶው በላይ ድምጽ አግኝተዋል ነው የተባለው።

ከ14 ሚሊየን በላይ ኬንያውያን ድምጽ የሰጡበት የኬንያ ምርጫ፥ አራት ዕጩዎች ተፎካክረውበታል።

በኬንያ የምርጫ ሕግ መሠረት አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ ፕሬዚዳንት ሆኖ ለመመረጥ 50+1 እና ከ47ቱ የሀገሪቱ ክልሎች በ24ቱ ክልሎች ከ25 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ይኖርበታል።

በምርጫው ሩቶ 50 ነጥብ 49 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ፥ ራይላ ኦዲንጋ ደግሞ 48 ነጥብ 8 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋዊ ውጤት ያመላክታል።

ኬንያ በፕሬዚዳንታዊ የፖለቲካ ሥርዓት የምትመራ ሀገር ስትሆን የመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓትን የምትከተል ሀገር እንደሆነች ይነገራል፡፡

ኬንያ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች በኋላ በፈረንጆቹ 1963 የኬንያው የአፍሪካ ብሔራዊ ኅብረት (ካኑ) ፓርቲ ሀገሪቷን በራስ-ገዝ አስተዳደር ለመምራት መንበረ-ሥልጣኑን ተረክቧል፡፡

ጆሞ ኬንያታም በዚሁ ዓመት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት በመሆን ሀገሪቷን እስከ ፈረንጆቹ 1978 ድረስ ኬንያን መርተዋል፡፡

በመቀጠልም ዳንዔል አራፕ ሞይ ሁለተኛው፣ ሙዋዪ ኪባኪ ሦስተኛው እንዲሁም ኡሁሩ ኬንያታ አራተኛው ፕሬዚዳንት በመሆን ኬንያን መርተዋል፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸውን ለ10 አመታት በምክትል ፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።
7.5K viewsNatnael Gecho, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 16:07:36 የለምለሚቷ ዎላይታ መጽሐፍ ደራሲ እና የዚሁ መጽሐፍ ደራሲ አባት አብርሃም ባባንቶ ባላ ናቸው። አቶ አብርሃም ባባንቶ ለዎላይታ ባህልና ታሪክ ዕድገት የነበራቸው እልህ እና ቁጭት ከፍተኛ ነበር፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ ሰለዎላይታ ባህል ታሪክ ማንነት በድፍረት የመግለጽና የመሞገት ባህሪው ወዳጆቹ ሁሌም የምኮሩበት ነበሩ።
በቅርቡ ለአንባቢያን የሚደርሰው "ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ
ትኩረቱ ምኑ ላይ ነው ? ደራሲው ስለመፀሐፉ ምን አስተያየት ሰጡ? ተጨማሪ ልንኩን በመጫን ያንብቡ
https://wolaitatimes.com/በቅርቡ-ለአንባቢያን-የሚደርሰው-ዎላይታ/
7.0K viewsNatnael Gecho, edited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 14:51:34 የከፍተኛ ትምህርት ሀገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ መጽደቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሀገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን፣ የሙያ ሥነ ምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ሥነ-ሥርዓቶችን አካቷል።

መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ኃይል ለማፍራት ከሚደረጉ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው ተብሏል።

በመመሪያው ዝግጅት ሂደት ውስጥ በሥርዓተ ትምህርት እና ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሙያ ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግብዓት የሰጡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ለትግበራ ይፉ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

የጸደቀው መመሪያ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
6.7K viewsNatnael Gecho, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 15:40:11
በግብጽ ካይሮ ከተማ ህዝብ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ የ41 ሠዎች ህይወት አለፈ።

በእሳት አደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 14 ሠዎች እንደቆሰሉ ተገልጿል።

አቡ ሰፊን በተባለው ቤተክርስቲያን የተነሳው ይህ አደጋ ትክክለኛ ምክንያት እስካሁን እንዳልታወቀ የጠቀሰው የኤፒ ዘገባ፤ የፓሊስ ሪፓርት ግን ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዘ አደጋ መሆኑን ያሳያል ብሏል።

የእሳት አደጋው የተነሳው ምእመናኑ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሠንበት ቅዳሴን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት መሆኑንም የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን መግለጿን ዘገባው ያሳያል።

የአገሪቷ የእሳት አደጋ ተቋም 15 ተሽከርካሪዎችን በመመደብ አደጋውን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጉንም ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
@wolaitatimes
7.4K viewsNatnael Gecho, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 16:36:31 በጉራጌ ዞን የአራቱ ወረዳዎች ምክር ቤቶች ዛሬ የወሰኗቸውን ውሳኔዎች ለፌደሬሽን ምክር ቤት ለማስገባት ስልጣን ስላላቸው ያቀርባሉ ተብሏል።

የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ምክር ቤቶች፤ በ“ክላስተር” የሚደራጀውን አዲስ ክልል የመቀላቀል ውሳኔን ያጸደቁት በሙሉ ድምጽ መሆኑን የየምክር ቤቶቹ አባላት ተናግረዋል።(ተጨማሪ ያንብቡ )
https://wolaitatimes.com/በጉራጌ-ዞን-የሚገኙ-አራት-ወረዳዎች-እና-አ/
7.6K viewsNatnael Gecho, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 12:53:42 ሰበር ዜና

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የማረቆ የቀቤናና የመስቃን ወረዳ ም/ቤቶች አስቸኳይ ጉባኤ በማድረግ የክላስተር አደረጃጀቱን በሙሉ ድምጽ ደግፈው አጸደቁ።

ም/ቤቶቹ በአዲሱ ሸዋ ክላስተር አደረጃጀት ዙሪያ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ከም/ቤት አባላት ጋር ውይይት አድርገው ከሌሎች ህዝቦች ጋር በክላስተር አንድ ላይ ለመደራጀት ወስነው በሙሉ ድምጽ አጽድቀል ።

የቀቤና ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በክላስተር አደረጃጀት ላይ አስቸኳይ ውሳኔ አስተላልፏል።
የየወረዳ ምክር ቤቶቹ መንግስት ነባሩን የደቡብ ክልል በሁለት ለማደራጀት ያስቀመጠዉን አቅጣጫ መነሻ በማድረግ በክላስተር ለመደራጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋልል። የምክክር መድረክም ማካሄድ ጀምሯል

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ምክር ቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። የጉራጌ ዞን በፌዴራልና በክልል ደረጃ ከተደረሰው ስምምነት ውጭ ከሌሎች ጋር አብሮ በአንድ ክልል ለመታቀፍ የቀረበውን ምክረ ሃሳብ ውድቅ ያደረገ ብቸኛ ዞን ሲሆን በስሩ የሚገኙ ወረዳዎች ደግሞ በካላስተሩ መታቀፍን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።
7.3K viewsTopia Media, 09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:13:18
"ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል።

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አማኤል አብርሃም ባባንቶ የዎላይታ ሕዝብ ታሪክና ባህል በተለያዩ መንገዶች ባካበቱት ከፍተኛ ልምድ ከኢትዮጵያ የዘመናዊ መንግስት ምስረታ ሂደት ጋር በማቀናጀት ያቀረቡ በመሆኑ በአፃፃፋቸው ለየት ያለ አቀራረብ እንደተጠቀሙ መፃፉን የተመለከቱ ምሁራን አስተያየት ሰጥተዋል።

የመፅሐፉ ደራሲ አቶ አማኑኤል አብራሃም በኢትዮጵያ እስከ ሚኒስቴር ደኤታነት ጨምሮ በተለያዩ በመንግሥት ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ሀገራቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በፊትም የተለያዩ መፅሃፍትን በመፃፍ ልምድ ያካበቱ ናቸው።

በዎላይታ ታሪክ ላይ በርካታ የጥናትና ምርምር መጽሐፍት እየታተሙ ቢሆንም ይህ መጽሐፍ ግን በመረጃ ሀብታምነቱ በአደረጃጀቱና በይዘቱ ለየት ያለና የዎላይታ ታሪክና ችግሮችን በጣም ገላጭ በሆነ መንገድ በበቂ ማስረጃ በማስደገፍ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ያስቀመጠ ረጅም ጊዜ ተወስዶ የተፃፈ መሆኑን አርካ አቦታ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ኘሮፌሰር መስክሮለታል።

ይህ የ "ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በከፍተኛ ጥራትና ደረጃ ለአንባቢያን በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ህትመት ላይ ሲሆን በቅርቡ በይፋ እንደሚደርስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የWT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
7.1K viewsNatnael Gecho, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ