Get Mystery Box with random crypto!

'ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ' የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል። የዚህ መጽሐ | Skyline media

"ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በቅርቡ ለአንባቢያን ይደርሳል።

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ አማኤል አብርሃም ባባንቶ የዎላይታ ሕዝብ ታሪክና ባህል በተለያዩ መንገዶች ባካበቱት ከፍተኛ ልምድ ከኢትዮጵያ የዘመናዊ መንግስት ምስረታ ሂደት ጋር በማቀናጀት ያቀረቡ በመሆኑ በአፃፃፋቸው ለየት ያለ አቀራረብ እንደተጠቀሙ መፃፉን የተመለከቱ ምሁራን አስተያየት ሰጥተዋል።

የመፅሐፉ ደራሲ አቶ አማኑኤል አብራሃም በኢትዮጵያ እስከ ሚኒስቴር ደኤታነት ጨምሮ በተለያዩ በመንግሥት ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ሀገራቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በፊትም የተለያዩ መፅሃፍትን በመፃፍ ልምድ ያካበቱ ናቸው።

በዎላይታ ታሪክ ላይ በርካታ የጥናትና ምርምር መጽሐፍት እየታተሙ ቢሆንም ይህ መጽሐፍ ግን በመረጃ ሀብታምነቱ በአደረጃጀቱና በይዘቱ ለየት ያለና የዎላይታ ታሪክና ችግሮችን በጣም ገላጭ በሆነ መንገድ በበቂ ማስረጃ በማስደገፍ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ያስቀመጠ ረጅም ጊዜ ተወስዶ የተፃፈ መሆኑን አርካ አቦታ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ኘሮፌሰር መስክሮለታል።

ይህ የ "ዎላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በከፍተኛ ጥራትና ደረጃ ለአንባቢያን በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ህትመት ላይ ሲሆን በቅርቡ በይፋ እንደሚደርስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የWT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw