Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የማረቆ የቀቤናና የመስቃን ወረዳ ም/ቤቶች አስቸኳይ ጉባኤ | Skyline media

ሰበር ዜና

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የማረቆ የቀቤናና የመስቃን ወረዳ ም/ቤቶች አስቸኳይ ጉባኤ በማድረግ የክላስተር አደረጃጀቱን በሙሉ ድምጽ ደግፈው አጸደቁ።

ም/ቤቶቹ በአዲሱ ሸዋ ክላስተር አደረጃጀት ዙሪያ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ከም/ቤት አባላት ጋር ውይይት አድርገው ከሌሎች ህዝቦች ጋር በክላስተር አንድ ላይ ለመደራጀት ወስነው በሙሉ ድምጽ አጽድቀል ።

የቀቤና ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በክላስተር አደረጃጀት ላይ አስቸኳይ ውሳኔ አስተላልፏል።
የየወረዳ ምክር ቤቶቹ መንግስት ነባሩን የደቡብ ክልል በሁለት ለማደራጀት ያስቀመጠዉን አቅጣጫ መነሻ በማድረግ በክላስተር ለመደራጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋልል። የምክክር መድረክም ማካሄድ ጀምሯል

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ምክር ቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ። የጉራጌ ዞን በፌዴራልና በክልል ደረጃ ከተደረሰው ስምምነት ውጭ ከሌሎች ጋር አብሮ በአንድ ክልል ለመታቀፍ የቀረበውን ምክረ ሃሳብ ውድቅ ያደረገ ብቸኛ ዞን ሲሆን በስሩ የሚገኙ ወረዳዎች ደግሞ በካላስተሩ መታቀፍን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ።