Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት ሀገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው | Skyline media

የከፍተኛ ትምህርት ሀገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ መጽደቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሀገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን፣ የሙያ ሥነ ምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ሥነ-ሥርዓቶችን አካቷል።

መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ኃይል ለማፍራት ከሚደረጉ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው ተብሏል።

በመመሪያው ዝግጅት ሂደት ውስጥ በሥርዓተ ትምህርት እና ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሙያ ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግብዓት የሰጡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ለትግበራ ይፉ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

የጸደቀው መመሪያ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡