Get Mystery Box with random crypto!

በግብጽ ካይሮ ከተማ ህዝብ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተነሳ የ | Skyline media

በግብጽ ካይሮ ከተማ ህዝብ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ የ41 ሠዎች ህይወት አለፈ።

በእሳት አደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 14 ሠዎች እንደቆሰሉ ተገልጿል።

አቡ ሰፊን በተባለው ቤተክርስቲያን የተነሳው ይህ አደጋ ትክክለኛ ምክንያት እስካሁን እንዳልታወቀ የጠቀሰው የኤፒ ዘገባ፤ የፓሊስ ሪፓርት ግን ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዘ አደጋ መሆኑን ያሳያል ብሏል።

የእሳት አደጋው የተነሳው ምእመናኑ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የሠንበት ቅዳሴን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት መሆኑንም የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን መግለጿን ዘገባው ያሳያል።

የአገሪቷ የእሳት አደጋ ተቋም 15 ተሽከርካሪዎችን በመመደብ አደጋውን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጉንም ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
@wolaitatimes