Get Mystery Box with random crypto!

Skyline media

የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media S
የቴሌግራም ቻናል አርማ skyline7777 — Skyline media
የሰርጥ አድራሻ: @skyline7777
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 49.60K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮ ስካይላይን የቴሌግራም ቻናል ነው። 🙌 ዓላማችን እናንተን ውድ ተከታታዮቻችንን በቅድሚያ ማሳወቅ ፣ ማስተማርና ዘና ፈታ የሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ በማተኮር ማገልገል ነው 🙌
ቁም ነገሮች፣ ቀልዶች፣fun GIF:ትረካዎች:
መጣጥፎች ሌሎችንም ዜናዎች የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗
ለጥቆማና አስተያየታችሁ
For any promotion 👉 @Skyline7777

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-06-24 01:48:06 Make money is important, but without money nothing can be done. Do you want to change things? Want to make more money than your job? Miss BTC, ETH, but also miss DEFI liquidity mining? Contact me as soon as possible, give yourself a chance,want to know more information to make your life change, your savings will grow quickly!!
Please contact to customer service: @Coinbase_Delia
342 viewsTopia Media, 22:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:23:34 #Update #News
የኢትዮጵያ መንግሥት ለእርዳታ አቅርቦት ሥርጭት የሚውል በየወሩ ሁለት ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ መፍቀዱ ተነገሯል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ጦርነቱ ተባብሶ ወደ አጎራባቾቹ የአማራ እና የአፋር ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ ወደ ትግራይ የሚገባው የሰብአዊ እርዳታ እና ነዳጅን አቅርቦት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።

መንግሥት የእርዳታ በተለይም የነዳጅ አቅርቦቱን የህወሓት አመራሮች ለወታደራዊ አላማ ሊያውሉት ይችላሉ የሚል ስጋት ያለው ሲሆን፣ የአውሮፓ ኅብረት ባለሥልጣኑም ይህንን የሚያስወግድ “የቁጥጥር ዘዴ” ተግባራዊ በማድረግ አቅርቦቱ እንዲፋጠን ጠይቀዋል። ተጨማሪ ያንብቡ
https://wolaitatimes.com/መንግሥት-ለእርዳታ-አቅርቦት-ሥርጭት-በየ/
1.9K viewsNatnael Gecho, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:26:58
3.0K viewsNatnael Gecho, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:26:54 ለዚህ ስራዬ “ደመወዝ የማገኘው ከሰማይ ነው” የሚሉት አቶ ማቲዎስ ‘ለስራ ማስኬጂያ’ ልጆቻቸው ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው ይገልጻሉ።

ለዚህ አገልግሎት መቼም ቢሆን ገንዘብ እንደማይቀበሉ ገልጸው “ለምሳሌ ቢሮህን ላድስ የሚል ባገኝ ግን አልከለክልም” ይላሉ።

በሀዋሳ በመልካም ስምና ዝናቸው የሚታወቁት ‘ኢንጀነሩ’ አቶ ማቲዎስ እድሜ ቢጫጫናቸውም ዛሬም ሰዎችን ለማስታረቅ ይተጋሉ።

‘ተጣሉ’ ‘ተቃቃሩ’ ‘ተኮራረፉ’ ‘ተለያዩ’ ‘ተፋቱ’ የሚሉ ቃላትን ፈጽሞ መስማት አይፈልጉም።

ከሰሙት ግን ይወቁትም፤ አይወቁትም ይቅረቧትም አይቅረቧትም እግር ላይ ለመውደቅ እግር ለማጠብ ‘ይቅር በል ይቅር በይ’ ለማለት የ85 ዓመቱ አዛውንት ዛሬም አይሰንፉም ስል ቢቢሲ አማረኛ በገፁ አስነብቧል።
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/
3.1K viewsNatnael Gecho, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:26:54 የልጃቸውን ገዳይ እግር ያጠቡት ኢትዮጵያዊ

አቶ ማቲዎስ ደስታ የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። አሁን የሚኖሩት ሀዋሳ ይሁን እንጂ ትውልድ እና እድገታቸው ዎላይታ ነው።

ድፍን የሀዋሳ ህዝብ ያወቃቸዋል። ያከብራቸዋል። ‘ኢንጅነር’ እያለም ይጠራቸዋል።

‘ኢንጅነር’ የሚለውን ስያሜ በትምህርት ያገኙት አይደለም።

ለሰላሳ ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተዘዋወሩ በቤት እና ህንጻ ግንባታዎች በመሳተፋቸው ነዋሪው የሰጣቸው እንጂ።

በሀዋሳም የኮንስትራክሽን ፍቃድ አውጥተው በርከት ያሉ ግንባታዎችን አከናውነው ተመስግነዋል።

‘ኢንጅነር’ በዚህ ብቻ አይደለም የሚታወቁት።

መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አነስተኛ ቢሮ በመክፈት ‘የእርቅ አገልግሎት’ ይሰጣሉ።

‘የእርቅ አገልግሎት’?! - ግር ሊያሰኝ ይችላል። የሀዋሳ ነዋሪ ግን በደንብ ያውቀዋል።

የ‘ኢንጅነር’ እውቅና ግን በዚህ ብቻ አያበቃም። እስከዛሬ ድረስ ‘ጉድ’ እየተባለ የሚወራ ነገር ፈጽመዋል - የልጃቸውን ገዳይ ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ‘ይቅር ለእግዚያብሔር ብያለሁ’ ብለዋል።

ይቅርታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እግሩንም አጥበዋል። ነገሩን አንድ በአንድ እንየው!

‘ኢንጅነር’ ማቲዎስ እና ሟቹ ልጃቸው
አቶ ማቲዎስ ደስታ የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። አሁን የሚኖሩት ሀዋሳ ይሁን እንጂ ትውልድ እና እድገታቸው ዎላይታ ነው።

በወጣትነት ዘመናቸው በመጀመሪያ የብረታ ብረት በመቀጠል የግንባታ ስራዎች ላይ እየተቀጠሩ ሰርተዋል።

በኋላም በግንባታ ሙያው የያዙትን ልምድ በማጠናከር እና ፍቃድ በማውጣት በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ ግንባታ ሲሰሩ ኖረዋል። በዚህ ስራቸው ያልረገጡት የኢትዮጵያ ክፍል የለም።

ከ54 ዓመታት በፊት በ1960 ዓመተ ምህረት ደግሞ ትዳር መሰረቱ።

“በትዳሬ ደርዘን ልጆችን አፍርቻለሁ” የሚሉት አቶ ማቲዎስ ከ12 ልጆቻቸው 12 የልጅ ልጆችን እንዳዩም ይናገራሉ።

ከልጅ ልጇቻቸው አንደኛዋ የሟቹ ልጃቸው የእስራኤል ማቲዎስ ልጅ ነች። አሁን የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን እየተከታተለች ነው።

እስራኤል “በጣም ሙያ ያለው የምወደው ልጄ ነበር” የሚሉት አቶ ማቲዎስ ከአስራ ሁለቱ ልጆቻቸው 5ኛው በሆነው እስራኤል ሞት እጅግ አዝነው እንደነበር ይገልጻሉ።

በ1998 ዓመተ ምህረት አንድ ቀን ከምሽቱ አምስት ሰዓት አከባቢ እስራኤል በሚኖርበት አካባቢ ግጭት እንደተፈጠረ እና ልጃቸውም ጉዳት እንደደረሰበት ለአቶ ማቲዎስና ቤተሰቦቻቸው ይነገራቸዋል።

“በዚያን ጊዜ ባለቤቴ በህይወት ነበረች። ሌሎች ሰዎችም ነበሩ ሮጠው ሄዱ - ለማየት። እኔ ግን ተንበርክኬ ጸለይኩ። ጸሎቴን ጨርሼ ስሄድ ሰዎች ተሰብሰበው ደረስኩ። ከዝያ ፖሊሶች በምርመራ አጣርተው [አስክሬኑን] አመጡ” ሲሉ የሚያስታውስት አቶ ማቲዎስ በተፈጠረ ጸብ ልጃቸው በስለት ተወግቶ መገደሉን ይናገራሉ።

“ልጄን የገደልከው አንተ ነህ እኔ ግን አንተን እወድሃለሁ”

አቶ ማቲዎስ ደስታ እና በስለት ተወግቶ የተገደለው ልጃቸው "የልጄ ገዳይ ተፈረደበት እና ማረሚያ ቤት ገባ። ማረሚያ ቤት ገባሁና ሰው [ገዳዩ] እሱ ነው ብሎ በርቀት አሳየኝ። እሱ ሳያየኝ ከኋላው ሄድኩ። ከዛ እግሩን ያዝኩት። ‘ለምን ያዝክ?’ አለኝ። ‘አይ ያንተን እግር ለማጠብ ነው የመጣሁት’ አልኩት።

‘ለምን አለ?’ ‘ልጄን የገደልከው አንተ ነህ እኔ ግን አንተን እወድሃለሁ አልኩት። ልጄን እስራኤልን ገድለሃልና አንተ የኔ ልጅ ትሆናለህ አልኩት።’

[ይህንን ሲሰማ] አፈር ላይ ተንከባለለ። አትንከባለል አልኩት። በእጄ ሃይላንድ ይዤ ነበር በዛ ነው ያጠብኩት። ...ዶክመንት አዘጋጀሁ እና ጉዳዩ ወደ ይቅርታ ቦርድ ሄደ። ከዚያም ተፈታ” ሲሉ ያኔ የሆነውን ያስታውሳሉ።

“ሰው እንኳን ልጁን የገደለበትን የሰደበበትን ይቅር ለማለት ሊቸገር እንደሚችል አውቃለሁ” የሚሉት አዛውንቱ ሰዎች ለማመን የሚቸግራቸውን ይህንን ነገር ፈጽመውታል።

ይሄ ነው ሰውን ‘ጉድ’ ያሰኘው። ሰውን ያስገረመው። እውነት አልመስልህ ያለው።

“ ‘አንተ ይቅርታ ስታደርግ ወንድሞች ልጆች ቤተሰቦች አይቀየሙህም ወይ? ያሉኝ አሉ።

እኔ ይሄንን አላውቅም አእምሮዬ ውስጥ የተሞላው ይቅር በል የሚል ነገር ነው እንጂ ያን ነገር የሚያውቀው እግዚያብሔር ነው’ ነው ያልኩት።

የኔ ልጆች እግዚያብሔርን ስለሚያመልኩ ሌሎች [ደግሞ] ስለ እኔ ስለሚያውቁ ሌላ ነገር አልተናገሩም” ሲሉ ያስረዳሉ።

ቢቢሲ ይቅርታ ያደረጉለትን ሰው እግር ያጠቡት በምን ምክንያት ነው? ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ጌታ ኢየሱስ እግር አጥቧል። ይሄንን ለማስተማር ነው ራሱን ዝቅ ያደረገው” ስለዚህም በሚያምኑበት እምነት መሰረት ፍጹም ይቅርታ ማድረጋቸውን ለመግለጽ ይህንን ፈጽሜያለሁ ብለዋል።

‘ኢንጅነር’ ይቅርታ ማድረጋቸውን የሰሙት የገዳይ ቤተሰቦች “እርስዎ ይህንን ካደረጉ ምን እናድርግልዎት” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ያስታውሳሉ።

እሳቸው ግን “እኔ ዋጋውን ከሰማይ ነው የማገኘው” ብለው ምንም አይነት የውለታ ምላሽ አልተቀበሉም።

ከዚህ በኋላ ከገዳዩም ይሁን ከቤተሰቦቹ ጋር ተገናኝተው አይውቁም። እሳቸው ይቅርታ ያደረጉለትን ሰው ቢያገኙትም ቢጠይቃቸው ደስ ይላቸዋል። ሆኖም ከዚያ ቀን በኋላ አልተገናኙም።

“ተጠራጥሮ ይሆናል። ይቅርታ ያደረገው ሌላ ነገር አስቦ ይሆናል ብሎ ይሆናል የጠፋው” ብለዋል።

‘ማንም የማይደፍረውን’ ይህንን በማድረጋቸው የመንፈስ እርካታ እንዳገኙ የሚጠቅሱት አቶ ማቲዎስ ውሳኔያቸው በህይወታቸው “እጅግ ደስተኛ” እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ።

“በሀገር ስለሚወራ፣ የእግዚያብሔር ቃል ‘ይቅርታ አድርጉ’ ስለሚል [ያን ስላደረኩ] በጣም ደስተኛ ነኝ” ሲሉም አክለዋል።

አቶ ማቲዎስ በሀዋሳ ከተማ የእርቅ አገልግሎት ይሰጣሉ።

የ‘ኢንጅነሩ’ የእርቅ አገልግሎት
በነገራችን ላይ፣ ኢንጅነሩ በደቡብ ክልል የሀገር ሽማግሌም ናቸው።

አቶ ማቲዎስ በመኖሪያ ቤታቸው በከፈቱት ቢሮ አማካኝነት ደግሞ ያለምንም ክፍያ የእርቅ አገልግሎት ይሰጣሉ።

በርግጥ ይህንን አገልግሎት የጀመሩት ልጃቸው ከመገደሉ እና እሳቸውም ይቅርታ ከማድረጋቸው በፊት ነው። 1995 ዓመተ ምህረት አካባቢ።

አገልግሎታቸው ከሳቸው ስም ጋር በሀዋሳ ከተማ የገነነው ግን ከዚያ ክስተት በኋላ ነው።

‘ይቅር በሉ’ ‘ይቅርታም ጠይቁ’ ‘ታረቁ’ ‘ቂም አትያዙ’ እያሉ ይመክራሉ። በተግባር የተደገፈ ምክር!

ከቤታቸው መግቢያ ላይ የእርቅ አገልግሎት እሰጣለሁ የሚል ማስታወቂያ ለጥፈዋል።

በራቸው ደግሞ እርቅ ለሚፈልግ ለየትኛውም ሰው ክፍት ነው።

እሳቸው ይህንን አገልግሎት በሁለት አይነት መልኩ ያከናውኑታል።

አንድ: ሁለት ያልተስማሙ ሰዎች ወደሳቸው መጥተው ‘አስማሙን’ ‘ፍረዱን’ ይላሉ።

እሳቸውም በቻሉት መንገድ ለማስታረቅ ይሞክራሉ። የማይታበየው ሃቅ ግን የመጡት ሰዎች ቢያንስ በሳቸው ፊት ተማምነው እና ተስማምተው መውጣታቸው።

ሁለት: የተጣሉ ሰዎች መኖራቸውን ሲሰሙ ተበድያለሁ ብሎ የሚያስበው ሰው ጋር ሄደው እግር ላይ ወድቀው እና እግር አጥበው ይቅርታ እንዲያደርጉ ይለምናሉ።

“ከሳሽ እና ተከሳሽ እኔ ቢሮ ከመጡ በኋላ ከሳሹን ተንበርክኬ እግር አጥባለሁ። እሱ ‘እንደዚህ ያለ ዕድሜ ኖረው፤ እንደዚህ ያለ ኮንትራክተር የነበሩ፤ እንዲህ ያሉ የልጆች አባት ሆነው እግር ያጥባሉ ብለው እሺ’ ይላሉ’” ብለዋል።

ቁጥሩን በትክክል ባያውቁትም የተለያዩ ባለትዳሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን በዚህ መልኩ ወደ እርቅ መመለሳቸውን ይናገራሉ።
2.8K viewsNatnael Gecho, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 16:35:10 የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናት ጤና ልማት ላይ ያተኮረው የአድቮከሲ ኮንፍራንስንየቀድሞ የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ አስጀመሩ ተጨማሪ ያንብቡ
https://wolaitatimes.com/በእናቶችና-የጨቅላ-ህጻናት-ጤና-ልማት-ላይ/
2.2K viewsNatnael Gecho, 13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 08:13:23
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ህገ ወጥና ኢመደበኛ በሆኑ ሃይሎች በንጹሀን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ንጹሀንን የመግደልና ማህበረሰቡን የማሸበሩ የዚህ አይነቱ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስም ገልጸዋል።

ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታን መመለስ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/
3.0K viewsNatnael Gecho, edited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:00:12
በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል ሀኮ ወረዳ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቆ ተመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ትምህርት ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገቢ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባ ሲሆን፥ ለግንባታውም 11 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ትምህርት ቤቱ 12 የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ሁለት ቤተ ሙከራ እና አንድ ቤተመጻሕፍት አለው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል የመጀመሪያውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ያስመረቀው።

ፅህፈት ቤቱ በሁለተኛው ዙር ካስገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይህ ሶስተኛው ሲሆን በጥቅሉ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስመርቋል።
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/
2.2K viewsNatnael Gecho, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 17:01:08
1ሺህ 127 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ዛሬ በ3 ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 127 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሱት ውስጥ ስድስቱ ሕጻናት መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ38 ሺህ 853 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/
2.3K viewsNatnael Gecho, 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 18:45:15 የቀድሞ የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት እና የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ከቪኦኤ አማርኛ (#VOA) ጋር ያደረጉት ቆይታ
#VOA #Amharic #exclusive #interview with H.E. Roman Tesfaye, the former First Lady of Ethiopia and CEO of HRF


1.1K viewsNatnael Gecho, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ