Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን | Skyline media

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች በንጹሀን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ህገ ወጥና ኢመደበኛ በሆኑ ሃይሎች በንጹሀን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ንጹሀንን የመግደልና ማህበረሰቡን የማሸበሩ የዚህ አይነቱ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስም ገልጸዋል።

ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታን መመለስ መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
የ WT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/